የአርዛፕ ድንጋዮች
የአርዛፕ መልህቅ ድንጋዮች በምሥራቅ ቱርክ አገር ተራራዎች የሚገኙ 12 እጅግ ታላቅ ድንጋዮች ናቸው። እነዚህ ድንጋዮች በአንዳንድ ክርስቲያን መምህር በተለይም በአቶ ዴቪድ ፋሶልድ እምነት የኖህ መርከብ መልህቅ ድንጋዮች መሆናቸውን ያምናል። ይህ እምነት እያንዳንዱ ድንጋይ በጫፍ ላይ ትልቅ ቀዳዳ ስላለበት ነው። ለኖህ መርከብ መልህቅ እንደ ነበረው የሚል ሀሣብ በቁራን ውስጥ ተገኝቷል። በተጨማሪም በሱመራዊው አፈ ታሪክ ጊልጋመሽ፣ ስለ ማየ አይህ ሲተረክ መልህቅ ድንጋዮች እንደ ነበሩት ያለው ሀሣብ ደግሞ ተገኘ።
እንደነዚህ የመሳሰሉት መልህቅ ድንጋዮች ከሜዲቴራኔያን አካባቢ ሥነ ቅርስ የሚታወቁ ናቸው። ሆኖም ሊቁ ሎረንስ ኮሊንስ የአርዛፕ ድንጋዮች ከሚገኙበት ሥፍራ ዙሪያ (ምሥራቅ ቱርክ) እንደ ተሠሩ ብሏል።
የውጭ ድረገጽ
ለማስተካከልስለ ድንጋዮቹ የሚገልጸው ኅልዮ በሙሉ (እንግሊዝኛ) Archived ጁላይ 12, 2007 at the Wayback Machine
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |