የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ እግር ኳስ ማህበር ወይም የቻይና እግር ኳስ ማህበር የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1924 እ.ኤ.አ. በቤዪጂንግ የተመሠረተ ሲሆን የፊፋ አባል የሆነው በ1931 እ.ኤ.አ. ነው። ከየቻይና የእርስ በርስ ጦርነት በኋላ እንደገና በ1955 እ.ኤ.አ. የተቋቋመ ሲሆን፣ በ1979 እ.ኤ.አ. እንደገና የፊፋ አባል ሆኗል።