የተፈጥሮ ጭማሪ
የተፈጥሮ ጭማሪ በሰው ልጅ ጥናት በኩል ከአንድ አገር (ወይም ክፍላገር ወዘተ.) ጥሬ ልደት መጠን ቁጥር (ልደቶች በየሺህ ሕዝብ በየዓመቱ) የዚያው አገር ጥሬ ዕረፍት መጠን (እረፍቶች በየሺህ ሕዝብ) ሲቀነስ የሚገኘው የሕዝቡ ጭማሪ መጠን ነው። ይህ መጠን ግን «የተፈጥሮ» በመባሉ የሰው ልጅ ፍልሰቶች (ሰዎች ከአንድ አገር ወደ ሌላ የሚዛወሩበት መጠን) ቸል ይላል።
የጥሬ ዕረፍት መጠን ከጥሬ ልደት መጠን ይልቅ ሲበዛ፣ ጭማሪ ሳይሆን የተፈጥሮ ቅነሳ አለ። አሁን በተለይ በምሥራቅ አውሮጳና በጃፓን ውስጥ ብዙ ልደቶች ስለሌሉ የተፈጥሮ ቅነሳ አለ፤ የሕዝብ ቁጥር በየዓመቱ ይቀነሳል። ሆኖም በአንዳንድ አገር የፍልሰቱ መጠን ከፍ ያለ በመሆኑ (ብዙ ሰዎች ወደዚያው አገር በመግባት ከመውጣት በላይ)፣ በጠቅላላ የኗሪዎቹ ቁጥር በየዓመቱ ይጨመራል። ከሁሉ ይልቅ የሆነው ቅነሳ ግን በሃይቲ ነው። በሃይቲ የልደት መጠን እጅግ ከፍተኛ ቢሆንም፣ የዕረፍት መጠን ግን ከዚያ እንኳን ይበዛል፤ ስለዚህ በጠቅላላ ቅነሳ አለ።
በአፍሪቃ ግን ከእረፍቶቹ ይልቅ ብዙ ልደቶች ስላሉ የተፈጥሮ ጭማሪ አለ፤ የሕዝቡም ቁጥር እየበዛ ነው። ከአገራት ከሁሉ ከፍተኛ የሆነው የጭማሪ መጠን ለኒጄር ነው።