ኢትዮጵያዊው ደራሲ፤ ጋዜጠኛ አና መምሀር የሺጥላ ኮከብ መስከረም 21 ቀን 1958ሃረርጌ ክፍለ ሃገር ተወልዶ የአንደኛ አና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በባቢሌ፤ ወተር አና ሃረር እንዲሁም የከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በሆሳእና ልጅ አበበ ወ/ ሰማያት ት/ቤት ተከታትሏ። ቀጥሎም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በባዮሎጂ በቢ ኤስ ሲ ዲግሪ ተመርቆ በኢሉባቦር ክፍለሃገር ሞቻ አዉራጃ እና መቱ ፤ እንዲሁም በአዲስ አበባ የከፍተኛ 12 እና በቀድሞው ተፈሪ መኮንን (እንጦጦ አጠቃላይ ) በመምሀረነት አገልገሏል። የሺጥላ ኮከብ ዶሰኛው እና ወገግታ የተሰኙ ከፍተኛ ተነባቢነት ያላቸዉ ልቦለዶቹን ገና በወጣትነት እድሜው ያበረከተ ሲሆን በጋዜጠኛነት ህይወቱም በየካቲት መጽሄት ዋና አዘጋጅነት፤ በአዲስ ዘመን እና የ ኢትዮጵያ ሄራልድ አዘጋጅነት አገልግሏ። በተለይ ለየት ያሉ የመጣጥፍ (ኤሴይ) አቀራረቦቹ ተንኳሽ (ፕሮቮካቲቭ) እና አነጋጋሪ በመሆናቸው ይታወቃሉ። በአሁኑ ጊዜ ነዋሪነቱ በጀርመን ሃገር ነው።