የሲቢሊን ራዕዮችግሪክ የተጻፉ በ12 መጻሕፍት ተከፋፍለው የትንቢት ግጥሞች ክምችት ናቸው። እነሱ የሲቢል (ሴት ነቢይ) ሥራ ናቸው ይላሉ። ይሁንና የዛሬ ሊቃውንት እኚህ ትንቢቶች በአይሁዶች ወይም በክርስቲያኖች ተጽፈው ዕውነተኛ የሲቢሊን መጻሕፍት ሊሆኑ አይችሉም ባዮች ናቸው። ትንቢቶቹ የተባሉ ከድርጊቶቹ በኋላ ተነበዩና ከ2ኛው መቶ ዘመን ዓክልበ እስከ 6ኛ መቶ ዘመን ከክርስቶስ በኋላ መጻፍ ነበረባቸው ሲሉ ይክራክራሉ። ምክንያቱም ከትንቢቶቹ መኃል ብዙዎች ስለ መሢህ ወይም ስለ ሌላ መጽሐፍ ቅዱስ ነክ ጉዳይ የሚነበዩ ናቸው። ለሎችም ደግሞ ስለ ሮማ መንግሥት ዕድልና ታሪክ ስለሚነበዩ ስለዚህ ከድርጊቶቹ በኋላ መነበይ ነበረባቸው ይላሉ የዛሬው ምሁራን።

ቢሆንም እነዚህ መጻሕፍት የአይሁድና የክርስትና ሃይማኖት ነክ ጉዳዮች ብቻ ሳይሆን ከግሪክና ከሮማ አረመኔ ሃይማኖት የተለቀሙ ብዙ ስሞች ወይም ሃሳቦች ይገኙባቸዋል። ለምሳሌ ከግሪክ ጸሐፊዎች ሆሜርሄሲዮድ፣ እንዲሁም ከብሉይ ኪዳን ስለ ኤደን ገነት ስለ ኖህና ስለ ባቢሎን ግንብ የሚል ወሬ አለባቸው።

በጥንት የታወቁት 'ሲቢሊን መጻሕፍት' በሮማ ከተማ በቤተ መቅደስ ይጠበቁ ሲሆን በ90 አመት ዓክልበ በእሳት ተቃጠሉ። ስለዚህ የሮማ ላይኛ ምክር ቤት (ሴናት) በ84 ዓክልበ ተልእኮዎች ተመሳሳይ ትንቢቶች አገኝተው እንዲተኩ ላኩዋቸው። ከዚያ እስከ 397 ዓ.ም. ቆዩ። በዚያን ጊዜ የአሪዮስ ክርስትና ትምህርት አራማጅ የሆነ ስቲሊኮ እንዳቃጠላቸው ይባላል። ነገር ግን ስለ ይዞታቸው ብዙ አይታወቅምና ከሚታወቁት 'ሲቢሊን ራዕዮች' ጋር አንድላይ አይሆኑም ብለው ምሁራን ይገመታሉ።

አንድ ክርስቲያን ፈላስፋ አቲናጎራስ አቴናዊው ክርስቲያኖች በአረመኔ ሮማ መንግሥት በተሠቃዩበት ወቅት በ168 ዓ.ም. ወደ ቄሣር ማርቆስ አውሬሊዮስ 'አቤቱታ ለክርስቲያኖቹ' ሲጽፍ ከነዚህ ዛሬም እውቅ ከሆኑት ንግሮች ቃል ለቃል በሰፊ መጥቀሱ እርግጠኛ ነው። የጠቀሳቸው ከነሆሜርና ሄሲዮድ ጋር ሲሆን ብዙ ጊዜ 'እነዚህ መጻሕፍት ሁሉ ለቄሣር ታዋቂ ናቸው' ብሎ ጻፈ። በዚህ ጊዜ መጻሕፍቱ በሮማ ገና ይገኙ ነበርና ስለዚህ ምናልባት ከሲቢሊን ራዕዮች አንዳንድ ትክክለኛ እንደ ሆነ ይቻላል።

ሌሎች የክርስትና አባቶችና ሃዋርያት ደግሞ የሲቢሊን ራዕዮችን ጠቀሱ። ቴዎፊሎስ ዘአንጾኪያአንጾኪያ ጳጳስ (170 ዓ.ም. አካባቢ) ቀለምንጦስ ዘእስክንድርያ (190 ዓ.ም. አካባቢ) ላክታንትዮስ (295 ዓ.ም. አካባቢ) እና ቅዱስ አውግስጢኖስ (390 ዓ.ም. አካባቢ) ሁላቸው ጠቅሰዋቸዋል ። ዩስቲኑስ ሰማዕት (140 ዓ.ም. አካባቢ) ደግሞ አንዳንድ የሱማይ ሲቢል ትንቢቶች ጠቅሰዋል። ይህ ጥቅስ ግን ዛሬ በሚታወቁት ንግሮች መሓል አይገኝም።

የሚከተለው ታዋቂ ጥቅስ የባቢሎን ግንብን ታሪክ ይመስላል።

ከሶስተኛው መጽሐፍ መስመሮች 119-147፦

(III: 119-147)

«በአሦር አገር ግንብ ሲሠሩ
(ሁላቸውም አንድ ቋንቋ ሲናገሩና
ወደ ላይ ወደ ኮከባም ሰማይ ለማረግ ሲወሰኑ
በአየሩ ላይ ግን ሕያዉ ወዲያው
ታላቅ ኃይል አኖረና ነፋሶች ከላይ
ታላቁን ግንብ አወረዱና መዋቲዎችን አስነሡ
እርስ በርስ እስከሚጣሉ ድረስ፤ ስለዚህ ሰዎች
ያችን ከተማ ባቢሎን ብለው ሰየሙዋት)
ግንቡ ሲወድቅና የሰዎች ልሳናት
ወደ ልዩ ልዩ ድምጾች በያይነቱ ሲዞሩ፣ ወዲያው ምድር ሁሉ
በሰዎች ተሞላችና መንግሥታት ተከፋፈሉ።
ከዚያም ከማየ አይህ በቅድሚያ ሰዎች ላይ ከመጣ ጀምሮ
ከመዋቲ ሰዎች አሥረኛው ትውልድ ታየ። ክሮኖስም ነገሠ
ቲታንያፔቶስም፤ ሰዎችም፦
'የጋያ እና የኡራኖስ ጥሩ ተወላጆች' አሏቸው
የምድርና የሰማይ ስሞች ለነሱ በመስጠት፥
ከመዋቲ ሰዎች መጀመርያዎቹ ነበሩና።
እንግዲህ በምድሪቱ ሦስት ኩፋሌዎች ነበሩ
እንደ እያንዳንዱ ሰው ድርሻ
እያንዳንዱም የገዛ ድርሻውን ነግሶ
አልተጣሉም - የአባት መሓሌ ነበረና
ድርሻዎቻቸውም እኩል ነበርና። ነገር ግን ጊዜው
ከእድሜ የተነሣ በአባቱ ላይ መጣ፥
እሳቸውም ሞቱ፤ ልጆቹም መሓሌውን በመጣስ
እርስ በርስ መራራ ትግል አስነሳሱ
የትኛው ንግሳዊ ማዕረግና ግዛት
በመዋቲዎች ላይ እንዲገኝ፤ እርስ በርስም
ክሮኖስና ቲታን ተዋጉ...»

(III: 1004-1031) - ሲቢሊቱ ስለ ራሷ ታሪክ የምትለው:-

«እነዚህን ነገሮች አሳይሃለሁ - እኔ በእብደት የወጣሁ
ከአሦር ባቢሎን ረጅም ቅጥሮች
ወደ ሄላስ (ግሪክ)፤ የእግዜርን መዓት ሁሉ ለመናገር...
ለመዋቲዎችም ስለ መለኮታዊ ምስጢራት
እነበይ ዘንድ። ሰዎችም
በሄላስ ከውጭ አገር እንደምሆን
ከኤሩትራይ ያለ ህፍረት እንደ ተወለድኩ ይላሉ፤ ሌሎችም
'ሲቡል' እንደምሆን ከእናት ኪርኬ ትወልጄ
ከአባት ግኖስቶስም እብድና ውሸታም።
ዳሩ ግን ነገሮች ሁሉ ለማለፍ በመጡበት ጊዜ
ታስታውሱኛላችሁ፤ ማንም ዳግመኛ
እብዲት አይለኝም የታላቅ አምላክ ነቢይቱ።
ቀድሞ ለአያቶቼ ምን እንደ ደረሰ
አሳይቶኛልና፤ ከመጀመርያው ምን እንደ ነበር
እግዜር አሳውቆኛልና፤ በልቡናዬም ውስጥ
ከእንግዲህ ወዲህ የሚሆኑትን ሁሉ አምላክ አኖረ፤
ሊመጣ ያለውን ነገር እነበይ ዘንድ፣
የነበረውንም፣ ለሰዎች እነግረው ዘንድ።
ዓለም በጎርፍ ሲሞላ
ከውሃ፣ አንድ ጨዋ ሰውም
ብቻውን ሲቀር፣ በእንጨት ቤት
ከዎፍም ከእንስሳም ጋር በውኆቹ ላይ ሲሔድ፣
ዓለም እንደገና ይሞላ ዘንድ፥
እኔ የልጁ ሙሽራ ነበርኩ ከወገኑም ነበርኩ
መጀመርያ ነገሮች የደረሱበት መጨረሻም
ሁሉ የታወቁለት፤ እንግዲህ ከገዛ አፌ
እነዚህ እውነተኛ ነገሮች ሁሉ ግልጽ ይሁኑ።»

የውጭ መያያዣዎች

ለማስተካከል