የማርያም ቅዳሴ ገፅ ፲፯

ዘቅዱስ ሕርያቆስ

የማርያም ቅዳሴ ገፅ ፲፯

ዘቅዱስ ሕርያቆስ


፻፴፬ ፤ ጸልዩ አቡነ ዘበሰማያት ።
፻፴፭ ፤ እንግዲህ እስከ ደኃሪት እስትንፋስ (ዕለተ ሞት) ድረስ ይህን ቃል እንስማ በምንከሰስበት ገንዘብ በሚፈረድብንና ይቅር በሚለን ገንዘብ ።
፻፴፮ ፤ ወልድ ለመፍረድና ይቅር ለማለት ከሰማየ ሰማያት እንደመጣ እንደዚሁም ይህ ኅብስት ከሳሽ ነው ፈራጅም ነው ይቅር ባይም ነው ።
፻፴፯ ፤ ከዚህ ከሚያስደነግጥ ቃል የተነሣ ነፍስ ትፍራ ሕዋስ ይንቀጥቀጥ በውስጥ ያለ ነፍስ የልብ ደጅም ይሰበር ።
፻፴፰ ፤ ይህን መለኮታዊ ኅብስት እንሆ ተቆረሰ ። ይህ ማኅየዊ ጽዋ እንሆ ተዘጋጀ ። የሚቀበል ይምጣ ። አስቀድሞ ራሳቹህን መርምሩ ሰውነታቹህንም አንጹ ።
፻፴፱ ፤ ንጹሕ ያልሆነ ሰው ቢኖር ይወገድ በኃጢአት የወደቀ ሰው ቢኖር አይርሳ የማይረሳ ነውና ።
፻፵ ፤ ይህን ቁርባን የሚያቃልል ሰው ቢኖር አይቅረብ ይከልከል እንጂ ይህ ኅብስት እንደምታዩት እንደ ምድራዊ ኅብስት ብላሽ አይደለም ። እሳት መለኮት ነው እንጂ ።
፻፵፩ ፤ ይህን ኅብስት የሚጎርስ ምን አፍ ነው ይህን ኅብስት የሚያላምጥ ምን ጥርስ ነው ይህን ኅብስት የሚችል ምን ሆድ ነው ።?
፻፵፪ ፤ አሁንም አምላካችን ሆይእንደ ቸርነትህ ነው እንጂ እንደ ኃጢአታችን አይደለም እንበል ።
፻፵፫ ፤ አምላካችን ሆይ እንደ ቸርነትህ ነው እንጂ እንደ ኃጢአታችንም አይደለም (፫ ጊዜ) ።
፻፵፬ ፤ ከዚህም በኋላ የመድኃኔ ዓለም የመላዕክት ሠራዊት በመድኃኔ ዓለም ፊት ይቆማሉ ። መድኃኔ ዓለምን ያመሰግኑታል የመድኃኔ ዓለም ሥጋውና ደሙን ።
ወደ መድኃኔ ዓለም
ፊት እንቅረብ እርሱንም በማመን ለክርስቶስ እንገዛለን ።