የማርያም ቅዳሴ ገፅ ፲፮

ዘቅዱስ ሕርያቆስ

የማርያም ቅዳሴ ገፅ ፲፮

ዘቅዱስ ሕርያቆስ


፻፳፬ ፤ ለጸሎት ተነሡ አቤቱ ይቅርበለን ሰላም ለሁላቹህ ይሁን
ከመንፈስህ ጋራ ።
፻፳፭ ፤ የመፈተት ጸሎት ።
ሁሉን የፈጠረ ሁሉን የጀመረ ሁሉንም የፈፀመ ሁሉንም የጨበጠ እግዚአብሔር መላዕክትና የመላዕክት አለቆች መናብርትና ሥልጣናት አጋእዝትና ኃይላት ፀሐይና ጨረቃ ከዋክብትም ድርገታትም የሚሰግዱለት ተገዢዎችና ግዛቱ ጉልቱም ናቸውና በሁሉ ባለጠጋ ሲሆን ራሱን ከሁሉ ድሀ አደረገ ።
፻፳፮ ፤ ኃያል ወልድን ፍቅር ከዙፋኑ ሳበው እስከሞትም አደረሰው ።
፻፳፯ ፤ የሚስቡትን ሰዎች በቀንዱ የማይበረታታ ለሚያርዱትም ሰዎች አንገቱን የሚያዘነብል ላም ምን ይደንቅ ።
፻፳፰ ፤ በሚሸልተው ፊት የማይናገር በግ እንደምን ያለ ነው ?። በመከራው ጊዜ በሚወጉት ፊት አፉን ያልገለፀ ምን ትዕግሥት ነው ?።
፻፳፱ ፤ ዮሴፍ ከተወጃጃት ክቡር ዕንቁም በውስጧ ካገኘባት ሣጥን የተገኘ ኅብስት እንደምን ያለ ነው?።
፻፴ ፤ በውስጧ ሰው ካልገባባት አዳራሽ የተገኘ ጽዋ እንደምን ያለ ነው ?።
፻፴፩ ፤ ፈፅሞ የተለየ ሳይሆን ከዚህ ኅብስት የተለየ ይህ ትእምርተ መስቀል ምን ድንቅ ነው መልኩ ልምላሜው ጣዕሙ አንድ ነው እንጂ ።
፻፴፪ ፤ መለኮቱ ከሰውነቱ ፈፅሞ የተለየ እንዳይደለ እንደዚሁም ይህ ትእምርተ መስቀል ከዚህ ኅብስት ፈፅሞ የተለየ አይደለም ።
፻፴፫ ፤ እንዲሁም ገናናነትህ ከትሕትናችን ትሕትናችን ከገናናነትህ ጋራ አንድ ይሁን ዓለምን የያዝህ አንተ አምላካችን ።