ዞዊ ዴሸኔል
ዞዊ ክሌር ዴሸኔል (ተወለደች ጃኑዋሪ 17 ቀን 1980 እ.ኤ.አ.) አሜሪካዊት ተዋናይት፣ ዘፋኝ እና የዘፈን ጸሐፊ፣ ሞዴል እና ፕሮድዩሰር ነች። የመጀመሪያውን ፊልሟን በ1999 እ.ኤ.አ. መምፎርድ ውስጥ፥ ከዚያም በመቀጠል ኦልሞስት ፌመስ በተባለው በእ.ኤ.አ. 2000ው የካሜሮን ክሮው ፊልም ላይ የአኒታ ሚለርን ገጸ-ባሕርይ ይዛ ተጫውታለች። ቀጥሎም በኮሜዲ ገጸ-ባሕርያት ዙሪያ በሠራችባቸው ፊልሞች እንደ ዘ ጉድ ገርል (እ.ኤ.አ. 2000)፣ ዘ ኒው ጋይ (እ.ኤ.አ. 2002)፣ ኤልፍ (እ.ኤ.አ. 2003)፣ ዘ ሂችሃይከርስ ጋይድ ቱ ዘ ጋላክሲ (እ.ኤ.አ. 2005)፣ ፌይለር ቱ ሎንች (እ.ኤ.አ. 2006)፣ የስ ማን (እ.ኤ.አ. 2008) እና (500) ዴይስ ኦፍ ሰመር (እ.ኤ.አ. 2009) ታዋቂ ሆናለች። ከእ.ኤ.አ. 2011 ጀምሮ በፎክስ በሚተላለፈው ኒው ገርል ሲትኮም ላይ ጄሲካ ዴይን ሆና ትተውናለች። በዚህም የኤሚ ሽልማት እና ሦስት የጎልደን ግሎብ ሽልማት እጩነቶችን ተቀብላለች።
ዞዊ ዴሸኔል | |
---|---|
ዞዊ ዴሸኔል በ57ኛው ዓመታዊ የሳን ፍራንሲስኮ ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል ላይ - እ.ኤ.አ. ሜይ 2014 | |
ባለቤት | ቤን ጊበርድ (ከእ.ኤ.አ. 2009 እስከ 2012) ጄከብ ፔሽኒክ (ከእ.ኤ.አ. 2015 ጀምሮ) |
ልጆች | 1 |
ሙሉ ስም | ዞዊ ክሌር ዴሸኔል |
አባት | ኬለብ ዴሸኔል |
እናት | ሜሪ ጆ ዴሸኔል |
የትውልድ ቦታ | ሎስ አንጄሌስ ካሊፎርንያ ዩ.ኤስ. |
የልደት ቀን | እ.ኤ.አ. ጃኑዌሪ 17 1980 |