ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች በኢትዮጵያ

ማውጫ

   1 ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች በኢትዮጵያ
       
       1.1 መስከረም
       1.2 ጥቅምት
       1.3 ኅዳር
       1.4 ታኅሣሥ
       1.5 ጥር        
       1.6 የካቲት       
       1.7 መጋቢት       
       1.8 ሚያዝያ        
       1.9 ግንቦት        
       1.10 ሰኔ        
       1.11 ሐምሌ        
       1.12 ነሐሴ        
       1.13 ጳጉሜ

መስከረም

መስከረም ፩ ቀን:

   ዕንቁጣጣሽ፣ ብሄራዊ ቀን  በኢትዮጵያ

መስከረም ፪ ቀን:

   ፲፭፻፴፭ ዓ/ም - አምባ ሰሜን በተባለ ሥፍራ ላይ በቡርቱጋል ሠራዊት እና በአህመድ ግራኝ መኻከል በተካሄደው ጦርነት ላይ ዶም ክርስቶፍ ዳጋማ    በጥይት ቆስሎ በግራኝ ወታደሮች ተማረከ።
   ፲፰፻፺ ዓ/ም - የዳግማዊ ምኒልክ የጦር አበጋዞች የከፋውን ንጉሥ ጋኪ ሸሮቾ በመማረክ ያንን መንግሥት ጨረሱ
   ፲፱፻፷፯ ዓ/ም -ከ ፶፰ ዓመታት በሥልጣን፣ መጀመሪያ በአልጋ ወራሽነትና የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሙሉ ሥልጣን እንደራሴነት፣ ከመጋቢት ፳፬ ቀን    
   ፲፱፻፳፪ ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ በንጉሠ ነገሥትነት ኢትዮጵያን የመሩት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በደርግ የአብዮት ሥርዓት ተሽረው ከሥልጣን ወረዱ።

መስከረም ፭ ቀን፡

   ፲፫፻፵፮ ዓ/ም - ኢትዮጵያዊው መነኩሴ አባ ኤውስጣቴዎስ በስደት በሚኖሩበት አርመን አገር ላይ ሞቱ።
   ፲፭፻፴፫ ዓ/ም -አጼ ልብነ ድንግል በነገሡ በ፴፪ ዓመታቸው ሐሙስ ዕለት ደብረ ዳሞ ላይ አረፉ። የንጉሠ ነገሥትነት ሥልጣን፣ ዘውድና ዙፋናቸው በዚሁ ዕለት ወደልጃቸው የ፲፰ ዓመቱ አጼ ገላውዴዎስ (ስመ መንግሥት፣ አፅራር ሰገድ) ተላለፈ።
   ፲፱፻፵፭ ዓ/ም - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኤርትራና ኢትዮጵያ በ«ኅብረታዊ መንግሥት» እንዲዋሃዱ አጸደቀ።
   ፳፻፫ ዓ/ም - በሁለት ትላልቅ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ድርጅቶች የመሪዎች መፈንቅል ተፈጸመ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ላለፉት ስድስት ዓመት ያገለገሉት አቶ ግርማ ዋቄ፣ ሥራቸውን ለቀቁ። አቶ ግርማን የሚተኳቸው ምክትላቸው አቶ ተወልደ ገብረማርያም ይሆናሉ ይባላል። በዚሁ ዕለት የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ላለፉት አራት ዓመታት ያገለገሉት አቶ አማረ አምሳሉም ሥራቸውን ለቀቁ።

መስከረም ፮ ቀን፡

   ፲፱፻፴፩ ዓ.ም. - የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ክቡር ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ ፤ በጣሊያን ወረራ ጊዜ ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጋር እንግሊዝ አገር በስደት ላይ እንዳሉ፣ በተወለዱ በስድሳ ዓመታቸው ዓረፉ።
   ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የቀድሞው የኢትዮጵያ መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር ፀሐፊ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተ-ወልድ ለደርግ የምርመራ ኮሚሽን ‘ዓለም በቃኝ’ እስር ቤት ሆነው ያዘጋጁትን “የታሪክ ማስተወሻ” ላኩ። በመስከረም ወር ፲፱፻፹፮ ዓ/ም በጦብያ መጽሔት ላይ የወጣው ይኼው የትሪክ ማስታወሻ ለሕይወት ታሪካቸው ዋቢ ምንጭ ሆኗል።
   ፲፱፻፸፪ ዓ/ም - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የነበረው ኢቲ-ኤጂዩ (ET-AGU) ዲ-ሲ ፫ (Douglas C-47 A -20-DK) አየር ዠበብ በደቡብ-ምዕራብ ኤርትራ፣ ከባረንቱ ማረፊያ ሊነሳ ሲያኮበኩብ በአፍንጫው ተደፍቶ ሲከሰከስ ከጥቅም ውጭ ሆኗል።
   ፳፻፫ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በአዋጅ ቁጥር 654/2001 መሠረት በየዓመቱ በመስከረም ወር በሁለተኛው ሳምንት ዕለተ ሰኞ እንዲከበር በተወሰነው ድንጋጌ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አርማ ያለበት ሰንደቅ ዓላማ ቀን።
   ፲፮፻፳፭ ዓ/ም - በዙፋን ስማቸው "መልአክ ሰገድ" የሚባሉት ዓፄ ሱስኒዩስ በጽኑ ደዌ ታመው በዕለተ ዐርብ ሞቱ፤ አዘዞ ላይ ተቀበሩ።
   ፲፱፻፵ ዓ.ም - የክቡር ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ አጽም በስደት ዘመን አርፈው ከተቀበሩበት ከእንግሊዝ አገር ወደ ውድ አገራቸው ኢትዮጵያ ተመልሶ በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተቀበረ።
   ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የሥራ ሚኒስትር ከአሜሪካ ጉዟቸው ሲመለሱ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁለት ቦይንግ ፯መቶ፳-ቢ (Boeing 720B) ጄት አውሮፕላኖች መግዣ እና ለቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ የሚውል ብድር ከ ኤክሲም ባንክ (Export Import Bank) ጋር የስምምነት ውል መፈራረማቸውን ይፋ አደርጉ።
   ፳፻፪ ዓ/ም በምዕራብ ጐጃም የአንድነት ቅርንጫፍ ቢሮ አስተባባሪዎች ላይ ድብደባ ተፈጸመ።
   ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የኢትዮጵያ የሠራተኞች ማኅበር ፕሬዚደንት፤ ምክትል ፕሬዚደንት እና ዋና ጸሐፊ አዲስ ሥልጣን በያዘው የደርግ ወታደራዊ መንግሥት ትዕዛዝ ተይዘው ታሠሩ።
   ፲፱፻፺፱ ዓ/ም የህውሐት ማእከላዊ ኮሚቴ አቶ መለስ ዜናዊ የድርጅቱ ሊቀ መንበር ሆነው እንዲያገለግሉ በድጋሚ መረጠ፡ ...

መስከረም ፲፭ ቀን፡

   ፲፱፻፱ ዓ/ም - በትልቁ የመስቀል በዓል ቀን መኳንንቱ ከነሠራዊቱ፤ ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ማቴዎስና እጨጌ ወልደ ጊዮርጊስ ከነካህናቱ በተሰበሰቡበት በ ፲ ነጥብ የተዘረዘረው የልጅ እያሱ ወንጀል ተነቦ እሳቸውን ሽረው ወይዘሮ ዘውዲቱን ንግሥት፣ ደጃዝማች ተፈሪን ራስ ብለው አልጋ ወራሽና የመንግሥቱ እንደራሴ ተደረጉ።
  ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - በፋሺስት ወረራ ጊዜ ኢትዮጵያን በመደገፍ በእንግሊዝ አገር እርዳታ በመሰብሰብ፣ የኢጣልያን ግፍ እና የምዕራባውያንን ድክመት በማጋለጥ የታገሉት ዕመት ሲልቪያ ፓንክኸርስት አረፉ። ሥርዓተ ቀብራቸው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በተገኙበት በመንግሥታዊ ሥርዓት በኢጣሊያ ጦርነት ሰማዕት ለሆኑ ጀግኖች በተዘጋጀው መካነ መቃብር፣ በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ፡፡
   ፳፻፩ ዓ/ም - በጅጅጋ ከተማ "አንድነት" በተባለ ሆቴል በተከሰተ ፍንዳታ አራት ሰዎች ሲሞቱ አስር ሰዎች ቆስለዋል።
   ፲፱፻፴፮ ዓ/ም - የሁለተኛው የዓለም ጦርነት መጀመሪያ ላይ የፋሺስት ኢጣልያ ሠራዊት አገራችንን ኢትዮጵያን ሲወር በድል አድራጊነት አዲስ አበባ የገባው ማርሻል ፒዬትሮ ባዶልዮ፤ ተሸናፊዋን አገሩን በመወከል የሽንፈቱን ስምምነት ፈረመ።

መስከረም ፳፩ ቀን፡

   ፲፬፻፵፮ ዓ/ም -ዓፄ ዘርአ ያዕቆብ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትን ግማደ መስቀሉንና ሌሎች ብዙ የቤተ ክርስቲያን ንዋያተ ቅድሳትን አምጥተው በግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም አስቀመጡ።
  ፲፭፻፺ ዓ.ም. - የንግሥ ዘመናቸውን (ከ ፲፭፻፶፯ ዓ.ም. እስከ ፲፭፻፺ ዓ.ም.) ሙሉ በቀይ ባሕር በኩል ቱርኮችን (ኦቶማን)፤ በደቡብ የኦሮሞዎችን ጥቃት በመከላከል ያሳለፉት የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ሰርጸ ድንግል በተወለዱ በ ፵፯ ዓመታቸው አረፉ።

መስከረም ፳፮ ቀን፡

  ፲፬፻፬ ዓ/ም - በ፲፫፻፸፭ ዓ/ም በኢትዮጵያ ዙፋን ላይ ተቀምጠው ለሃያ ዘጠኝ ዓመት የነገሡትና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ግማደ መስቀል ወደኢትዮጵያ ያስመጡት ዳግማዊ ዓፄ ዳዊት ፈረሳቸው ረግጧቸው ሞቱ።

መስከረም ፳፯ ቀን፡

  ፲፱፻፳፩ ዓ/ም - ልዑል ራስ ተፈሪ መኮንን በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ እጅ ዘውድ ጭነው ንጉሥ ተፈሪ ተባሉ።
  ፲፱፻ ዓ/ም - የሐረር ገዥ የነበሩት ደጃዝማች ይልማ መኮንን (የራስ መኮንን የመጀመሪያ ልጅ እና የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ታላቅ ወንድም) አርፈው ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በአባታቸው መቃብር ተቀበሩ።
 ፲፱፻፵፭ ዓ/ም - በታላቋ ብሪታኒያ የኢትዮጵያ አራተኛው ዋና መላክተኛ (Envoy Extraordinary and Minister Plenipotentiary) የነበሩት ሐኪም አዛዥ ወርቅነህ (Dr. Charles Martin) በዚህ ዕለት አረፉ።
 ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የኢትዮጵያ መንግሥት አልጋ ወራሽ አስፋ ወሰን፣ ሎንዶን በህክምና ሲረዱ ቆይተው፣ ለማገገም በዛሬው ዕለት ወደ ስዊዘርላንድ አመሩ።