አንድ ለመንገድ

ለማስተካከል
  • ከዘመናት በኋላ ወደ ትውልድ ሀገርዎ ሲሔዱ ለዘመድ ወዳጅ የሚሆን ነገር በሻንጣዎ መቀርቀብዎ አይቀሬ ነው። በትከሻዎ በሚያነግቱት ቦርሳ ደግሞ፣ ዶኩሜንቶች፣ የአድርሱልኝ ደብዳቤና መልዕክት ይይዙ ይሆናል፤ እኛስ ለማያውቅዎ ለማያውቁት ኢትዮጲያዊ ተማሪ፣ በእጅዎ መፅሐፍ ብናስጨብጥዎ?

በአመት በመቶ ሺህ የመቆጠሩ ኢትዮጲያውያን ከአለም ዙሪያ ወደ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ይገባሉ። እያንዳንዳቸው አንዳንድ መፅሐፍ ቢይዙ በዓመት በመቶ ሺህ የሚቆጠር መፅሐፍት ወደ ሀገራችን ያስገባሉ። ይህም ማለት አሁን በሀገራችን ከሚገኙት ቤተ-መፅሐፍት 3 ጊዜ የሚበልጡ ቤተ- መፅሐፍት ማለት ነው። በአሥር ዓመታት ሀገራችን በሚሊዮን የሚቆጠር መፅሐፍት ይኖራታል። ከእርስዎ የሚጠበቀውን እንንገርዎ

  • ወደ ኢትዮጵያ ሲጓዙ አንድ መፅሐፍ ይያዙ። እርስዎ በቅርብ የማይሄዱ ከሆነ ለሚሄድ ሰው አንድ መፅሐፍ ያስይዙ። ሀይስኩል፣ ኮሌጅ፣ ወይንም ዩኒቨርሲቲ የተማሩባቸውን መፅሐፍት መላክ ይችላሉ ። በካናዳ የሚኖሩ ከሆነ Good Will Store መጽሐፍት በ2 ዶላር ይሸጣሉ ከዚያ ገዝተው መላክም ይችላሉ የተቻለ መንገድ ካለም ይጠቀሙን። የእኛ ድርሻስ ምንድነው?
  • ትኬት ከሚገዙበት አንድ መጽሃፍ እንዲወስዱ መፅሐፍ ሰብስበን የአውሮፕላን ትኬት መሸጫ ቦታዎች መጽሃፍቱን እናስቀምጣለን ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የመፅሐፍ ማከማቻ ኮንቴይነር ያገኛሉ እዛ ከተው ከዘመዶችዋ ይቀላቀላሉ ።
  • አንድ ለመንገድዎ፣ አንድ ለዛ ኢትዮጲያዊ ተማሪ መፅሐፍ ይያዙ።