ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ጥቅምት 1
- ፲፱፻፶ ዓ/ም - የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ድዋይት አይዘንሃወር በዘርያነት ምክንያት በዴላዌር ምግብ ቤት መስተንግዶ የተከለከሉትን የጋና ገንዘብ ሚኒስቴር ኮምላ አግቤሊ ግብዴማን ይቅርታ ጠየቁ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የክራሩ ጌታ፤ የኮሪያው ዘማች፤ ካሳ ተሰማ በተወለደ በ፵፯ ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
- ፲፱፻፹፬ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ጉባዔ (Ethiopian Human Rights Council) በ ፴፪ መሥራች አባላት አዲስ አበባ ላይ ተመሠረተ።