ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ጥር 16
- ፲፱፻፷፬ ዓ/ም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በጃፓን ሠራዊት ውስጥ ተሰልፎ የነበረው ፶ ዓለቃ ሾዪቺ ዮኮይ ጦርነቱ ባከተመ በ ሃያ ሰባት ዓመቱ ተደብቆ በኖረበት በጉዋም ጫካ ውስጥ ተገኝቶ ወደአገሩ ሲመለስ «በሕይወቴ ስመለስ ትልቅ እፍረት እየተሰማኝ ነው።» ብሎ ተናገረ። ሾዪቺ ከተመለሰ በኋላ ለሃያ አምስት ዓመታት ኖሯል።
- ፲፱፻፶፯ ዓ/ም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የናዚዎችንና የፋሺስትን ሥርዓት በመጻረር ዝና ያተረፉት ታላቅ የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር፤ ወታደር፤ የታሪክ እና የሥነ ጽሑፍ ምሁር እንዲሁም በሥነ ጽሑፍ የኖቤል ሽልማት ተቀባይ የነበሩት ዊንስተን ቸርቺል በተወለዱ በዘጠና አንድ ዓመታቸው አረፉ ።