ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ኅዳር 5
- ፲፰፻፸፪ ዓ/ም - የዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ እና የእቴጌ ጥሩወርቅ ውቤ ልጅ፣ ልዑል ዓለማየሁ ቴዎድሮስ በመቅደላ ጦርነት ተሰደው በሚኖሩበት እንግሊዝ አገር ከ፲፩ ዓመት ቆይታ በኋላ በተወለዱ በ፲፰ ዓመታቸው ባደረባቸው የሳምባ ምች ሕመም በዚህ ዕለት አረፉ።
- ፲፰፻፹፪ ዓ.ም.- የሕንድ የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስቴር፣ ጃዋሀርላል ኔህሩ በዚህ ዕለት ተወለዱ
- ፲፱፻፲፩ ዓ.ም.- የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ሲያከትም፣ የቀድሞዋ ቼኮዝሎቫኪያ ሪፑብሊክ ሆነች።
- ፲፱፻፷፬ ዓ.ም. - በእስክንድርያ (ኮፕት) ቤተ ክርስቲያን አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ፓትርያርክ ሆነው በወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ ወንበር ተቀመጡ።