ኅዳር ፳፬

  • ፲፱፻፷፱ ዓ.ም. በጃማይካ የ’ሬጌ’ ሙዚቃ ባላባት ቦብ ማርሌይ ላይ የገደላ ሙከራ ተደረገ። በሁለት ጥይቶች ቢመታም ማርሌይ ከሁለት ቀን በኋላ መድረክ ላይ ወጣ።
  • ፲፱፻፸፬ ዓ.ም. ሕንድ አገር ውስጥ በቦፓል ከተማ ፥ የአሜሪካዩኒየን ካርባይድ ( Union Carbide) የኬሚካል ኩባንያ ውስጥ በተከሰተው አደጋ መርዛዊ ኬሚካል አየሩን በክሎት ሦስት ሺህ ስምንት መቶ ሰዎች ሲሞቱ እስከ ስድስት መቶ ሺህ ሰዎች በአደጋው ምክንያት ጤናቸው እንደተበላሸ ይገመታል።