• ፲፰፻፷ ዓ/ም - የስቅለት ዓርብ ዕለት በ ሎርድ ናፒዬር የሚመራው የእንግሊዝ ሠራዊት እና የዓፄ ቴዎድሮስ ሠራዊት በመቅደላ ተራራ ሥር በምትገኘው እሮጌ በምትባል ሥፍራ ላይ ጦርነት ገጥመው የዓፄ ቴዎድሮስ የጦር አዛዥ የነበሩት ፊታውራሪ ገብርዬ ሞቱ።
  • ፲፱፻፷ ዓ/ም - የአሜሪካ ፕሬዚደንት ሊንደን ጆንሰን ጥቁር አሜሪካውያን ላይ የነበረውን የመኖሪያ ቤት ጭቆና ሕገ-ወጥ የሚያደርግ የሰብዓዊ መብት ሕግ አጽድቀው ፈረሙ።
  • ፲፱፻፸፩ ዓ/ም - በታንዛኒያ መንግሥት ድጋፍ የተንቀሳቀሱ የኡጋንዳ ታጋዮች የአገሪቱን በትረ-ሥልጣን ከአምባ ገነኑ ኢዲ አሚን እጅ ፈልቅቀው ጨበጡ። አሚን ሸሽቶ ወደሊቢያ ኮበለለ።