ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/መጋቢት 21
- ፲፱፻፬ ዓ/ም የሞሮኮ መሪ ሱልጣን አብደልሃፊድ አገሪቱን በፈረንሳይ ጥላ ሥር ያደረገውን ስምምነት ፈረሙ። ሞሮኮ ከ ፵፬ ዓመት በኋላ መጋቢት ፳፱ ቀን ፲፱፻፵፰ ዓ/ም በ ግርማዊ ዳግማዊ ሀሰን መሪነት ነጻነቷን ተቀዳጀች።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም የታኅሣሥ ግርግር በመባል በታሪክ መዝገብ የሚታወቀውን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ በግንባር ቀደምነት ያካሄዱት የክብር ዘበኛ አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል መንግሥቱ ነዋይ በተቀበሉት ፍርድ መሠረት በስቅላት ተቀጡ።