ሐምሌ ፫
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - ከአደን የብሪታኒያ አየር ኃይል ሠፈር የተላከ ‘አየር ወለድ የባሕር አደጋ ተከላካይ’ ቡድን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ የአየር ባለሥልጣናት ጋር የሁለት ቀን ውይይት ለማድረግ አዲስ አበባ ገባ።
- ፲፱፻፸ ዓ/ም - በሞሪታንያ በተካሄደ መፈንቅለ መንግሥት ፕሬዚዳንቱ ሞክታር ኡልድ ዳዳ ከሥልጣን ወረዱ።
- ፲፱፻፺፪ ዓ/ም - በደቡባዊ ናይጄሪያ ውስጥ ከሚያንጠባጥብ የነዳጅ ቧንቧ ነዳጅ ሲቀዱ በፍንዳታ ሁለት መቶ ሃምሣ የመንደር ነዋሪዎች ሕይወታቸውን መስዋዕት አድርገዋል።