ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ሐምሌ 19
ይህ ቀን ልዩ ቀን ነው!!! የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታዮች ትልቅ ትኩረት የሚሰጡት ቀን ሲሆን፤ በዚህ ዕለት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱን ቅዱስ ኢየሉጣን ያዳነበት ቀን ነው። ይህ በዓል በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት ተከብሮ ይውላል። በተለይ ደግሞ በመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን በልዩ ሁኔታ ይከበራል።
- ፲፱፻፵፭ ዓ/ም በኩባዊው ፊደል ካስትሮ መሪነት ሞንካዳ በሚባል የሠራዊት ሠፈር ላይ የተሞከረው ያልተሳካ ጥቃት በአገሪቱ ፕረዚደንት ፉልጀንሲዮ ባቲስታ ላይ የተከሰተውን የኩባ አብዮት የመጀመሪያ ድርጊት ሆነ።
- ፲፱፻፵፰ ዓ/ም የግብጽ መሪ ጋማል አብደል ናሰር የዓለም ባንክ ለአስዋን ግድብ ሥራ ብድር/ዕርዳታ ሲከለክላቸው በምላሽ የሱዌዝ ን ቦይ የኣገር ንብረት ኣደረጉት።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት የከተማ ቦታን በግል መያዝ ክልክል መሆኑንና የከተማ መሬት ሲወረስም ምንም ካሣ እንደማይከፈል የሚያበሥረውን «የከተማ ቦታና ቤት አዋጅ» አወጣ።