ወደ ሮማውያን በአዲስ ኪዳን የመጀመሪያው መልዕክት ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንጦስ እያለ በ፶ ዎቹ ዓ.ም. የጻፈው መልዕክት ነው ። ይህ ምዕራፍ ፲፬ ሲሆን በ፳፫ ንዑስ ክፍሎች ይከፈላል ። ጳውሎስ በዚህ መልዕክቱ "አትፍረድ ይፈረድብሃል፡" በሚለው የእግዚአብሔር ትዛዝ ላይ የሚያተኩር ነው ።

ወደ ሮማውያን ፲፬
በ፫ኛው ክፍለ ዘመን የተጻፈ ወደ ሮማውያን ፲፬ - ወደ ሮማውያን ፲፮ በኮዴክስ ካሮሊነስ
አጭር መግለጫ
ፀሐፊ ጳውሎስ
የመጽሐፍ ዐርስት ወደ ሮማውያን
የሚገኘው በአዲስ ኪዳን ፮ኛው መጽሐፍ
መደብ የጳውሎስ መልዕክት


ቅዱስ ጳውሎስ ለሮማውያን መልዕክቱን የጻፈበት ምክኒያት አይሁዳውያንና ሮማውያን በሰላም አንድላይ በሮም ለብዙ ዘመን ሲኖሩ ቆይተው ክርስትና በተመሠረተበት ወቅት ፣ አይሁዳውያን ክርስቶስ እኛን ነው የመረጠን ለመንግሥቱ እናንተን አይደለም... ሲሊ ሮማውያን ደግሞ እናንተ ሰቀላችሁት እንጂ ምን አረጋቹህለት... እየተባባሉ እርስበርሳቸው ጥል ስለፈጠሩ እነሱን ለማስታረቅ ጻፈው ።

የጳውሎስ መልዕክት ወደ ሮማውያን ምዕራፍ ፲፬

ቁጥር ፩ - ፲ ለማስተካከል

1፤በእምነት፡የደከመውንም፡ተቀበሉት፥በዐሳቡም፡ላይ፡አትፍረዱ። 2፤ዅሉን፡ይበላ፡ዘንድ፡እንደ፡ተፈቀደለት፡የሚያምን፡አለ፥ደካማው፡ግን፡አትክልት፡ይበላል። 3፤የሚበላ፡የማይበላውን፡አይናቀው፡የማይበላውም፡በሚበላው፡አይፍረድ፥እግዚአብሔር፡ተቀብሎታልና። 4፤አንተ፡በሌላው፡ሎሌ፡የምትፈርድ፡ማን፡ነኽ፧ርሱ፡ቢቆም፡ወይም፡ቢወድቅ፡ለገዛ፡ጌታው፡ነው፤ነገር፡ ግን፥እግዚአብሔር፡ሊያቆመው፡ይችላልና፥ይቆማል። 5፤ይህ፡ሰው፡አንድ፡ቀን፡ከሌላ፡ቀን፡እንዲሻል፡ያስባል፥ያ፡ግን፡ቀን፡ዅሉ፡አንድ፡እንደ፡ኾነ፡ ያስባል፤እያንዳንዱ፡በገዛ፡አእምሮው፡አጥብቆ፡ይረዳ። 6፤ቀንን፡የሚያከብር፡ለጌታ፡ብሎ፡ያከብራል፤የሚበላም፡እግዚአብሔርን፡ያመሰግናልና፥ለጌታ፡ብሎ፡ ይበላል፤የማይበላም፡ለጌታ፡ብሎ፡አይበላም፥እግዚአብሔርንም፡ያመሰግናል። 7፤ከእኛ፡አንድ፡ስንኳ፡ለራሱ፡የሚኖር፡የለምና፥ለራሱም፡የሚሞት፡የለም፤ 8፤በሕይወት፡ኾነን፡ብንኖር፡ለጌታ፡እንኖራለንና፥ብንሞትም፡ለጌታ፡እንሞታለን።እንግዲህ፡በሕይወት፡ኾነን፡ ብንኖር፡ወይም፡ብንሞት፡የጌታ፡ነን። 9፤ስለዚህ፡ነገር፥ሙታንንም፡ሕያዋንንም፡ይገዛ፡ዘንድ፥ክርስቶስ፡ሞቷልና፥ሕያውም፡ኾኗልና። 10፤አንተም፡በወንድምኽ፡ላይ፡ስለ፡ምን፡ትፈርዳለኽ፧ወይስ፡አንተ፡ደግሞ፡ወንድምኽን፡ስለ፡ምን፡ ትንቃለኽ፧ዅላችን፡በክርስቶስ፡ፍርድ፡ወንበር፡ፊት፡እንቆማለንና፦

ቁጥር ፲፩ - ፳ ለማስተካከል

11፤እኔ፡ሕያው፡ነኝ፥ይላል፡ጌታ፥ጕልበት፡ዅሉ፡ለእኔ፡ይንበረከካል፡ምላስም፡ዅሉ፡እግዚአብሔርን፡ ያመሰግናል፡ተብሎ፡ተጽፏልና። 12፤እንግዲያስ፡እያንዳንዳችን፡ስለ፡ራሳችን፡ለእግዚአብሔር፡መልስ፡እንሰጣለን። 13፤እንግዲህ፡ከዛሬ፡ዠምሮ፡ርስ፡በርሳችን፡አንፈራረድ፤ይልቁን፡ግን፡ለወንድም፡እንቅፋትን፡ወይም፡ ማሰናከያን፡ማንም፡እንዳያኖርበት፡ይህን፡ቍረጡ። 14፤በራሱ፡ርኩስ፡የኾነ፡ነገር፡እንደ፡ሌለ፡በጌታ፡በኢየሱስ፡ኾኜ፡ዐውቄያለኹ፡ተረድቻለኹም፤ነገር፡ ግን፥ምንም፡ርኩስ፡እንዲኾን፡ለሚቈጥር፡ለርሱ፡ርኩስ፡ነው። 15፤ወንድምኽንም፡በመብል፡ምክንያት፡የምታሳዝን፡ከኾንኽ፥እንግዲህ፡በፍቅር፡አልተመላለስኽም።ክርስቶስ፡ ስለ፡ርሱ፡የሞተለትን፡ርሱን፡በመብልኽ፡አታጥፋው። 16፤እንግዲህ፡ለእናንተ፡ያለው፡መልካም፡ነገር፡አይሰደብ፤ 17፤የእግዚአብሔር፡መንግሥት፡ጽድቅና፡ሰላም፡በመንፈስ፡ቅዱስም፡የኾነ፡ደስታ፡ናት፡እንጂ፡መብልና፡ መጠጥ፡አይደለችምና። 18፤እንደዚህ፡አድርጎ፡ለክርስቶስ፡የሚገዛ፡እግዚአብሔርን፡ደስ፡ያሠኛልና፥በሰውም፡ዘንድ፡የተመሰገነ፡ነው። 19፤እንግዲያስ፡ሰላም፡የሚቆምበትን፡ርስ፡በርሳችንም፡የምንታነጽበትን፡እንከተል። 20፤በመብል፡ምክንያት፡የእግዚአብሔርን፡ሥራ፡አታፍርስ።ዅሉ፡ንጹሕ፡ነው፥በመጠራጠር፡የተበላ፡እንደ፡ ኾነ፡ግን፡ለዚያ፡ሰው፡ክፉ፡ነው።

ቁጥር ፳ - ፳፫ ለማስተካከል

21፤ሥጋን፡አለመብላት፡ወይንንም፡አለመጠጣት፡ወንድምኽም፡የሚሰናከልበትን፡አለማድረግ፡መልካም፡ነው። 22፤ለአንተ፡ያለኽ፡እምነት፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ለራስኽ፡ይኹንልኽ።ፈትኖ፡መልካም፡እንዲኾን፡ በሚቈጥረው፡ነገር፡በራሱ፡ላይ፡የማይፈርድ፡ብፁዕ፡ነው። 23፤የሚጠራጠረው፡ግን፡ቢበላ፡በእምነት፡ስላልኾነ፡ተኰንኗል፤በእምነትም፡ያልኾነ፡ዅሉ፡ኀጢአት፡ነው።