ወደ ሮማውያን በአዲስ ኪዳን የመጀመሪያው መልዕክት ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንጦስ እያለ በ፶ ዎቹ ዓ.ም. የጻፈው መልዕክት ነው ። ይህ ምዕራፍ ፲፩ ሲሆን በ፴፫ ንዑስ ክፍሎች ይከፈላል ። ጳውሎስ በዚህ መልዕክቱ ስለእግዚአብሄር ልዩ ልዩ ስጦታዎች ትምህርት ይፈጽማል ። መዳንም ላመኑት እንጂ ላላመኑት እንደማይሆን ያረጋግጣል ።

ወደ ሮማውያን ፲፩
በ፫ኛው ክፍለ ዘመን የተጻፈ ወደ ሮማውያን ፲፩ ቁ. ፴፫ - ወደ ሮማውያን ፲፪ ቁ.፭ በኮዴክስ ካሮሊነስ
አጭር መግለጫ
ፀሐፊ ጳውሎስ
የመጽሐፍ ዐርስት ወደ ሮማውያን
የሚገኘው በአዲስ ኪዳን ፮ኛው መጽሐፍ
መደብ የጳውሎስ መልዕክት

ቅዱስ ጳውሎስ ለሮማውያን መልዕክቱን የጻፈበት ምክኒያት አይሁዳውያንና ሮማውያን በሰላም አንድላይ በሮም ለብዙ ዘመን ሲኖሩ ቆይተው ክርስትና በተመሠረተበት ወቅት ፣ አይሁዳውያን ክርስቶስ እኛን ነው የመረጠን ለመንግሥቱ እናንተን አይደለም... ሲሊ ሮማውያን ደግሞ እናንተ ሰቀላችሁት እንጂ ምን አረጋቹህለት... እየተባባሉ እርስበርሳቸው ጥል ስለፈጠሩ እነሱን ለማስታረቅ ጻፈው ።

የጳውሎስ መልዕክት ወደ ሮማውያን ምዕራፍ ፲፩

ጠቃሚ መልዕክቶች ለማስተካከል

  • ቁጥር ፡ ፮
  • ቁጥር ፡ ፴፬
  • ቁጥር ፡ ፴፮

ቁጥር ፩ - ፲ ለማስተካከል

 1፤እንግዲህ፦እግዚአብሔር፡ሕዝቡን፡ጣላቸውን፧እላለኹ።አይደለም፡እኔ፡ደግሞ፡እስራኤላዊና፡ከአብርሃም፡ ዘር፡ከብንያምም፡ወገን፡ነኝና። 2፤እግዚአብሔር፡አስቀድሞ፡ያወቃቸውን፡ሕዝብ፡አልጣላቸውም።መጽሐፍ፡ስለ፡ኤልያስ፡በተጻፈው፡ የሚለውን፥በእግዚአብሔር፡ፊት፡እስራኤልን፡እንዴት፡እንደሚከስ፥አታውቁምን፧ 3፤ጌታ፡ሆይ፥ነቢያትኽን፡ገደሉ፥መሠዊያዎችኽንም፡አፈረሱ፥እኔም፡ብቻዬን፡ቀረኹ፥ነፍሴንም፡ይሿታል። 4፤ነገር፡ግን፥አምላካዊ፡መልስ፡ምን፡አለው፧ለበዓል፡ያልሰገዱትን፡ሰባት፡ሺሕ፡ሰዎች፡ለእኔ፡ አስቀርቻለኹ። 5፤እንደዚሁም፡በአኹን፡ዘመን፡ደግሞ፡በጸጋ፡የተመረጡ፡ቅሬታዎች፡አሉ። 6፤በጸጋ፡ከኾነ፡ግን፡ከሥራ፡መኾኑ፡ቀርቷል፤ጸጋ፡ያለዚያ፡ጸጋ፡መኾኑ፡ቀርቷል። 7፤እንግዲህ፡ምንድር፡ነው፧እስራኤል፡የሚፈልጉትን፡አላገኙትም፤የተመረጡት፡ግን፡አገኙት፤ 8፤ሌላዎቹም፡ደነዘዙ፤እንዲሁም፦ዐይኖቻቸው፡እንዳያዩ፡ዦሮዎቻቸውም፡እንዳይሰሙ፡እግዚአብሔር፡ የእንቅልፍ፡መንፈስን፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ሰጣቸው፡ተብሎ፡ተጽፏል።ዳዊትም፦ 9፤ማእዳቸው፡ወጥመድና፡አሽክላ፡ማሰናከያም፡ፍዳም፡ይኹንባቸው፤ 10፤ዐይኖቻቸው፡እንዳያዩ፡ይጨልሙ፥ዠርባቸውንም፡ዘወትር፡አጕብጥ፡ብሏል።

ቁጥር ፲፩ - ፳ ለማስተካከል

11፤እንግዲህ፦የተሰናከሉ፡እስኪወድቁ፡ድረስ፡ነውን፧እላለኹ።አይደለም፤ነገር፡ግን፥እነርሱን፡ያስቀናቸው፡ ዘንድ፡በእነርሱ፡በደል፡መዳን፡ለአሕዛብ፡ኾነ። 12፤ዳሩ፡ግን፡በደላቸው፡ለዓለም፡ባለጠግነት፡መሸነፋቸውም፡ለአሕዛብ፡ባለጠግነት፡ከኾነ፥ይልቁንስ፡ መሙላታቸው፡እንዴት፡ይኾን፧ 13-14፤ለእናንተም፡ለአሕዛብ፡እናገራለኹ።እኔ፡የአሕዛብ፡ሐዋርያ፡በኾንኹ፡መጠን፡ሥጋዬ፡የኾኑትን፡ አስቀንቼ፡ምናልባት፡ከነርሱ፡አንዳንዱን፡አድን፡እንደ፡ኾነ፡አገልግሎቴን፡አከብራለኹ። 15፤የእነርሱ፡መጣል፡ለዓለም፡መታረቅ፡ከኾነ፡ከሙታን፡ከሚመጣ፡ሕይወት፡በቀር፡መመለሳቸው፡ምን፡ ይኾን፧ 16፤በኵራቱም፡ቅዱስ፡ከኾነ፡ቡሖው፡ደግሞ፡ቅዱስ፡ነው፤ሥሩም፡ቅዱስ፡ከኾነ፡ቅርንጫፎቹ፡ደግሞ፡ ቅዱሳን፡ናቸው። 17፤ነገር፡ግን፥ከቅርንጫፎች፡አንዳንዱ፡ቢሰበሩ፡አንተም፡የበረሓ፡ወይራ፡የኾንኽ፡በመካከላቸው፡ገብተኽ፡ ከነርሱ፡ጋራ፡የወይራ፡ዘይት፡ከሚወጣው፡ሥር፡ተካፋይ፡ከኾንኽ፥በቅርንጫፎች፡ላይ፡አትመካ፤ 18፤ብትመካባቸው፡ግን፡ሥሩ፡አንተን፡ይሸከምኻል፡እንጂ፡ሥሩን፡የምትሸከም፡አንተ፡አይደለኽም። 19፤እንግዲህ፦እኔ፡እንድገባ፡ቅርንጫፎች፡ተሰበሩ፡ትል፡ይኾናል። 20፤መልካም፤እነርሱ፡ካለማመን፡የተነሣ፡ተሰበሩ፥አንተም፡ከእምነት፡የተነሣ፡ቆመኻል።ፍራ፡እንጂ፡ የትዕቢትን፡ነገር፡አታስብ።

ቁጥር ፳፩ - ፴ ለማስተካከል

21፤እግዚአብሔር፡እንደ፡ተፈጠሩት፡ለነበሩት፡ቅርንጫፎች፡የራራላቸው፡ካልኾነ፡ለአንተ፡ደግሞ፡ አይራራልኽምና። 22፤እንግዲህ፡የእግዚአብሔርን፡ቸርነትና፡ጭከና፡ተመልከት፤ጭከናው፡በወደቁት፡ላይ፡ነው፥በቸርነቱ፡ግን፡ ጸንተኽ፡ብትኖር፡የእግዚአብሔር፡ቸርነት፡ባንተ፡ላይ፡ነው፤ያለዚያ፡አንተ፡ደግሞ፡ትቈረጣለኽ። 23፤እነዚያም፡ደግሞ፡ባለማመናቸው፡ጸንተው፡ባይኖሩ፥በዛፉ፡ውስጥ፡ይገባሉ፤እግዚአብሔር፡መልሶ፡ሊያገባቸው፡ይችላልና። 24፤አንተ፡በፍጥረቱ፡የበረሓ፡ከነበረ፡ወይራ፡ተቈርጠኽ፡እንደ፡ፍጥረትኽ፡ሳትኾን፡በመልካም፡ወይራ፡ ከገባኽ፥ይልቁንስ፡እነዚያ፡በፍጥረታቸው፡ያሉት፡ቅርንጫፎች፡በራሳቸው፡ወይራ፡እንዴት፡አይገቡም፧ 25፤ወንድሞች፡ሆይ፥ልባሞች፡የኾናችኹ፡እንዳይመስላችኹ፡ይህን፡ምስጢር፡ታውቁ፡ዘንድ፡ እወዳለኹ፤የአሕዛብ፡ሙላት፡እስኪገባ፡ድረስ፡ድንዛዜ፡በእስራኤል፡በአንዳንድ፡በኩል፡ኾነባቸው፤ 26፤እንደዚሁም፡እስራኤል፡ዅሉ፡ይድናል፤እንዲህ፡ተብሎ፡እንደ፡ተጻፈ። መድኀኒት፡ከጽዮን፡ይወጣል፡ ከያዕቆብም፡ኀጢአተኛነትን፡ያስወግዳል። 27፤ኀጢአታቸውንም፡ስወስድላቸው፡ከነርሱ፡ጋራ፡የምገባው፡ኪዳን፡ይህ፡ነው። 28፤በወንጌልስ፡በኩል፡ስለ፡እናንተ፡ጠላቶች፡ናቸው፥በምርጫ፡በኩል፡ግን፡ስለ፡አባቶች፡ተወዳጆች፡ ናቸው፤ 29፤እግዚአብሔር፡በጸጋው፡ስጦታና፡በመጥራቱ፡አይጸጸትምና። 30፤እናንተም፡ቀድሞ፡ለእግዚአብሔር፡እንዳልታዘዛችኹ፥አኹን፡ግን፡ካለመታዘዛቸው፡የተነሣ፡ምሕረት፡እንዳገኛችኹ፥

ቁጥር ፴፩ - ፴፮ ለማስተካከል

31፤እንዲሁ፡በተማራችኹበት፡ምሕረት፡እነርሱ፡ደግሞ፡ምሕረትን፡ያገኙ፡ዘንድ፡እነዚህ፡ደግሞ፡አኹን፡ አልታዘዙም። 32፤እግዚአብሔር፡ዅሉን፡ይምር፡ዘንድ፡ዅሉን፡ባለመታዘዝ፡ዘግቶታልና። 33፤የእግዚአብሔር፡ባለጠግነትና፡ጥበብ፡ዕውቀቱም፡እንዴት፡ጥልቅ፡ነው፤ፍርዱ፡እንዴት፡የማይመረመር፡ ነው፥ለመንገዱም፡ፍለጋ፡የለውም። 34፤የጌታን፡ልብ፡ያወቀው፡ማን፡ነው፧ 35፤ወይስ፡አማካሪው፡ማን፡ነበር፧ወይስ፡ብድራቱን፡ይመልስ፡ዘንድ፡ለርሱ፡አስቀድሞ፡የሰጠው፡ማን፡ነው፧ 36፤ዅሉ፡ከርሱና፡በርሱ፡ለርሱም፡ነውና፤ለርሱ፡ለዘለዓለም፡ክብር፡ይኹን፤አሜን።

 
በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ Bible የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።