ወደ ሮማውያን ፲
ወደ ሮማውያን በአዲስ ኪዳን የመጀመሪያው መልዕክት ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንጦስ እያለ በ፶ ዎቹ ዓ.ም. የጻፈው መልዕክት ነው ። ይህ ምዕራፍ ፲ ሲሆን በ፳፩ ንዑስ ክፍሎች ይከፈላል ። ጳውሎስ በዚህ መልዕክቱ መዳን በእስራኤላዊነት እንዳልሆነ ያስተምራል ። አሁንም እግዚአብሔር የመዳን ስጦታውን ለተከታዮቹ እንዲሰጣቸው ይጸልያል ።
ወደ ሮማውያን ፲ | |
---|---|
አጭር መግለጫ | |
ፀሐፊ | ጳውሎስ |
የመጽሐፍ ዐርስት | ወደ ሮማውያን |
የሚገኘው | በአዲስ ኪዳን ፮ኛው መጽሐፍ |
መደብ | የጳውሎስ መልዕክት |
ቅዱስ ጳውሎስ ለሮማውያን መልዕክቱን የጻፈበት ምክኒያት አይሁዳውያንና ሮማውያን በሰላም አንድላይ በሮም ለብዙ ዘመን ሲኖሩ ቆይተው ክርስትና በተመሠረተበት ወቅት ፣ አይሁዳውያን ክርስቶስ እኛን ነው የመረጠን ለመንግሥቱ እናንተን አይደለም... ሲሊ ሮማውያን ደግሞ እናንተ ሰቀላችሁት እንጂ ምን አረጋቹህለት... እየተባባሉ እርስበርሳቸው ጥል ስለፈጠሩ እነሱን ለማስታረቅ ጻፈው ።
የጳውሎስ መልዕክት ወደ ሮማውያን ምዕራፍ ፲
ቁጥር ፩ - ፲
ለማስተካከል1፤ወንድሞች፡ሆይ፥የልቤ፡በጎ፡ፈቃድና፡ስለ፡እስራኤል፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ልመናዬ፡እንዲድኑ፡ነው። 2፤በዕውቀት፡አይቅኑ፡እንጂ፡ለእግዚአብሔር፡እንዲቀኑ፡እመሰክርላቸዋለኹና። 3፤የእግዚአብሔርን፡ጽድቅ፡ሳያውቁ፡የራሳቸውንም፡ጽድቅ፡ሊያቆሙ፡ሲፈልጉ፥ለእግዚአብሔር፡ጽድቅ፡ አልተገዙም። 4፤የሚያምኑ፡ዅሉ፡ይጸድቁ፡ዘንድ፡ክርስቶስ፡የሕግ፡ፍጻሜ፡ነውና። 5፤ሙሴ፡ከሕግ፡የኾነውን፡ጽድቅ፡የሚያደርገው፡ሰው፡በርሱ፡በሕይወት፡እንዲኖር፡ጽፏልና። 6፤ከእምነት፡የኾነ፡ጽድቅ፡ግን፡እንዲህ፡ይላል፦በልብኽ፦ማን፡ወደ፡ሰማይ፡ይወጣል፧አትበል፤ይህ፡ ክርስቶስን፡ለማውረድ፡ነው፤ 7፤ወይም፦በልብኽ፦ወደ፡ጥልቁ፡ማን፡ይወርዳል፧አትበል፤ይህ፡ክርስቶስን፡ከሙታን፡ለማውጣት፡ነው። 8፤ነገር፡ግን፥ምን፡ይላል፧በአፍኽ፡በልብኽም፡ኾኖ፡ቃሉ፡ቀርቦልኻል፤ይህም፡የምንሰብከው፡የእምነት፡ቃል፡ነው። 9፤ኢየሱስ፡ጌታ፡እንደ፡ኾነ፡በአፍኽ፡ብትመሰክር፡እግዚአብሔርም፡ከሙታን፡እንዳስነሣው፡በልብኽ፡ ብታምን፡ትድናለኽና፤ 10፤ሰው፡በልቡ፡አምኖ፡ይጸድቃልና፥በአፉም፡መስክሮ፡ይድናልና።
ቁጥር ፲፩ - ፳፩
ለማስተካከል11፤መጽሐፍ፦በርሱ፡የሚያምን፡ዅሉ፡አያፍርም፡ይላልና። 12፤በአይሁዳዊና፡በግሪክ፡ሰው፡መካከል፡ልዩነት፡የለምና፤አንዱ፡ጌታ፡የዅሉ፡ጌታ፡ነውና፥ለሚጠሩትም፡ ዅሉ፡ባለጠጋ፡ነው፤ 13፤የጌታን፡ስም፡የሚጠራ፡ዅሉ፡ይድናልና። 14፤እንግዲህ፡ያላመኑበትን፡እንዴት፡አድርገው፡ይጠሩታል፧ባልሰሙትስ፡እንዴት፡ያምናሉ፧ያለሰባኪስ፡እንዴት፡ይሰማሉ፧ 15፤መልካሙን፡የምሥራች፡የሚያወሩ፡እግሮቻቸው፡እንዴት፡ያማሩ፡ናቸው፡ተብሎ፡እንደ፡ተጻፈ፡ ካልተላኩ፡እንዴት፡ይሰብካሉ፧ 16፤ነገር፡ግን፥ዅሉ፡ለምሥራቹ፡ቃል፡አልታዘዙም።ኢሳይያስ፦ጌታ፡ሆይ፥ምስክርነታችንን፡ማን፡ አመነ፧ብሏልና። 17፤እንግዲያስ፡እምነት፡ከመስማት፡ነው፥መስማትም፡በእግዚአብሔር፡ቃል፡ነው። 18፤ዳሩ፡ግን፦ባይሰሙ፡ነው፡ወይ፧እላለኹ።በእውነት፦ድምፃቸው፡በምድር፡ዅሉ፡ላይ፡ቃላቸውም፡እስከዓለም፡ዳርቻ፡ወጣ። 19፤ነገር፡ግን፦እስራኤል፡ባያውቁ፡ነው፡ወይ፧እላለኹ።ሙሴ፡አስቀድሞ፦እኔ፡ሕዝብ፡በማይኾነው፡ አስቀናችዃለኹ፡በማያስተውልም፡ሕዝብ፡አስቈጣችዃለኹ፡ብሏል። 20፤ኢሳይያስም፡ደፍሮ፦ላልፈለጉኝ፡ተገኘኹ፥ላልጠየቁኝም፡ተገለጥኹ፡አለ። 21፤ስለ፡እስራኤል፡ግን፦ቀኑን፡ዅሉ፡ወደማይታዘዝና፡ወደሚቃወም፡ሕዝብ፡እጆቼን፡ዘረጋኹ፡ይላል።
ጠቃሚ መልዕክቶች
ለማስተካከል- ቁጥር ፪
- ቁጥር ፭
- ቁጥር ፰
- ቁጥር ፲፬ - ፳፩