ዎለድ

ለገንዘብ አጠቃቀም የተከፈለ ድምር
(ከወለድ የተዛወረ)

ዎለድ ማለት አንድ ሰው ከተበደረው ዋና ዕዳ በተጨማሪ በየጊዜው የሚከፍለው ገንዘብ ነው። ተበዳሪ ይህን ገንዘብ ለምን ለአበዳሪ ይከፍላል ቢባል ምክንያቱ አበዳሪው ገንዘቡን በሌላ ተግባር ላይ ከማዋል ይልቅ ለተባድሪ ስለሰጠ፣ ስለዚያ ውለታ ነው ተብሎ ሊታሰብ ይቻላል።

ሁለት አይነት ዎለድ አለ። አንደኛው ቀጥተኛ ዎለድ ሲባል ሁለተኛው ተደራራቢ ዎለድ ይባላል።

ቀጥተኛ ዎለድ ከዋናው ዕዳ አንጻር ሁልጊዜ እኩል በሆነ ውድር የሚገኝ ዎለድ ነው። በምሳሌ ለማየት ያክል፦ አለሚቱ ከባንክ 1000 ብር በቀጥተኛ ዎለድ ብትበደር እና የዎለዱ ውድር በዓመት 10% ቢሆን፣ እንግዲህ የዎለድ እዳዋ በየዓመቱ 100ብር ይሆናል ማለት ነው። ስለዚህም በመጀመሪያው ዓመት መጨረሻ ሙሉው እዳዋ 1100 ብር፣ በሁለተኛው ዓመት መጨረሻ 1200 ብር ......ወዘተ እያለ ይሄድና በመቶኛው ዓመት መጨረሻ እዳዋ 2000 ብር ይሆናል። በዚህ አይነት የዎለድ ስርአት አጠቃላዩ እዳ ከዋናው እዳ እጥፍ ለመሆን አንድ መቶ አመት ይወስድበታል ማለት ነው።

ሌላኛው ዓይነት ዎለድ "ተደራራቢ ዎለድ ነው። በብዙ አበዳሪዎች ዘንድ ተጠቃሚነት ያለውም ይህ ዓይነቱ የዎለድ ስርዓት ነው።

ተደራራቢ ዎለድ እሚባለው ከዋናው ብድር መጠን ላይ በወለድ የተጠራቀመ እዳ ተደርቦበት የሚሰላ ዎለድ ነው። ለምሳሌ፦ አለሚቱ ከባንክ 1000 ብር በተደራራቢ ዎለድ ብትበደር እና የዎለዱ ውድር በዓመት 10% ቢሆን፣ እንግዲህ አጠቃላይ እዳዋ በአመቱ መጨረሻ 1100 ብር ይሆናል ምክንያቱም የአንድ ሺህ አንድ ፐርሰንት መቶ ስለሆነ። ይሁንና የሚቀጥለው አመት መጨረሻ እዳዋ ሲሰላ፣ ከዋናው እዳ፣ ከአንድ ሺው ብር ብቻ ሳይሆን ተደራቢው መቶ ብር ታክሎበት ከአንድ ሺህ አንድ መቶው ላይ ነው። ስለዚህ የወለድ እዳዋ መቶ አስር ብር ነው። አጠቃላይ እዳዋ 1210 ብር ይሆናል። በሶስተኛው ዓመት 1331 ብር.....ወዘተ ይልና....በመቶኛው ዓመት አጠቃላይ እዳዋ $13,780,612.34 (አስራ ሶስት ሚሊዮን ብር በላይ) ይደርሳል ማለት ነው። ይህ እንግዲህ ተደራራቢ ወለድ ከቀጥተኛ ዎለድ የቱን ያክል በፍጥነት እንደሚያድግ ያሳያል።

የተደራራቢ ዎለድ አጠቃላይ ዕዳ በሂሳብ ቋንቋ በቀላሉ ሊሰላ ይችላል። ለዚህ ሲባል የተሰራ ቀመር አለ። ይሄውም፦

መጪ አጠቃላይ ዕዳ = ዋናው ዕዳ *(1+ ውድር)ጊዜ

ለምሳሌ የአለሚቱን የመቶ አመት ዕዳ ለማስላት፣ ዋናው ዕዳን በ አንድ ሺህ እንተካለን፣ ውድሩ 10% ስለሆነ በ 0.1 ይተካል፣ ጊዜው ደግሞ መቶ አመት ስለሆነ በ 100 ይተካል። ስለሆነም፣ መጪው አጠቃላይ እዳ = 1000*(1+0.1)100 ይሆንና በካልኩሌተር ሲሰላ $13,780,612.34 ይገኛል ማለት ነው።