ኮብጣኽ ኮዕል ብሬግ
ኮብጣክ ኮኤል ብሬግ በአይርላንድ አፈ ታሪክ ከ364 እስከ 314 ዓክልበ. ድረስ የአየርላንድ ከፍተኛ ነጉሥ ነበር።
የአይርላንድ ታሪኮች እንዳሉት የኮብጣኽ ዘመን ለ50 ዓመታት ቆየ። በሌቦር ጋባላ ኤረን አቆጣጠር ዘንድ፣ በግብጽ ፈርዖን በጥሊሞስ ፊላዴልፎስ ዘመን (289-254 ዓክልበ.) ገዛ፤ በሌላ ቦታ ግን ኮብጣኽ የሞተበት በልደት በዓል 307 አመት ከክርስቶስ ልደት በፊት (1 እ.ኤ.አ. ወይም ታህሳስ 7 ዓክልበ. እንደ ተቆጠረ) ይለናል። ይህም የድሮ መቆጠሪያ የላውድ አቆጣጠሮች (1014 ዓም ተቀነባብሮ) ይመስላል። በኋላ የነገሠው የሩድራይጌ ማክ ሲጥሪጊ ዘመን 70 አመታት ሳይሆን 30 ዓመት ብቻ ከሆነ (111-81 ዓክልበ.) ድምሩ ልክ ይሆናል። በ17ኛው ክፍለ ዘመን የታተመው የአራት ሊቃውንት ዜና መዋዕል እንደ ቆጠረው ግን፣ የኮብጣኽ ዘመን ከ600 እስከ 550 ድረስ ነበረ።