ክዋቻ

የዛምቢያ ብሄራዊ መገበያያ ገንዘብ

ክዋቻዛምቢያ ሕጋዊ ገንዘብ ስም ነው። አንድ ክዋቻ መቶ እንግዊ ማለት ነው።

እስከ ፲፱፻፹፬ ዓ.ም. ድረስ የዛምቢያ የወረቀት ገንዘብ የፕሬዚደንት ኬነዝ ካውንዳን ምስል ያሳዩ ነበር። ከ፲፱፻፹፭ ዓ.ም. ጀምሮ ግን የካውንዳ ምስል በ "የአፍሪቃ አሳ አጥማጅ ንስር" ምስል ተተክቷል።

የስሙ ምንጭ ለማስተካከል

ክዋቻ የሚለው ቃል በንያንጅኛ እና በቤምባ ቋንቋዎች ንጋት ማለት ሲሆን "አዲስ የነጻነት ንጋት" የሚለውን የዛምቢያን ብሔራዊ መፈክር ያስተጋባል። "እንግዊ" ደግሞ በንያንጅኛ ብርሃን ወይም መብራት ማለት ነው።