ካሥ «ቢግ ማማ» ኤሊየት (1934-1966 ዓም፣ ልደት ስም፦ ኤለን ናዖሚ ኮውን) በጣም ዝነኛ አሜሪካዊት ዘፋኝ ነበረች። በሙዚቃዊ ጥበብዋ በቬትናም ጦርነት ዘመን በተለይም «ዘ ማማዝ ኤንድ ዘ ፓፓዝ» («እናቶቹና አባቶቹ») በተባለ ቡድን ነበረች። በዚህ ቡድን በዋንነት ታዋቂ የሆነ ምርጥ ዘፈን «ካሊፎርኒያ ድሪሚንግ» (የካሊፎርኒያ ማለም) መሆኑ ይታወሳል። እንዲሁም በቢግ ማማ በኩል የሄሮይንና የሌሎች አይነቶች አደገኛ አደንዛሽ ሱስነት እንዳደረባት ይባላል። ብዙም ጊዜ በቴሌቪዥን ፈርገማዎች ትታይ ነበር።

ካሥ ኤሊየት በቴለቪዥን 1961 ዓም

በመጨረሻ በ1966 ዓም በአንድ ግብዣ ላይ ስትቆይ አንድ ሳንድዊች እየበላች አንቆ ገደላት ይባላል። እድሜዋም ፴፪ ዓመታት ነበረ። በእድሜዋም እጅግ ስመ ጥሩ ስትሆን በኋላ ግን በአጠቃላይ ስለ ጦርነት የነበራት ተጽእኖዋ እና አስተዋጽኦ አሁን ተረስታለች።