ኩዋላ ሉምፑር (Kuala Lumpur) የማሌዢያ ዋና ከተማ ነው። በክላንግና በጎምባክ ወንዞች የሚጋጠሙበት ሥፍራ ሆኖ የስሙ ትርጉም «ጭቃማ መጋጠሚያ» ነው። የተሠራው በቻይና ሠራተኞች በ1849 ዓ.ም. ነበር።

ኩዋላ ሉምፑር
KL + Putrajaya locator.png

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር የአካባቢውን ኗሪ ሲጨምር 7.2 ሚሊዮን ሰዎች ሆኖ ሲገመት የራሱ የከተማው ኗሪ ቁጥር ደግሞ 1,887,674 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 03°08′ ሰሜን ኬክሮስ እና 10°42′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።