ኩንግ-ፉ
ኩንግ-ፉ (ቻይንኛ፦ ጎንግፉ) በቻይና ሀገር የሚያስተምሩ የትግል (ቡጢ) ሙያ ማለት ነው። በትክክለኛ ቻይንኛ ይህ የቡቅሻ ትግል ዉሹ ሲባል፣ የ«ኩንግፉ» ትርጉም በትክክል የማናቸውም አይነት ሙያ ወይም መልመጃ ነው። ለምሳሌ፣ «ኮንግ-ፉ ቻ» ማለት በሻይ (ቻ) ሥነ ሥርዓት ያለው ሙያ ማለት ነው። ከ1960ዎቹ ጀምሮ ግን የቻይና ቡቅሻ በተለይ በእንግሊዝኛ ኩንግ-ፉ ተብሏል።
ከሥነ-ፍጥረት እነዚህ እንስሳት ስለ ቡጢ ዘዴያቸው እንደ ምሳሌዎች ይወሰዳሉ፦
- እባብ - ለፍጥነት - ጣቶቹ አንድላይ
- ነብር - ለግፊት - ጣቶቹ እንደ ነብር ጥፍሮች
- ግስላ - ለምታት - ጣቶቹ በዓጽቆች ጐብጠው
- ሽመላ እና ሸማ አልብስ - ለመውጋት - ጣቶቹ ከአውራ ጣት ጋር
- ዝንጀሮ - ለደመ ነፍስ