ኩሩቭ
ኩሩቭ (Kurów) በደቡብ-ምሥራቅ ፖሎኝ ያለች መንደር ናት። ከፑዋቪ እና ከሉብሊን ከተሞች መካከል በኩሩፍካ ወንዝ ላይ ትገኛለች። በ1997 2,811 ኗሪዎች ነበሩባት።
በጳጉሜ 4 ቀን 1931 ዓ.ም. መንደሪቱ በጀርመን ሉፍትቫፈ (የአየር ኀይል) በቦምብ በጣም ተደበደበች። በጦርነቱ ጊዜ ጀርመኖች የባርዮች ሠፈር እንድትሆን አደረጉዋት። ዳሩ ግን አብዛኛው የታሠሩት ፖሎኞች ወደ ጫካ አምልጠው አርበኞች ሆኑ።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |