- ዕንቁላሉን ቀቅሎ ከበሰለ በኋላ ልጦ ቀዝቃዛ ውኃ ውስጥ መጨመር (ይህም ዕንቁላሉ እንዳይጠቁር ይረዳል)
- . ሰላጣውን በደንብ ማጠብና እንደ ጎመን ቀንጥሶ በሚቀርብበት ዕቃ ላይ ማድረግ፤
- . ቲማቲሙን አጥቦ በስሱ መቁረጥ፤
- . ዕንቁላሉን እንደ ቲማቲሙ በክቡ መክተፍ፤
- . ሰላጣውን በቲማቲሙና በዕንቁላሉ ማስጌጥ፤
- . ዘይቱን፣ ኮምጣጤውን፣ ጨውና ቁንዶ በርበሬውን በአንድ ላይ አደባልቆ በዚያ ላይ ማፍሰስና ማቅረብ፡፡