እነሞር ጉራጌ ዞን ውስጥ ከሚገኙት ወረዳዎች አንዱና ዋነኛው ሢሆን በውስጡም 66 ቀበሌዎች አሉ። በወረዳው የተለያዩ የግብርና ምርቶች የሚመረቱ ሲሆን ከእነዚህም መካከል እንሰት፣ ቡና፣ ጫት ጤፍ እንዲሁም ፍራፍሬዎችም ይመረታሉ። ወረዳዋ ሦስት አይነት የአየር ፀባይ ያላት ሲሆን እነርሱም ቆላ፣ ደጋ፣ ወይናደጋ ናቸው። የወረዳው ዋና ከተማ ጉንችሬ ናት።