ኤፍሬም ታምሩ
ኤፍሬም ታምሩ የኢትዮጵያ ታዋቂ ዘፋኝ ሲሆን ብዙ ለስለስ ያሉ የሙዚቃ ስራወችን በማበርከት ይታወቃል።
የህይወት ታሪክ
ለማስተካከልበ1960 ዓ.ም. አካባቢ ደጀን በተባለ ቦታ በትምህርት ቤቱ ውስጥ ሙዚቃ ጀመረ። ሆኖም ለርሱ ከፍተኛ ለውጥ ያመጣለት በ1963 ዓ.ም. ወደ ደብረ ማርቆስ ሄዶ በሙዚቃ ውድድር ማሸነፉ ነበር። ይህም ካጠቃላ ጎጃም አንደኛነትን ያስገኘለት ሲሆን በዚሁ የኪነጥበብ ሥራ እንዲተጋ አይነተኛ ምክንያት ነበር።
ድምጻዊ ኤፍሬም ታምሩ
ከእናቱ አትገኝ ብዙነህ እና ከአባቱ ከአቶ ታምሩ … ባህር ዳር ተወለደ፡፡
1ኛ ክፍል ባህርዳር፡
2ኛ ክፍል ደ/ማርቆስ
3ኛ-ን ሲዳሞ ጠቅላይ ግዛት - ዲላ
4ኛ-ን ወሎ ጠቅላይ ግዛት
5ኛን አዲስ አበባ ከዛ ተመልሶ ደግሞ ወደ ደ/ማርቆስ …
ከዚህ ሁሉ በፊት የ12 ዓመት ልጅ ሳለ በየክፍለሀገሩ እየዞረ ከሚጫወት ባንድ ጋራ ጊምቢ፣ ወለጋ፣ ጅማ አብሮ ተጫውቷል፡፡
ቤቱ ሲመለስ ታዲያ ‹ጎሽ የኔ ልጅ፡ አበጀኽ› እየተባለ እንዳይመሰላችኹ … በእግር ብረት እየታሠረ፣ እየተገረፈ ነው፡፡
ከአዲስ አበባ ተመልሶ ደጀን በሚማርበትም ወቅት ደ/ማርቆስ ድረስ እየኼደ ይጫወት ነበር፡፡
2ኛ ደረጃ ተማሪ ሳለ፡ ከአያሌው መስፍን ጋር ይገናኛሉ፡፡
እርሱም አጨዋወቱን ተመልክቶ ‹በአንድ ሸክላ አብረን እንጫወታለን› ሲለው ትምህርቱን አቋርጦ ለአምስት ወር ያህል በየክፍለ ሀገሩ ዞረ፡፡
ከዛም በምሥራቅ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ጨረሰ፡ …
ቬነስ፣ ዲያፍሪክ፣ ራስ ሆቴል፣ ግዮን፣ ሒልተን … የተጫወተባቸው ሥፍራዎች ናቸው፡፡
ድምጻዊ ኤፍሬም ታምሩ 12 አልበሞችን ሠርቷል፡፡
‹እንደገና› ከተሰኘው በቅርቡ ከሮሃ ባንድ ጋር ከሠራው አልበም ጋር፡፡ የተሳኩም ነበሩ፡፡
በአዚያዜሙም የሙያ ባልንጀሮቹ ‹ዘፍኖ ማሳመን ይችላል፣ ዘፍኖ ማስተኛት፣ ማስለቀስ፣ ማስደሰት … ይችላል … በአዚያዜሙ ሀዘንን ያሽራል› ይሉታል፡፡
አድናቂዎቹ -
ከዘፋኞች ኩሩ
ኤፍሬም ታምሩ … ይሉታል፡፡
የስራ ዝርዝር
ለማስተካከልአልበሞች
ለማስተካከል- ኋላ እንዳይቆጭሽ
- [መድሀኒቴ ]
ማጣቀሻወች የኤፍሬም ዘፈኖች
ለማስተካከልጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |