ኤና ዴርግ
ኤና ዴርግ በአይርላንድ አፈ ታሪክ ዘንድ ከ633 እስከ 621 ዓክልበ. ግድም ድረስ የአየርላንድ ከፍተኛ ነጉሥ ነበር።
መልኩ ቀይ ወይም ደመግቡ ስለ ሆነ፣ «ዴርግ» (ቀይ) ተባለ። የዱዊ ፊን ልጅ ነበር፣ ቂም በማብቀል የአባቱን ገዳይ ሙይረዳኽ ቦልግራኽ ከገደለ በኋላ፣ በከፍተኛ ንጉሥነት ተከተለው። በዘመኑ ለመጀመርያው ጊዜ በአይርላንድ መሐለቅ እንደ ተሠራ ተጽፏል።
የአይርላንድ ታሪኮች እንዳሉት የኤና ዘመን ለ12 ዓመታት ቆየ፤ ከዚያ ከሥራዊቱ ጋር በስሊየቭ ሚሽ ተራሮች ከተስቦ አረፈ። ልጁም ሉጋይድ ያርዶን በዙፋኑ ተከተለው።
የላውድ አቆጣጠሮች (1014 ዓም ተቀነባብሮ) እና የድሮ አቆጣጠር በመከተል፣ የኤና ዘመን ከ633 እስከ 621 ዓክልበ. ድረስ ይሆናል። (በኋላ የታዩት ታሪኮች ግን ከዚያ በፊት ያደርጉታል።)