ኤሌክትሪክ ፍሰት ማለት በአንድ ስፋት ያለው ገጽታ ውስጥ ያለ የኤሌክትሪክ መስክ ፍሰት መጠን ማለት ነው። በተወሰነ ምናባዊ ገጽታ ውስጥ የሚያልፉ የመስክ መስመሮች ብዛት ጋር አብሮ ተወዳዳሪ (ፕሮፖርሽናል) ነው።

ኢምንት የኤሌክትሪክ መስክ ፍሰት በኢምንት ገጽ ውስጥ

ሒሳባዊ ቀመር

ለማስተካከል

በአንዲት ኢምንት ስፋት   ባላት ገጽታ ውስጥ የሚገኝ ኢምንት ፍሰት   እንዲህ ይቀመራል፦

 

E በዛች ገጽታ ውስጥ የሚያልፍ የኤሌክትሪክ መስክ ነው። ዶት ፕሮደክት(  ) የሚያሳየው የሁለቱ ጨረሮች (ስፋት እና መስክ) ጥላ ብዜትን ነው። ጥላ ብዜት፣ አንዱ ጨረር ከሌላው ጨረር አኳያ ያለውን መጠን ማስያ ነው። የስፋቱ ጨረር የተሰራው ከስፋቱ መጠንና፣ ለስፋቱ ቀጤ ነክ ከሆነ አሀድ ጨረር ነው።

እንግዲህ፣ ኢምንት የሆኑትን ፍሰቶች በካልኩለስ አሰባስበን ስንጠርዛቸው የአጠቃላይ ገጽታ S ን ኤሌክትሪክ ፍሰት እናገኛለን ማለት ነው:

 

E -- ኤሌክትሪክ መስክ
dA -- ኢምንት ገጽታ
  የተዘጋው ገጽታ የውጭኛ ክፍል። ወይንም ሙሉው ገጽታ።


የጋውስ ህግ - ለዝግ ገጽታ

ለማስተካከል

በውስጡ የኤሌክትሪክ ቻርጅ Q አፍኖ ለያዘ ዝግ ገጽታ የሚያገለግል ቀመር የጋውስ ህግ ይባላል። ይህ ቀመር በተሰጠ ዝግ ገጽታ (ለምሳሌ ሉል) ያለን የኤሌክትሪክ ፍሰት ያለካልኩለስ ጥረዛ ያገኛል።

 

QS በዝግ ገጽታ ውስጥ ታፍኖ ያለ የጠታራ የ ኤሌክትሪክ ቻርጅ ብዛት ነው።
ε0ኤሌክትሪክ ቋሚ ቁጥር ነው።


ደግሞ ይዩ

ለማስተካከል

ተጨማሪ ንባብ (እንግሊዝኛ)

ለማስተካከል