ሁለት መስመሮች ቀጤ ነክ ናቸው የሚባሉት እኩል የሆኑ ጎረቤት ማዕዘኖች መፍጠር ሲችሉ ነው። ስለሆነም መስመር AB ለመስመር CD ነጥብ A ላይ ቀጤ ነክ ነው። አንድ መስመርና አንድ ጠለለል፣ ወይንም ሁለት ጠለሎች ቀጤ ነክ ሊሆኑ ይችላሉ።

መስመር AB ለመስመር CD ቀጤ ነክ ነክ ነው። ለዚህ ምክንያቱ መስመር AB የሚፈጥራቸው ማዕዘኖች (ብርቱካንና ሰማያዊ ቀለማት)፣ 90 ዲግሪ በመሆናቸው ነው

አንድ መስመር ለሌላ መስመር ቀጤ ነክ ከሆነ በሁለቱ መስመሮች መቋረጥ የሚፈጠሩት ማዕዘኖች π/2 ራዲያን ወይንም 90° ናቸው። ይህ አረፍተነገር ሲዞር ሁለት መስመሮች መገናኛቸው ላይ 90 ዲግሪ ከፈጠሩ፣ ቀጤ-ነክ ናቸው ይባላሉ።

ሁለት መስመሮች ቀጤ ነክ ከሆኑ በሂሳብ አጻጻፍ እንዲህ ይወከላሉ፦ ABCD ። የቀጤ ነክነት ምልክት ነው።

ቀጤ ነክ ከኩርባ አንጻር

ለማስተካከል

ሁለት ቀጥተኛ መስመሮች   እና   በሚከተሉት እኩልዮሾች ቢሰጡን፡

  :  
  :  

  እና   የሁለቱ መስመሮች ኩርባ ይሰኛሉ። ሁለቱ መስመሮች   እና   ቀጤ ነክ የሚሆኑት፣ የኩርባቸው ብዜት ውጤት -1 (ማለት፡  ) ከሆነና ከሆነ ብቻ ነው፡: