ቻርጅ
የኤሌክትሪክ ቻርጆች በቁስ አተም ውስጥ ከሚገኙ እኑሶች ውስጥ የአንድ አንዶቹ የተፈጥሮ ጠባይ ናቸው። ቻርጆች እራሳቸውን የሚገልጡት በሌሎች ሙሌት እኑሶች ላይ በሚያሳርፉት የስበት ወይም ግፊት ጉልበት ነው።
የኤሌክትሪክ ቻርጆች እራሳቸውን በሁለት ክፍል ይከፍላሉ፣ የአንዱ ክፍል አባላት የራሱን ክፍል አባላት ሲገፋ፣ የሌላውን ክፍል አባል ግን ይስባል። እኒህ ክፍሎች ስም ወጥቶላቸው አንዱ ክፍል ፖዚቲቭ (+) ሲሰኝ፣ ሌላው ወገን ደግሞ ነጌቲቭ (- ) ይሰኛል።
የቻርጆች ቁጠባ መርህ
ለማስተካከልለብቻ በሚገኝ ስርዓት ውስጥ ያለ የኤሌክትሪክ ፖዚቲቭና ነጌቲቭ ቻርጅ ድምር ውጤት ምንጊዜም አይለወጥም። ወይንም፣ የተጣራ የኤሌክትሪክ ቻርጅ አይፈጠርምም አይጠፋምም። ለምሳሌ በአንድ የጨው ክሪስታል ውስጥ 5 ነጌቲቭ እና 5 ፖዚትቭ ቻርጆች ቢኖሩ፣ በአጠቃላይ ያ ክሪስታል 0 ቻርጅ አለው ይባላል። ክሪስታሉ ከማናቸውም የውጭ ቁሶች ጋር እስካልተነካካ ድረስ 0 ቻርጅ እንዳለው ይቀጥላል። ይሄ መርህ በብዙ ሳይንስ ተሞክሮወች እንደተጋገጠ፣ ምንጊዜም ፀንቶ ይሰራል።
የቻርጆች ጠጣርነት (ኳንተምነት)
ለማስተካከልቻርጆች የተሰሩት ከጠጣር እኑስ ቻርጆች እንጂ እንደተፈለገ ከሚከፋፈሉ ፈሳሽ ነገሮች አይደለም። በተፈጥሮ ተለይተው የሚገኙ ቻርጆች ምንጊዜም የኤለመንታሪ ቻርጅ, e = 1.602×10−19 ኩለምብ ኢንቲጀር ብዜቶች ናቸው። ማለት የዚህ ቻርጅ 2 እጥፍ፣ 3 እጥፍ ወዘተ ሊሆኑ ይችላሉ እንጅ ለምሳሌ 2.04 እጥፍ ሊሆኑ አይችሉም። (ለዚህ ህግ አንድ ብቻ ተቃውሞ አለ፣ እርሱም ኳርክ ሲሆን የሙሌቱ ብዛት ⅓e ነው። ሆኖም ኳርኮች ለብቻቸው ተነጥለው አይገኙም፣ ይልቁኑ ምንጊዜ በሃድሮን (ፕሮቶን እና ኒውትሮን) ውስጥ ተጣብቀው ነው ሚገኙት)። ፕሮቶን ሙላቱ e ሲሆን የኤሌክትሮን ቻርጅ −e ነው። አንድ ፕሮቶን 2 ሙላታቸው +2/3e እና አንድ -⅓e ኳርኮች አሉት፣ በተቃራኒ አንድ ኒውትሮን ከ ሁለት -⅓e እና አንድ +2/3e ኳርኮች የተሰራ ነው።
የቻርጅ ልኬት
ለማስተካከልየቻርጅ መለኪያ ኩሎምብ ሲባል ምልክቱም C ነው። 1C ከ6.242e^18ue}} ጋር እኩል ነው። በሌላ ጎን አንድ ኩሎምብ ማለት በአንድ አምፔር ጅረት ውስጥ በ1ስኮንድ የሚያልፍ ቻርጅ ብዛት ነው። የኤሌክትሪክ ቻርጅ ብዘት በ Q ይወከላል። የኤሌክትርክ ሙሌት መጠንን የሚለካው መሳሪያ ኤሌክትሮሜትር ይባላል።