ኢንጂነር ኣያና ብሩአማርኛ የጽሕፈት መሣሪያንና በመሣሪያው የኣከታተቡን ዘዴ የፈጠሩ ኢትዮጵያዊ ሊቅ ናቸው። [1] [2]

ኣድዋ ድል በኋላ ኢትዮጵያውያን የእንግሊዝኛውን የታይፕራይተር ወይም የጽሕፈት መሣሪያ ኣጠቃቀም ከተረዱ ወዲህ መሣሪያውን ለኣማርኛ ቀለሞች እንዲያገለግል ለ85 ዓመታት ግድም ቢታገሉም ሳይሳካ ቀርቷል። በመካከሉ ከተደረጉት የተለያዩ ሙከራዎች መካከል የኢንጂነር ኣያና ሥራ ኣንዱ ነበር። ዋናውም ችግር የመሣሪያው መርገጫዎች በኣማርኛ ፊደላት መብዛት የተነሳ በቂ ስለኣልነበሩ ፊደላቱን ከተለያዩ መርገጫዎች በመሰብሰብ በመቀጣጠል የሚያስከትብ ዘዴ ወደ ፲፱፻፳፭ ዓ.ም. ግድም ኣቀረቡ። በእዚህ ዘዴ “” ከኣንድ መርገጫ ከተከተበ በኋላ “ሁ” ፊደል የሚከተበው “ሀ” ጎን የመቀነስ ምልክትን ወይም “-” በማስቀመጥ ነበር። ይኸንኑ የመቀነስ ምልክት “”፣ “”፣ “” እና የመሳሰሉት ጎን በማስቀመጥ “ሁ”፣ “ሉ”፣ “ሑ”፣ “ሙ” ስለሚመስሉ ኣንዱኑ መቀጠያ ለተለያዩ የፈጠራ ቁርጥራጮች እንዲሆን ተደረገ። እንደነ “ሹ” የመሳስሉትን በቅጥልጥል ለመክተብ ከ“” እና የመቀነስ ምልክት የተሠራውን “ሱ” ፊደል በሌላ መርገጫ ቀደም ብሎ ወይም ወደኋላ መልሶ ሌላ ረዥም መሰመር ከሌላ መርገጫ ከ“ሰ” ኣናት ላይ በማስቀመጥ ነበር የሚሠራው።

ይህ የቅጥልጥል ፊደል ኣሠራርና መኖር ዓማርኛ ባልሆነ ነገር ቀለሞቹን በመሰሉ ነገሮች የቢሮ ሥራ መሥራት ስለተቻለ ኣያና ብሩ ለኢትዮጵያ ታላቅ ባለውለታ ናቸው። የኣያና መሣሪያ ባይኖር ኖሮ የቢሮ ጽሑፎችን በእጅ ጽሑፍ ተጠቅሞ መቀጠል ማዛለቁ ስለሚያጠራጥር ኢንጂነር ኣያና ለዓማርኛ እድገት ክፍተኛ ኣስተዋጽዖ ኣድርገዋል። እንዲህም ሆኖ ትክክለኛውን የግዕዝ ቀለሞች የኢትዮጵያ ማተሚያ ቤቶች ቀደም ብለው ሲጠቀሙባቸው ስለነበርና በኋላም ሲጠቀሙበት ስለነበረ የታይፕ ፊደል ከማተሚያ ቤቶቹ ጋር ግንኙንት ኣልነበረውም። የኣያና የጽሕፈት መኪና ቀለሞችም የዓማርኛ ፊደላት ኣልነበሩም፤ ሊሆኑም ኣይችሉም። ይህ ልዩነት ያልገባቸውና ከመቶ ያነሱ መርገጫዎች ላይ የተበተኑትን የታይፕ ቁርጥራቾጭ ከ፪፻ በላይ የሆኑት የዓማርኛ ቀለሞች ኣንድ የሚመስሏቸው ዛሬም ኣሉ።

የኢንጂነሩ የጽሕፈት መኪና ፊደል እንደ እንግሊዝኛው ወደ ኮምፕዩተር መግባት ነበረበት የሚሉ ቢኖሩም የእንግሊዝኛው ቅጥልጥል ስላልሆነና ትክክለኛዎቹን ቀለሞች ስለከተበ ነው ወደ ኮምፕዩተር የተሻሻለው። የዓማርኛው መሣሪያ ግን ዓማርኛ ስላልከተበ ወደ ኮምፕዩተር መግባት የለበትም ብለው በጽሑፍ ተከራክረው ያስቀሩት ዶ/ር ኣበራ ሞላ ናቸው። [3] Archived ማርች 5, 2016 at the Wayback Machine [4] ከእዚህም ሌላ የዓማርኛ መሣሪያው ብዙ ችግሮች ኣሉት። ለምሳሌ ያህል ያልተሟላ ከመሆኑ ሌላ የገጹ ስፋት ወይም የፊደሉ መጠን ሲቀየር ቅጥሎቹ ይገነጠላሉ ወይም ይደበቃሉ። ማሕተም የመሳሰሉትን ለመሥራት ሲሞከር ቅጥሎቹ ኣንዳንድ ስፍራዎች ይዘው ስለሚቀመጡ ኣያሠሩም። የቀለሞቹ ኣመዳደብና ኣከታተብ ለመቀጠል ማመቸት ላይ የተመሠረተ ነው። ፊደላቱ ሲቀጠሉ ኣስቀጣይና ተቀጣይ ኣስቀያሚ ኣዳዲስ መልኮች እንዲኖሯቸው ኣስገድዷል። በተጨማሪም የታይፕ መሣሪያው ዓላም ጽሑፍን ወረቀት ላይ ለማስፍር ብቻ ሲሆን የኮምፕዩተር ጥቅም ኮዶቹን ማስቀመጥ ነው። የጽሕፈት መሣሪያው ውሱን ኣሠራር በኣንድ የፊደል መጠን እንዲሠራ ሲሆን ኮምፕዩተር ኣንዱን ፊደል ለተለያዩ የፊደል መጠኖችና ቅርጾች የሚያሠራ ነው። የታይፕ መጻፊያው በኣንድ የላቲን የፊደል ገበታ ምትክ የቀረበ ስለሆነ ጊዜው የኣለፈበት መሣሪያ ነበር። ዶክተሩ ግዕዙን ወደ ኮምፕዩተር የኣስገቡት በስምንት የእንግሊዝኛ የፊደል ገበታዎች ምትክ መሆኑ ታትሟል። መሣሪያው ተሻሽሎም ሊጠቅም ስለማይችልና ሁሉንም የግዕዝ ቀለሞች ሊያስከትብ ስለማይችል ወደ ኮምፕዩተር አንዳይገባ በምክንያት ቀርቧል። [5] በምትኩ ትክክለኛዎቹን የግዕዝ ፊደላት ወደ ኮምፕዩተር በዶክተሩ ኣዲስ ዘዴ ለመጀመሪያ ጊዜ ሥራ ላይ ውሏል። በእዚህ የተነሳ ወደ ዩኒኮድ የዓለም ፊደላት መደብ የገባው ትክክለኛው የግዕዝ ፊደል ስለሆነ በዓማርኛ ታይፕራይተር ቁርጥራጭ ፊደላት መጠቀም ከቀረ ቆይቷል። ዶክተሩ የአማርኛ ታይፕራይተየር ኣማርኛን እንዳልጻፈ ስለሚያውቁ እንጂ ቀደም ብለው የታይፑን ዓይነት ማውጣት ስለሚችሉ ሁሉንም የዓማርኛ ቅጥልጥሎች የሚያስከትብ GeezEdit Amharic P ፊደል ለመጀመሪያ ጊዜ ሠርተው ሰዉ ስለ ኤድስ እንዲያነብበት በነፃ ለግሰዋል።

የኣማርኛ ታይፕራይተር ከኣንድ የፊደል ገበታ የመቀጣጠል ዘዴ እ.ኤ.ኣ. ከ1985 ጀምሮ በኮምፕዩተርም ቀርቦ ነበር። ግዕዝ በዶ/ር ኣበራ ሞላ ኮምፕዩተራይዝድ ስለሆነ የታይፕራይተሩ ዘዴ ውድቅ ቢሆንም ይኸን ከኣቀረቡትም ኣንዱ ግዕዝ ያልሆነውን በሓሰት Ethiopic ነው ከማለቱም ሌላ ፓተንት ኣለኝ የሚል ኢትዮጵያዊ ኣለ። ዶክተሩ እየተቃወሙም እ.ኤ.ኣ. በ1992 ለዩኒኮድ የቀረበ የተሻሻለ የታይፕ መሣሪያ ቅጥልጥል ፊደል እዚህ [6] ኣለ። ዶክተሩ የዓማርኛ ፊደላት ተቀጣጥለው ለኮምፕዩተር ኣይቀርቡም ብለው ከኣሸነፋ በኋላ ሌሎች እ.ኤ.ኣ. በ1996 [7] ትክክኛዎቹን የዓማርኛ፣ ትግርኛና ኦሮምኛ ቀለሞች ኣቅርበው የኣናሳ ቋንቋዎች የግዕዝ ፊደላት መብዛት የኣልፈለጉ መንደርተኞች በቅጥልጥልነት ዩኒኮድ መደብ ውስጥ እንዲገቡ የፈለጉትንም ኣሸንፈው ዛሬ ወደ 500 የሚጠጉ የግዕዝ ቀለምች በተነጣጠል በዩኒኮድ ዕውቅና ኣግኝተዋል። ይህ ሁሉ ሲደረግ እያንቀላፉ ከኣሉት መካከል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምሁራንና ሌሎችም ኣሉበት።

ኢንጂነር ኣያና ብሩ ጣልያን ኢትዮጵያን በወረረችበት ጊዜ ኣርበኛ ነበሩ። [8]

የውጭ መያያዣዎች ለማስተካከል

  • [9] Archived ሴፕቴምበር 6, 2013 at the Wayback Machine ስለ አማርኛ ፊደል መሻሻል የተደረጉ ጥናቶች መዘርዝር፣ ክንፈ ሚካኤል፣ ፳፻፪ ዓ.ም.፣ ሜልበርን፣ ኦስትሬልያ
  • [13] ኣበራ ሞላ