አፅትላን
አፅትላን (ናዋትል፦ Aztlān) በሜክሲኮ የሚገኙት የናዋ ብሐሮች አፈታሪካዊ መኖሪያ አገር ቤት ነው። አፅቴክ የሚለው ስያሜ ትርጉም «የአፅትላን ሕዝብ» ነው።
በናዋትል ትውፊቶች ዘንድ፣ 7 ጎሣዎች በ7 ዋሻዎች ውስጥ ቺኮሞጽቶክ በተባለ አገር ይኖሩ ነበር። እነርሱም ሾቺሚልካ፣ ትላዊካ፣ አኮልዋ፣ ትላሽካላን፣ ቴፓኔካ፣ ቻልካ እና መሺካ ተባሉ። ከጊዜ በኋላ እነኚህ ጎሣዎች ከዚያ ወጥተው ወደ አጽትላን ፈለሡ።
በአንዳንድ የትውፊት ሰነድ ውስጥ አጽትላን እንደ ሰላማዊ ገነት ይባላል፤ በአንዱ ዘንድ ግን በአጽትላን አዝቴኮች በአምባገነን ሥር ይኖሩ ነበር። በቄሳቸው ተምረው፣ አዝቴኮቹ ከዚያ ሸሹ፣ በመንገዳቸውም አምላካቸው ዊጺሎፖችትሊ ስማቸው «አዝቴክ» እንዳይሆን ከለከለ፤ ከእንግዲህ ወዲህ «መሺካ» እንዲባሉ ነገራቸው።
በትውፊቶቹ አቆጣጠር ከአጽትላን ወደ ደቡብ የተጓዙበት አመት 1056 ዓ.ም. ነበር። በመጨረሻ መሺካዎች በአዲስ አገራቸው (የዛሬ ሜክሲኮ ሸለቆ) ደረሱ።
ይህ አጽትላን ከሜክሲኮ ወደ ስሜን ስለ ተገኘ፣ አሁን ዩናይትድ ስቴትስ በሚባለው ግዛት ውስጥ እንደ ነበር የሚሉ አስተሳሰቦች ብዙ አሉ።