==

ዐፄ ዐምደ ጽዮን
የዐጼ ዐምደ ጽዮን ደብዳቤ በቫቲካን ቤተ መጻህፍት ለ700 አመታት የተቀመጠ
የዐጼ ዐምደ ጽዮን ደብዳቤ በቫቲካን ቤተ መጻህፍት ለ700 አመታት የተቀመጠ
ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ
ግዛት ከ1314-1344
ቀዳሚ ዐፄ ወደም አራድ
ተከታይ ዐፄ ነዋየ ክርስቶስ
ባለቤት ብሌን ሳባ
ሙሉ ስም ገብረ መስቀል
ሥርወ-መንግሥት ሰሎሞን
አባት ወደም አራድ
ሀይማኖት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስትና

==


ቀዳማዊ ዐጼ ዐምደ፡ጽዮን (የዙፋን ስም ገብረ መስቀል) ከ1314 እስከ 1344 ዓ.ም. የነገሡ ሲኾን በጥንቱ ዘመን ከተነሱ ነገሥታት ውስጥ በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ሰፋ ያለ አሻራ ትተው ካለፉት (ለምሳሌ፦ ዘርዐ ያዕቆብ ) ጎን ወይም በላይ ስማቸው ይጠቀሳል[1] ። ዐጼ ዐምደ ጽዮን የዐጼ ይኩኖ አምላክ የልጅ ልጅና የዐጼ ወድም አራድ ልጅ እንደሆኑ ይታመናል[2]፡፡ ይኩኖ አምላክ አዲሱን የሰሎሞን ሥርወ መንግሥት ቢመሰርቱም፣ በልጅ ልጆቻቸው የነበረው ፉክክርና አዲስ ከሚስፋፋው የእስልምና ሃይማኖት የሚሰነዘረው ጥቃት ስርዓቱን ስጋት ላይ የጣለ ነበር። ዐጼ ዐምደ ጽዮን ይህን ፉክክር በማስቆምና በዘመናት በማይደበዝዘው ጀግንነታቸው የኢትዮጵያን ድንበር ከሞላ ጎደል አሁን በሚታወቀው መልኩ በማስቀመጥ፣ የዐዲሱን ሥርወ መንግሥት መሰረት በማጽናት እንዲሁም በማረጋጋት ዝናቸው በጥንቱ አለም ክአፍሪቃ ቀንድ እስከ አውሮጳ የተንሰራፋ ነበር [3]

የአጼ ዐምደ ጽዮን ዘመንና ዘመቻዎች

ለማስተካከል

ዘመቻ ወደ ደቡብ ምዕራብና ሰሜን ኢትዮጵያ

ለማስተካከል

ዐምደ ጽዮን በእንዴት መንገድ ወደ ስልጣን እንደመጡ መረጃ የለም፣ ስለሆነም ታሪክ አጥኝው ታደሰ ታምራት ንጉሱ ከአባታቸው ጋር ትግል ገጥመው ዘውድ ላይ እንደወጡ መላ ምት ያቀርባል [4] ። ንጉሱ በመንግስታቸው መጀመሪያ (፲፫፻፲፮ ዓ.ም. ) የተሳካላቸው ዘመቻዎች በጎጃምዳሞትሐድያ በማድረግ እኒህ አካባቢወች እንዲገብሩ ሆነ[5]። ሆኖም በኒህ ዘመቻወች ትኩረታቸው ስለተሳበ በተገኘው ክፍተት የእንደርታ ገዢ የነበረው ይብቃ እግዚአምባ ሰናይትብልሃትንና ተምቤን ሰራዊትን በማደራጀት በንጉሱ ላይ ተነሳ [6]። በ1320ዓ.ም ንጉሱ የይብቃ እግዚን አመጽ ከደመሰሱ በኋላ በአምባ ሰናይት የጦር ዕዝ አቋቋመው ወደ ስሜን በመዝመት እስከ ቀይ ባህር ድረስ ያለውን ክፍል ለመቆጣጠር ቻሉ [7]። በዚህ ወቅት እንደረታን እንድታስተዳድር የተሰየመችው የትግሬ ተወላጅ የነበረችው የንጉሡ ሚስት ንግሥት ብሌን ሳባ ነበረች። ስልጣኗም ባልታ ብሃት በመባል ይታወቅ ነበር። ቆይቶ እንደርታን እንዲያስተዳድር የተደረገው የንጉሱ ሦሥተኛ ልጅ ባህር አሰገድማዕከለ ባህር ማረግ ነበር፣ ግዛቱም እስከ ቀይ ባህር ወደብ ድረስ የተንሰራፋ ነበር [8]

ዘመቻ ወደ ደቡብና ደቡብ ምስራቅ

ለማስተካከል

የንጉሱ ትኩረት ወደ ሰሜን መሆኑን የተረዱት የደቡብ እስላማዊ ክፍሎች፣ በቀይ ባህር ንግድ ላይ ያላቸውን ቁጥጥር እና ሃይል ተመርኩዘው የአርብቶ አደሩን ክፍል በማስተባበር የሃይል ማደግ አሳዩ። በተለይ በወላስማ ሱልጣኖች የሚመራውና በደቡብ ምዕራብ ሸዋ የሚገኘው የይፋት ግዛት በሃይል ተጠናከረ። ይህ ክፍል፣ ከአጼ ዐምደ ጽዮን ዘመን በፊት ጀምሮ ለመካከለኛው የኢትዮጵያ መንግስት ግብር ከፋይ ነበር። ሆኖም ክፍሉ በዚህ ዘመን እራሱን ችሎ ለመገንጠል ፈለገ [9]። በዚህ ሁኔታ የክርስቲያንና የእስልምና ግዛት በሰሜንና በደቡብ እየተጠናከሩ ሁለት የሃይል ማዕከሎች በመፍጠር ፉክክር ውስጥ ገብተው ከፍተኛ ጦርነት መነሳቱ ግድ ሆነ።

ወደ ግብጽ ተልኮ የነበረው ጥንታይ የተሰኘው የንጉሡ መልዕክተኛ ሃቀዲን በተባለ የይፋት ገዢ መታሰር በመጨረሻ ጦርነቱ ገንፍሎ እንዲወጣ አደረገ። ዐምደ ጽዮን ይፋትን ከደመሰሰ በኋል በጀበልወርጂ አርብቶ አደሮች ተቃጥቶበት የነበረውን ጥቃት ድል በማድረግ እንዲሁም የክርስቲያን ክፍሎች፣ ተጉለትዝጋመንዝ አመጾችን በማጥፋት ሃቃዲንን በማሰር ከስልጣን አስወገደው ። በርሱ ቦታ ወንድሙን ሰአደ'አድዲን አህመድን ከላይ የተገለጹት ክፍሎችን አስተዳዳሪ አድርጎ ሾመው።




ስምንቱ የደቡብ መንግስታትም፣ የሱማሌንና የሃድያን ጨምሮ ለሱ ግብር ይከፍሉ እንደነበር ሳልት የተሰኘው የእንግሊዝ ጻህፊ ዘግቦት ይገኛል። የኢትዮጵያም ድበር በኢየሩሳሌም የተከፈተው በኒሁ ንጉስ መልካም ፈቃድ ነበር። ከዚህ በተረፈ «የወታደሩ እንጉርጉሮ» የተሰኙት አራቱ የአማርኛ መዛግብት በዚህ ዘመን እንደተጻፉ ታሪክ ዘጋቢወች ይናገራሉ።


  1. ^ Edward Ullendorff, his review of Huntingford's translation of The Glorious Victories of Amda Ṣeyon, King of Ethiopia, Bulletin of the School of Oriental and African Studies, University of London, 29 (1966), p. 600
  2. ^ Basset I, II
  3. ^ Cerulli 1932
  4. ^ ታደሰ ታምራት፣ pices 4, ቅጽ 1, ገጽ 505
  5. ^ Marrasini, Lo Scettro e lacroce, La Camagna Di 'Amda Seyon I contro l'Ifat (1332)
  6. ^ ታደሰ ታምራት፣ 1970፣ ገጽ 95f
  7. ^ ታደሰ ታምራት 1970: ገጽ 95
  8. ^ Conti Rossini, 1901: ገጽ 34
  9. ^ ታደሰ ታምራት፣ ቤተከርስቲያንና ሀገር፣ ገጽ 130