አብዱ ኪያር የኢትዮጵያ ታዋቂ ዘፋኝ ሲሆን ብዙ ዘመናዊ የሙዚቃ ስራዎችን በማቅረብ ይታወቃል።
አብዱ ኪያር ከሰባት ልጆች የመጨረሻው ነው። ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ከጨረሰ በኋላ በ1997 እ.ኤ.አ. ኤክስፕረስ ባንድን ተቀላቀለ። ኮፊ ሀውስ እና አንበሳ ክለብ በተባሉ የምሽት ክበቦች ይዘፍን ነበረ። ከዚያም በ1998 እ.ኤ.አ. ወደ ጅዳ፣ ሳዑዲ አረቢያ ሄዶ በቡቲክ ውስጥ ይሰራ ነበረ።