አባ ሳሙኤል ወልደ ካህንራስ ተፈሪ መኮንን (በኋላ ንጉሠ ነገሥት ቀደማዊ ኃይለ ሥላሴ) እና የዘመዳቸው የራስ እምሩ ኃይለ ሥላሴ አስተማሪ 1894-1904 ዓ.ም. ግድም ሁለታቸው በሐረር የኖሩ ልጆች በሆኑበት ጊዜ ነበሩ።

ጃንሆይ በጻፉት መጽሐፍ ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ (ምዕ. 1) መሠረት፣ አባታቸው ራስ መኮንን ፣ ልጆቹን በፈረንሳይኛ በቀን አንድ ሰአት እንዲያስተምሯቸው የጉዋዶሎፕ ሐኪም ዶ/ር ቢታልያን እንዳስቀጠሩ ይታወሳል። ይህ በቂ እንዳልሆነ ስለመስላቸው፣ ከሐረር የፈረንሳይ ካፑቺን መነኩሴ ሚሲዮን አባ ሳሙኤል የተባለውን ኢትዮጵያዊ ደግሞ አስቀጠሩ።[1]. የሳሙኤል አባት አለቃ ወልደ ካህን ከዚህ በፊት የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ተከታይ ወደ መሆን እምነቱን አዛውረው ነበር።

የታሪክ ጸሐፊ ኤች ጂ ማርኩስ እንደሚለው፣ ስለዚሁ ሁኔታ «ራስ ተፈሪ በራሳቸው ወገን ወደ ካቶሊክ ሃይማኖት ለመዛወር ያስባሉ» የሚል ጥርጣሬ በመኳንንት መካከል ተነሣ። ይህንን ጥርጣሬ ጸጥ ለማድረግ፣ ተፈሪ በ1898 ዓ.ም. ዳግመኛ በተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተጠመቁ።[2].

የወደፊት ንጉሥ በሕይወታቸው መጽሐፍ እንዳስታወሷቸው፤

«አባ ሳሙኤል ትልቅ ዕውቀት ያለው፡ ለመማርም ለማስተማርም የሚተጋ፡ በደግነትና በትሕትና ከማንም ሰው ዕውቀትን እንደ ንብ የሚቀሥም፡ በፍቅረ እግዚአብሔና በፍቅረ ቢጽ የተጠመደ፡ የነፍሱን እንጂ የሥጋውን ጥቅም ለማግኘት የማይጥር ደግ ሰው ነበር።»

በኋላ በመጽሐፉ 5ኛው ምዕራፍ በግንቦት 30 ቀን 1907 ዓ.ም. በሃረማያ ባሕር ከሰመጡት 7 ሰዎች መካከል አባ ሳሙኤል አንድ ሆነው እንዳረፉ ይላሉ።

ዋቢ ምንጮች ለማስተካከል

  • Haile Selassie I, My Life and Ethiopia's Progress, Volume One: 1892-1937 ISBN 0-94839-040-9
  1. ^ Historical Dictionary of Ethiopia p. 193.
  2. ^ H.G. Marcus, Haile Selassie I: The Formative Years, 1892-1936, p. 7.