የታችኛው የአዋሽ ሸለቆ

አዋሽ ወንዝ

ለማስተካከል

አዋሽ (አንዳንዴ ሲፃፍ  በኦሮምኛ Awaash ፤በአማርኛ  አዋሽ ፤በ አፋርኛ  ወአዮት፤በሶማሌኛ  ወብጋድር)የኢትዮጵያ ዋና ወንዝ ነው። የወንዙ ፍሰት(ሂድት) ሙሉ  በሙሉ  በኢትዮጵያ  ወሰን ውስጥ የተቀመጠ  ሲሆን እርስ በርስ የተሳሰሩ ሐይቆችን በሰንሰለት ውስጥ የተቀመጠ ነው፡፡ የወንዙ ፍሰት   ከጋርጎሪ  ሐይቅ ጀምሮ በጅቡቲ ድንበር ላይ ከሚገኘው አብይ ሐይቅ (ወይም አብይ ባድ)ያበቃል ወይም ይደመደማል) ። ይህ አካሄድ ከጣድጁራ ባህረ ሰላጤ ራስ 100 ኪሎ ሜትር (60 ወይም 70 ኪሎ ሜትር) ርቀት ላይ ይገኛል። ዋና የወንዙ የተዘጋ (ኢንዶርሂክ) ተፋሰስ ክልል የአማራየኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎችን  እንዲሁም የአፋርን ደቡባዊ ግማሽ ክፍል የሚሸፍን የተዘጋ ተፋሰስ ክልል ነው፡፡

የአዋሽ ሸለቆ (በተለይም መካከለኛው አዋሽ) ከፍተኛ  ቁጥር ያለው በሆሚኒን ቅሪተ አካላት መገኛ በመሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ የታወቀ ነው። ይህ ሸለቆ የሰው ልጆችን ቀደምት ዝግመተ ለውጥ ወደር የለሽ  ዕውቀት ይሰጣል።[1] "ሉሲ"፣ በጣም ታዋቂ ከሆኑት ቀደምት የሆመኒን ቅሪተ አካላት መካከል አንዱ፣ በታችኛው አዋሽ ሸለቆ ተገኘ ነው።[1] የአዋሽ የታችኛው ሸለቆ ለቅሪተ አካልና ለሰው ልጅ ባለዉ ጠቀሜታ በ1980 ዓ.ም. በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ መዝገብ ላይ ተቀርጾ ነበር።[1]

መጠቆሚያዎች

ለማስተካከል
  1. ^ https://en.wikipedia.org/wiki/Awash_River#cite_note-unesco-1