ሐረር
ዋና ከተማ እና በግንብ የተጠረች ከተማ | |
---|---|
ከላይ ከግራ ወደ ቀኝ: ቡዳ በር (በድሮ በሪ); የሸሪፍ ሙዚየም; ጃሚያ መስጊድ; ስላሴ ቤተ ክርስቲያን; የጁገል ገጽታ በርቀት | |
ቅጽል ስም፡ የቅዱሳን ከተማ( مدينة الأَوْلِيَا) | |
በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ቦታ | |
Coordinates: | 9°18′40″N 42°7′40″E |
ሀገር : | ኢትዮጵያ |
ክልል : | ሀረሪ |
መንግስት | |
ፕሬዝዳንት : | ኦርዲን በድሪ |
ከፍታ: | 1,885 ሜ (6,184 ጫማ |
የህዝብ ብዛት
(2007)[1] | |
ጠቅላላ : | 99,368 |
ግምት (2021):[2] | 153,000 |
የሰዓት ዞን UTC+3 (EAT): | የዳዉድ ሥርወ መንግሥት |
የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ቦታ | |
ይፋዊ ስም: | ሃረር ጁጎል፣ በግንብ የታጠረች ታሪካዊ ከተማ |
መስፈርት : | የባህል፡ ii, iii, iv, v |
ማጣቀሻ: | 1189 |
የተመዘገበው: | 2006 (30ኛ ዙር) |
አካባቢ: | 48 ሄክታር |
ማስታወሻዎች
ለማስተካከልa. ቀደም ሲል ሐረር ተብሎ ተጽፏል; [3] ሌሎች ልዩነቶች ሃረር እና ሀረር ያካትታሉ ።
ሐረር ( በአማርኛ ሐረር: በሐረሪኛ ሐረር;[4] በ ኦሮሞኛ: አደሬ ቢዮ; [5] በሱማሊኛ: ሄሬር; በአረብኛ: ሐረር ) ጥንት የሚኖሩ የአገሬው ተወላጆች ዘንድ ጌይ [6] (ከተማው በሐረሪ ሲጠራ ጌይ Gey ') በምስራቅ ኢትዮጵያ በቅጥር ግንብ የታጠረች ከተማ ነች ። በአረብኛም የቅዱሳን ከተማ ( مدي نة ا በመባል ትታወቃለች ይታወቃል ። ሐረር የሐረሪ ክልል ዋና ከተማ ነች ። ጥንታዊቷ ከተማ በምስራቃዊ የሀገሪቱ ክፍል በተራራ ጫፍ ላይ የምትገኝ ሲሆን ከኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ አምስት መቶ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በ1,885 ሜትር (6,184 ጫማ) ከፍታ ላይ ትገኛለች። ለዘመናት ሀረር ትልቅ የንግድ ማዕከል ሆና በንግዱ መስመር ከተቀረው የኢትዮጵያ ክፍል፣ ከመላው የአፍሪካ ቀንድ ፣
ከአረብ ባሕረ ገብ መሬት ፣ ከእስያ እና ከወደቦቿ፣ ከውጪው ዓለም ጋር ተቆራኝታለች። በ2006 ዓ.ም በዩኔስኮ ለባህላዊ
ቅርሶቿ እውቅና በመስጠት የቀድሞዋ ሀረር ጁጎል በአለም ቅርስነት ተመዝግቧል ። [7] ሐረር በጊዚው በነበረው የንግድ ላይ ከአረብ ባህረ ሰላጤ ጋር በነበራት የረዥም ጊዜ የንግድ ትስስር ላይ በንቃት በመሳተፏ ምክኒያት የኢትዮጵያ መንግሥት በከተማው ውስጥ ያሉ ታሪካዊ ቦታዎችን ወይም ዕቃዎችን ማፍረስ ወይም ጣልቃ መግባቱን የወንጀል ወንጀል አድርጎታል። እነዚህም የድንጋይ ቤቶች፣ ሙዚየሞች እና ከጦርነት የተወገዱ ዕቃዎች ይገኙበታል። ዩኔስኮ እንደገለጸው “በእስልምና አራተኛዋ ቅድስት ከተማ” ተብላ ትቆጠራለች
” 82 መስጊዶች ያሏት እና ከእነዚህ ውስጥ ሦስቱ በ 10 ኛው ክፍለ ዘመን የተፈጠሩ እና 102 መቅደሶች ባለቤት ናት። [8][9]
በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ያልታተመ የከተማዋ ታሪክ የሆነው የያህያ ነስረላህ ፋትሀ መዲናት ሀረር ሪከርድ መሰረት፣ ታዋቂው ቅዱስ አባድር ኡመር አር-ሪዳ እና ሌሎች በርካታ የሀይማኖት መሪዎች በሐረር አምባ ላይ እንደሰፈሩ ዘግቧል። 1216 (612 AH).
[10] ሐረር በ 1520 በሱልጣን አቡበከር ኢብኑ ሙሐመድ አዲሱ የአዳል ሱልጣኔት ዋና ከተማ ሆነች ። [11] ከተማዋ
በሚቀጥለው የሐረር ኢሚሬትስ ወቅት ፖለቲካዊ ውድቀት ታይቷል ፣ በግብፅ ኬዲቫት ጊዜ ውስጥ የተወሰነ ጠቀሜታ
አገኘች ። በኢትዮጵያ ኢምፓየር ዘመን ፣ ከተማዋ ብትፈራርስም የተወሰነ የባህል ክብሮቿን ማስጠበቅ ችላለች ።
ታሪክ
ለማስተካከልሀረር መቼ እንደተመሰረተች በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ቀናቶች የተጠቆሙ በመሆኑ ምክኒያት በግልፅ ይህ ነው ለማለት አይቻልም ።[12] ያም ሆነ ይህ ዘመናዊቷ የሐረር ከተማ በአብዛኛው በ1700ዎቹ መጀመሪያ ላይ ትገኛለች ነገር ግን ቦታው ራሱ የከተማ ቦታ ሆኖ ቆይቷል። [12]የመጀመርያዎቹ የክልሉ ነዋሪዎች የሐረሪ ሕዝብ ሳይሆኑ አይቀርም ። [13] ሐረር በስድስተኛው ክፍለ ዘመን የሃርላ
ኪንግደም ግዛት አካል ነበረች። [14] [15]በእስልምና ዘመን ከተማዋ በዘይላ የተዋሕዶ መንግስታት ጥምረት ነበረች ። [5]
በአስራ ሁለተኛው ክፍለ ዘመን የኖረው አይሁዳዊ ተጓዥ ቢንያም የቱዴላ እንደሚለው ፣ የዘይላ ክልል በምዕራብ በአል
-ሐበሻ የታጠረ የሀቪላ ምድር ነበር። [16][17]
በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሐረር በማህዙሚ ሥርወ መንግሥት የሸዋ ሱልጣኔት ሥር ነበረች ። [18][19]
እስልምና ከዘይላ ጋር በመገበያየት በሐረር አምባ ላይ በ10ኛው-11ኛው መቶ ክፍለ ዘመን እ.ኤ.አ. [12] በ 13 ኛው ክፍለ
ዘመን እስልምና በክልሉ ውስጥ የበላይ ሃይማኖት ሆነ። [12]
የሙስሊም መንግስታት መነሳት
ለማስተካከልሐረር በመካከለኛው ዘመን መጨረሻ በአፍሪካ ቀንድ የእስልምና ባህልና ሃይማኖት ማዕከል ሆና ብቅ አለች ።
ፋትህ መዲናት ሀረር እንደሚለው ፣ በ612ኛው ሂጅራ (1216 መቶ ክፍለ ዘመን እ.ኤ.አ..) አካባቢ ታዋቂው ቅዱስ አባድር ኡመር አል-ሪዳ ከብዙ የሀይማኖት አባቶች ጋር ከአረብ ባሕረ ሰላጤ መሬት መጥተው አባድር በሃርላ ጋቱሪ እና አርጎባ ህዝቦች ይገኙበታል ተብሎ በሚታመንበት በሐረር አምባ ላይ ለመኖር መጡ።. [20] በባህሉ መሠረት የአባድር ወንድም ፋክር አድ-ዲን የሞቃዲሾ
ሱልጣኔትን ሲመሰርት ከዘሮቹ አንዱ የሀዲያ ሱልጣኔትን መሰረተ ። [21][22]
በ14ኛው ክፍለ ዘመን በአምደ ጺዮን 1 ኛ ታሪክ መሰረት ሐረር (ጌይ) በሃርላ አገር ቅኝ ግዛት ነበር። [23] በመካከለኛው ዘመን፣
ሐረር የአዳል ሱልጣኔት አካል ነበረች ፣ በ1520 በሱልጣን አቡበከር ኢብን መሐመድ አገዛዝ ስር በነበረችበት ጊዜ ዋና ከተማዋ ሆነች ። አሥራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን ለከተማዋ ወርቃማ ዘመን ነበር። የአገሬው ባህል ያበበበት ፣የነበሩ በርካታ ገጣሚዎችም እንዲጽፉ ምቹ ሁኔታ ተፈጥፘል ። በተጨማሪም በቡና ፣ በሽመና ፣ በቅርጫት ስራ (እደ ጥበብ) እና በመፅሃፍ ጥረዛ ትታወቅ ነበር ።
በአስራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን በሐረር፣በኩል አህመድ ኢብኑ ኢብራሂም አል-ጋዚ “ጉሬይ”ወይም “ግራኝ”ሁለቱም ትርጉማቸው “ግራኝ” በመባል የሚታወቁት መሪ፣ ግዛቱን በማስፋፋት የኢትዮጵያ ኢምፓየር ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖችን ህልውና አደጋ ላይ የጣለ ጦርነት ከፍቷል።
የሱ ተከታይ አልጋ ወራሽ የነበሩት አሚር ኑር ኢብኑ ሙጃሂድ ህዝቧን ከኦሮሞ ወረራ ለመከላከል በከተማዋ ዙሪያ የመከላከያ ግንብ ገነባ። ይህ አራት ሜትር ከፍታ እና አምስት በሮች ያሉት ግንብ መጠሪያው ጁገል ግንብ ሲባል ይህ ታሪካዊ ግንብ አሁንም ያልተቋረጠ እና የከተማዋ ነዋሪዎች የሀረሪ ህዝብ ምልክት ነው ። በግንቡ ውስጥም የስልጤ ፣ የወለኔ ፣የ ሀላባ እና
የሀረሪ ህዝብ ይኖሩ የነበረ ቢሆንም ከሀረር በስተቀር ቀሪዎቹ ሦስቱ ወደ ጉራጌ ክልል ሄደዋል። [24]
የአህመድ ጦርነት ልክ እንዳበቃ ብዙም ሳይቆይ ሀረር በከባድ ረሃብ ተመታች። [25] ራሀቡን ተከትሎ የምግብና የእንስሳት ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ የጨመረ ሲሆን የአንድ ሰዓ( አራት እፍኝ የሚሞላ) ማሽላ 12 አሽራፊ ሲሸጥ እኩል መጠን ያለው ጨው ዋጋ 15 . [25]
እና አንዲት ላም ከ300 በላይ አሽራፊዎች ገብቶ ነበር። [25] ኢኮኖሚው ከረሃብ ሲያገግም የአራት እፍኝ ማሽላ ዋጋ ከ4-5 ማሃለቅ
(የአሽራፊው 3/4) ወርዷል። [25] በኑር ኢብኑ ሙጃሂድ ዘመን በተከሰተ ሌላኛው ረሃብ ዘመን ላይ የአንድ ሰዓ(አራት እፍኝ የሚሞላ) ማሽላ ዋጋ ወደ 2 አሽራፊዎች ከፍ ብሏል። [25]ይህ በሐረር ውስጥ የአሽራፊ እና ማሀላክ እንደ መገበያያ ገንዘብ ተብለው ሲጠሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።[25]
በሐረር ጎዳናዎች ላይ ከእንጨት የተሠሩ በረንዳዎች።
የሐረር ኢሚሬትስም የራሱን ገንዘብ አትᎂል፣ የመጀመሪያዎቹ ሊነበቡ የሚችሉ ቀን የያዙ ሲሆን ገንዘቡም ላይ 615 ሂጅራ (1218/19 CE)ይዘዋል ። ነገር ግን የመጀመሪያዎቹ ሳንቲሞች (በ1789 CE) የታተሙ ሲሆን ተጨማሪ ገንዘቦች በአስራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን ታትᎂል። [26]
ኤሊሴ ሬክሉስ (1886) ከሐረር ወደ ዘይላ የሚወስዱትን ሁለቱን ጥንታዊ መንገዶች ፣ማለትም በገዳቡርሲ አገር የሚያልፍ አንድኛው
መንገድ እና ሌላኛው የኢሳ ግዛትን የሚያልፉ መንገዶችን ሁለቱንም የዲር ጎሳ ቤተሰብ መሆኑን ይገልፃል።
"አብዛኛውን ጊዜ በዘራፊዎች የሚዘጉት እነዚህ ሁለቱ መንገዶች ከሀረር ወደ ዘይላ የሚያመሩ ሲሆኑ ፣ አንደኛው
ከከተማው በስተሰሜን በኩል ያለውን ሸለቆ አቋርጦ በጋለዴሳ ወንዝ መተላለፊያና ሸለቆ ውስጥ በማለፍ ወደ አዋሽ ተፋሰስ ይወርድና ከዚ ቦታ በመነሳት በኢሳ ግዛት በኩል ወደ ደቡብ
አቅጣጫ በሚታዩት እና እንደሰንሰለት በተያያዙ አለታዊ አካባቢዎች በኩል ወደ ባሕሩ ይገባል ።
ሌላው እና የበለጠ ቀጥተኛ ግን የበለጠ ወጣ ገባ መንገድ የጋዲቡርሲስን ወይም የጉዳቡርሲስን ሀገር አቋርጦ በሰሜን-ምስራቅ በሚገኘው ወደ ዳርሚ ይገባል ።
ዘይላ ከተማ በጋዲቡርሲ ጎሳ በተከበበ የባህር ዳርቻ ላይ ካለ ደሴቶች እና ኮረብታዎች በስተደቡብ የምትገኝ ሲሆን በደሴቷም ሁለት ወደቦች አሏት ፣ ከነዚህም አንደኛው በጀልባ መንቀሳቀስ የሚያስችል ነገር ግን ለመርከብ መጓጓዣ የማይመች ሲሆን ሁለተኛው ከከተማው በስተደቡብ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን ይህ ወደብ
ምንም እንኳን በጣም ጠባብ ቢሆንም ከ 26 እስከ 33 ጫማ ጥልቀት ያለው እና ለትልልቅ የመጓጓዣ ጀልባዎች አስተማማኝ የወደብ ግልጋሎት ያቀርባል."[27]
ውድቀት
ለማስተካከልከ1900 እስከ 1920 ባለው ጊዜ ውስጥ በሐረር ወደ ገበያ በሚወስደው መንገድ ላይ ያለ ትዕይንት
የአሚር ኑር ሞትን ተከትሎ በሀረር ላይ የሀብት እና የስልጣን ማሽቆልቆል ተከሰተ። ተከታዩ ገዥ እና የአህመድ
ግራኝ ዘመድ የነበሩት ኢማም ሙሀመድ ጃሳ በሌላኛ መጠሪያቸው ደግሞ አሕመድ ኢብኑ ኢብራሂም አል ጋዚ እየተባለ የሚታወቀው መሪ የኦሮሞ ወረራ እየጨመረ በመጣው ጫና በመሸነፍ ወንድሙን የሀረር ገዥ በማድረግ በ1577 ከተማዋን ትቶ ወደ አውሳ ሄደ። አዲሱ የጦር ሰፈር ከኦሮሞ ወረራ የበለጠ ጥበቃ ማድረግ አለመቻሉ በወቅቱ አደገኛ እና አጎራባች የነበሩት የአፋር ህዝብ ቀልብ ስቦ በሐረር በኩል ወደ በባህር ወደብ የሚጓዙ መንገደኞች ላይ ጥቃት መፈጸም እንዲችሉ ምቹ ሁኔታ ተፈጠረላቸው፡፡ በቀጣዩ ክፍለ ዘመን የአውሳ ኢማምነት ውድቀትን ተከትሎ ሀረር በአሊ ኢብኑ ዳዑድ መሪነት ነፃነቷን አገኘች ፡፡ ይህ መሪ ከተማዋ በግብጽ ቁጥጥር ስር ከመሆኗ በፊት ከ1647 እስከ 1875 የገዛው ሥርወ መንግሥት መስራች ነው ። [28]
እ.ኤ.አ. በ1800ዎቹ አሚር አህመድ ሳልሳዊ ኢብን አቡበከር እናቱ (ሶማሊያዊው የጊሪ ጎሳ መሪ እህት) የሆነችው ወደ ዘይላ የሚወስደውን መንገድ መቆጣጠሯን ተከትሎ በተፈጠረ አለመግባባት ከዘይላ ወደብ የሚገቡ እና የሚላኩ ምርቶችን በሙሉ አቁሞ
በምትኩ በርበራን መረጡ። [29] ሪቻርድ ፍራንሲስ በርተን በርበራን እና ሀረር አካባቢን ተጉዞ ከጎበኘ ቡሀላ እንደገለጸው
በ1854 የሰማውን አንድ ታዋቂ ሀረሪ ደጋግሞ ተናግሯል፡- “በርበራ ላይ ለማዘዝ የሚሞክር የሀረርን ፂም በእጁ ይይዛል።." [30] በዚህ
ወቅት የሲዳማ እና የጉራጌ ባሮች በኩል የሚመጡ ምርቶች ወደ ባህር ዳርቻ የሚላኩ ጠቃሚ ምርቶች ነበሩ። [31]በሁለቱ ታሪካዊ ከተሞች መካከል ጉልህ ድርሻ ያለው የንግድ ልውውጥ የኢሳቅ ሱማሌ ጎሳ ነጋዴዎች ይቆጣጠሩት የነበረ ሲሆን በአለም አቀፍ ገበያ በርበራ ቡና ተብሎ በሚጠራው ታዋቂው የሐረሪ የቡና ፍሬ ንግድም ይካፈሉ ነበር። [32] ሐረር የብዙ የሶማሊያ ሊቃውንት መኖሪያ
ሀረር በአሚር አብዱልሻኩር ኢብኑ ዩሱፍ የግዛት ዘመን ያለማቋረጥ ይብዛም ይነስ ሳንቲሞችን ማተም የጀመረችበት ወቅት ነበር ። [25] ከንግሥናው የተረፉት ሳንቲሞች ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ፣ ከፍተኛ የብር ይዘት ያለው እና የጥሩ ቅብ
አጠቃቀምን የሚያንፀባርቁ ግልጽ ጽሑፎችን በአንድ ላይ የያዘ ነበር፡፡[25] በሙሐመድ ኢብኑ አሊ የግዛት ዘመን ንጉሱ የጎሳ ወንድሞቹ ላይ ያለውን ግዴታ ለመወጣት እንዲያስችለው ከፍተኛ መጠን የብረት ማእድን (Tin) ካለው ንጥረ ነገር የተዋቀረ አዲስ ሳንቲም አስተዋወቀ ። [25] አሮጌው ገንዘብ ያለው ማንኛውም ሰው በአዲሱ ዓይነት እንዲለውጥ ወስኗል። [25] መሐመድ ሙክታር በ1876 የግብፅ ጦር መኮንን ይህንን እንደ ትልቅ ማጭበርበር አውግዟል። [25] እ.ኤ.አ. በ 1883 አንድ ጀርመናዊ ተጓዥ ገንዘቡ ከመደበኛ እሴቱ አንድ አስረኛ እንኳን ዋጋ እንደሌለው ጽፏል። [25]
19 ኛው ክፍለ ዘመን
ለማስተካከልእ.ኤ.አ. በ1875 መሐመድ ራኡፍ ፓሻ ለሳይንሳዊ ጉዞ አመስሎ የግብፅን ጦር በመምራት ከዘይላ ወደ ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ መሀል
ገባ። እ.ኤ.አ ጥቅምት 11 ቀን 1875 ሐረርን ያዘ። [35]ራኡፍ ፓሻ በመጀመሪያ የሀረሪ ሳንቲሞችን ከስርጭት አግዶ እነዚህን ገንዘቦች በግብጽ ገንዘብ ለመተካት በማሰብ የተወሰኑ ናሙናዎችን ለምርመራ ወደ ካይሮ ልኳል። [25] ነገር ግን የግብፅ መንግስት ለዚህ በቂ ገንዘብ ማቅረብ ባለመቻሉ የሀረሪ ምንዛሪ ጥቅም ላይ እንዲውል መከረው። [25] ሆኖም የሐረሪ ማሃለቅ ዋጋ በፊት ከነበረበት ከ33 ወደ ማሪያ ቴሬዛ ታለር ከነበረው 300 መሀለቅ ወደ ዶላር በሚል ማሻሻያ ተደርጎበታል። [25] የሳንቲሞቹ የብር ይዘት ትንተና ከተጠናቀቀ በኋላ 311 ማሀለቅ ወደ ታለር ተቀይሯል። [25] በግብፅ አገዛዝ ዘመን (1875-1884), አርተር Rimbaud መሰረታቸውን በኤደን ውስጥ ያደረጉ የተመሰረቱ በርካታ የተለያዩ የንግድ ኩባንያዎች በአካባቢው ሥራ አስፈፃሚ ሆኖ በከተማው ውስጥ ይኖሩ ነበር . ገዳይ የሆነ በሽታ ወደ ፈረንሳይ እንዲመለስ
እስካስገደደው ድረስ በ1888 በቡና፣ በሙስክ እና በቆዳ መገበያየት ቀጠለ። መኖሪያው ነበር የሚባለው ቤት አሁን
ሙዚየም ሆኗል። [36]
እ.ኤ.አ. በ1885 ሀረር ነፃነቷን በአሚር አብዱላሂ አስመለሰች ፣ ይህ ግን ለሁለት አመታት እ.ኤ.አ. እስከ ጥር 9 ቀን 1887 ዓ.ም ብቻ የቆየ ሲሆን ለዚህም ምክኒያቱ በዘለቀው ጨለንቆ ጦርነት መሰረቱን በሸዋ ላይ ያደረገው እና እያደገ በመጣውን የኢትዮጵያን ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ሚኒልክ በጦርነቱ ድል በማድረጉ ነበር ። [37]
ሀረር ዘመናዊው የኢትዮጵያ መንግስት በዳግማዊ ምኒልክ ዘመን የመጀመሪያዎቹን ሳንቲሞች ያወጣበት ቦታ ሲሆን ይህም
በ1885 E.C. ( 1892 CE.) ነው። [25]
መጀመሪያ ከተማዋን አቋርጦ ለመሄድ ታስቦ በተጀመረው እና በፈረንሣይ የተገነባው የአዲስ አበባ ጅቡቲ የባቡር መስመር
ዝርጋታ የተጀመረው ፕሮጀክት ለወጪ ቁጠባ ሲባል መስመሩን በሰሜናዊ ተራሮች በኩል በሀረር እና አዋሽ ወንዝ መካከል እንዲያልፍ በመቀየሩ ምክኒያት ሐረር የንግድ ጠቀሜታዋን አጥታለች ። በዚህም ድሬዳዋ እ.ኤ.አ.በ1902 አዲሲቷ ሐረር ተብላ ተመሠረተች ።
እንግሊዞች ታሪካዊውን የሐረር-በርበራ የንግድ እንቅስቃሴን ለማጠናከር ሁለቱን ከተሞች በባቡር ማገናኘት የሚያስችል የባቡር መስመር ዝርጋታ ስራ ለመጀመር ያቀደ ቢሆንም ይህ ተነሳሽነት በፈረንሳይ እና በብሪታንያ መካከል ያለውን Entente Cordiale
ይጎዳል በሚል በፓርላማ ውድቅ ተደርጓል ። [38] ሀረርን ከሶማሌ ጠረፍ የሚያገናኙት የንግድ መስመሮች በሙሉ በሶማሌ እና በኦሮሞ ግዛቶች በኩል የሚያልፍ ሲሆን በነዚ ግዞቶች ውስጥ ባሉ የጋዳ ቡርሲ እና የኢሳ ንኡስ ጎሳዎች የሆኑ የዲር ጎሳ ማህበረሰቦች ንግዱን በብቸኝነት እንደተቆጣጠሩት በሐረርና በሐረሪዎች ታሪክ ላይ ተገልጿል ።
"በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የአሚሮች የስልጣን ወሰን በሀረር እና በአቅራቢያዋ ብቻ ተወስኖ
የነበረ ሲሆን ወደ ባህር ዳር የሚወስደው የንግድ መስመር በሙሉ በኦሮሞ እና በሶማሌ ግዛቶች
በኩል ያልፋል። በመሆኑም የነበረው የንግድ አማራጭ በሁለት መንገዶች መጠቀም ሲሆን አንደኛው በሶማሌ ኢሳ እና በኖሌ ኦሮሞ ግዛቶች በኩል ያለው ጃልዴሳ መስመር ሲሆን ሌላው በገዳ ቡርሲ ግዛት አልፎ የሚገኘው የዳርሚ መንገድ በመሆኑ እና የንግዱን መስመር ሶማሌዎች በሞኖፖል በመያዛቸው ምክኒያት በዚ መስመር የሚጓጓዙ ነጋዴዎቹ የሁሉም አይነት እንግልትና ዝርፊያ ሰለባ ሆነዋል።... ነጋዴዎቹን በበላይነት እንዲቆጣጠሩ ለአባንሶች (የካራቫን ጠባቂ ወኪሎች ) ማለትም ከወደቡ ጠረፍ ላይ የሚገኙት የኢሳ ወይም ገደ ቡርሲ ጎሳ አካል የሆኑ እና በግዛቱ ውስጠኛው ክልል የሚገኙት የጃርሶ ጎሳዎች በአደራ ተሰጥቶታል። [39]
እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ
ለማስተካከልበሐረር የሚገኝ ባህላዊ ቤት በእስላማዊ ካሊግራፊ ያጌጠ።
የሐረረ ባህላዊ ቤት (ጌይ ጋር) ሐረር በማርሻል ሮዶልፎ ግራዚያኒ መሪነት በጣሊያን ወታደሮች ተያዘች ግንቦት 8 ቀን [40] የአንግሎ ኢትዮጵያ ስምምነት እኤአ በ1944 መጠናቀቁን ተከትሎ ምንም እንኳን እንግሊዞች ሀርጌሳ ላይ የነበረውን ሂደት ወደ ኢትዮጵያዊ ለመመለስ ፈቃደኛ ባይሆኑም የእንግሊዝ መንግስት በሐረር ቆንስላ እንዲመሰርት ፍቃድ ተሰጠው፡፡ የብሪታንያ መንግስት በሃውድ ውስጥ የ1954ቱን የለንደን ስምምነት የሚጥስ እንቅስቃሴዎችን በተደጋጋሚ እንደሚፈጽም የቀረበበት ሪፖርት ተከትሎ እኤአ መጋቢት 1960 የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆንስላ ጽ/ቤቱ እንዲዘጋ አዘዘ። [41]
በአቢሲኒያ የጥበቃውን የውስጥ ክፍል በቀላሉ ተደራሽ ለማድረግ እና በተመሳሳይ ንግድ አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችል ከበርበራ እስከ ሀረር የሚዘረጋ የባቡር ሀዲድ መስመር ዝርጋታ ለማከናወን ሀሳብ ቢቀርብም ከጅቡቲ እስከ አዲስ አበባ ካለው የፈረንሳይ የባቡር መስመር ጋር መወዳደር ደካማ ፖሊሲ ይሆናል በሚል ሀሳቡ ውድቅ ሆኗል። [42]
እ.ኤ.አ. በ1995 ከተማዋ እና አካባቢዋ በራሱ መብት የኢትዮጵያ ክልል (ወይም ክልል ) ሆነ ። ከድሬዳዋ ወደ ከተማዋ ውሃ
ለማድረስ የሚያስችል የቧንቧ መስመር በመገንባት ለመስራት ተሞክፘል።[43]
ባህል
ለማስተካከልእንደ ሰር ሪቻርድ በርተን ዘገባ መሰረት ሀረር የጫት ተክል መገኛ ነች።[44] የመጀመሪያው የቤት ውስጥ የቡና ተክልም የሐረር ነበር
ተብሏል።
የአየር ንብረት
ለማስተካከልዓመቱን በሙሉ፣ የከሰዓት በኋላ የአየር ሙቀት በጣም ሞቃት ሲሆን ጥዋት ደግሞ ቀዝቃዛ እስከ መለስተኛ ቅዝቃዜ ሲኖር ዝናብ
በማርች እና ኦክቶበር መካከል መጠነኛ ዝናብ ሲኖር ኦገስት ከፍተኛ ዝናብ ያገኛል ቀሪው ወራት ማለትም ከኖቬምበር እስከ ፌብሩዋሪ ብዙ ጊዜ ደረቃማ የአየር ሁኔታ ይኖራል።
የሐረር የአየር ንብረት መረጃ | |||||||||||||
---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|
ወር | ጥር | የካቲት | መጋቢት | ሚያዚያ | ግንቦት | ሰኔ | ሀምሌ | ነሐሴ | መስከረም | ጥቅምት | ህዳር | ታህሳስ | አመት |
አማካይ ከፍተኛ °C (°F) | 25.3
(77.5) |
26.3
(79.3) |
27.1
(80.8) |
26.9
(80.4) |
27.0
(80.6) |
25.5
(77.9) |
23.8
(74.8) |
22.6
(72.7) |
23.9
(75.0) |
26.1
(79.0) |
25.8
(78.4) |
25.8
(78.4) |
25.5
(77.9) |
አማካይ ዝቅተኛ °C (°F) | 11.9
(53.4) |
12.9
(55.2) |
13.7
(56.7) |
14.5
(58.1) |
14.6
(58.3) |
14.1
(57.4) |
14.0
(57.2) |
13.6
(56.5) |
13.5
(56.3) |
13.1
(55.6) |
12.1
(53.8) |
12.0
(53.6) |
13.3
(56.0) |
አማካይ የዝናብ መጠን ሚሜ (ኢንች) | 17
(0.7) |
20
(0.8) |
57
(2.2) |
84
(3.3) |
91
(3.6) |
68
(2.7) |
99
(3.9) |
126
(5.0) |
94
(3.7) |
49
(1.9) |
12
(0.5) |
6
(0.2) |
723
(28.5) |
ምንጭ፡- የአየር ንብረት-ውሂብ[45] |
የስነ ሕዝብ አወቃቀር
ለማስተካከልየሶማሊያ የገሪ ፣ ኢሳ ፣ ካራንሌ ሃዊያ እና በርተሪ ጂድዋክ ማህበረሰቦችን የሚያሳይ የድሮ የሀረር ካርታ ።
በ Central Statistical Agency of Ethiopia (CSA) አስተባባሪነት እኤአ በ 2007 በተደረገው ብሄራዊ የህዝብ ቆጠራ መሰረት አ የሐረር ከተማ ሕዝብ ቁጥር 99,368 ሲሆን ከዚህ ውስጥ 49,727 ወንድ እና 49,641 ሴቶች ናቸው። [1] ፡ 7 በሐረር
ከተዘገቡት ስድስት ትላልቅ ብሔረሰቦች ውስጥ አማራ (40.55%)፣ ኦሮሞ (28.14%)፣ ሐረሪ (11.83%)፣ ጉራጌ (7.94%)፣
ሶማሌ (6.82%) እና ትግራውያን ( 2.76%); ከ2 በመቶ በታች ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦችን ያቀፉ ናቸው። [1] : 23
አማርኛ በ 49.2% የከተማው ነዋሪ የመጀመሪያ ቋንቋ ሲሆን እንግሊዘኛ 23.7% ይነገር ነበር።ሀረሪ በ12.2%፣ ሶማሌ
በ6.6 በመቶ [1] ፡ 25 ብዙሃኑ የከተማ ነዋሪዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ነን የሚሉ ሲሆን 48.54%
የሚሆነው ህዝብ ያንን እምነት እንደሚከተል ሲገልጽ 44.56% የሚሆነው ህዝብ ሙስሊም ነኝ ሲል 6.14% ፕሮቴስታንት
ነው። [1] ፡ 28 [46]
ብሄር
ለማስተካከልባርከር ሃይንስ በ1840 እንደዘገበው አብዛኛው የሀረር ህዝብ ሀረሪዎች ቢሆንም ጥቂት ኦሮሞ ፣ አፋር ፣ ሶማሌ ኢሳ እና
የየመን አረብ ነጋዴዎችም አሉበት። [47] በ1855 ሪቻርድ ፍራንሲስ በርተን ሐረርን ወደ 8,000 የሚጠጉ ነዋሪዎች
እንዳሏት እና ከነዚህም 3,000 በደዊስ (ዘላኖች) 2,500 ሀረሪዎች እና 2,500 ሱማሌዎች በማለት ገልጿል፡፡ [48]በርተን ወደ ከተማው የሚያመራ ትልቅ የኦሮሞ ህዝብ መያዙን ዘግቧል።[49] በግብፅ Khedivate የሐረርን ኢሚሬትስ ወረራ ውስጥ ባደረገው ጉብኝት ወቅት ሐረር ኢሚሬትስ ተመራማሪ ፖልቲሽኬ ሐረርን ወደ 40,000 የሚጠጉ ነዋሪዎች እንዳሏት ሲገልጹ ከእነዚህ ውስጥ 25,000 የሚሆኑት ሐረሪዎች፣ 6,000 ኦሮሞዎች፣ 5,000 ሶማሌዎች፣ 3,000 አቢሲኒያውያን እና ጥቂት አውሮፓውያን እና እስያውያን ናቸው። [50]
የኢትዮጵያ ኢምፓየር የሐረርን ኢምሬትስ ድል ካደረገ በኋላ የዐማራ ፍልሰት በሐረር እና አካባቢዋ ሰፈረ ። [51] ልጅ እያሱ
በአቢሲኒያ ታጣቂዎች ከስልጣን መወገዱን ተከትሎ የከተማው የሶማሌ ህዝብ ተበታትኗል። [52] የሀረሪ ተወላጆች
በሃይለስላሴ መንግስት ብሄር ተኮር ጭፍጨፋ ምክንያት በአንድ ወቅት ጁገል ግንብ በታጠረው ከተማ ውስጥ በብዛት ይኖሩ የነበሩት
ቁጥራቸው ከ15% በታች ሊወርድ ችሏል ። [53][54][55] በኢትዮጵያ አገዛዝ በደረሰው ጭቆና ምክንያት በ1970ዎቹ መጨረሻ በአዲስ አበባ የሚኖሩ ሀረሪዎች በሐረር ከተማ ከነበሩት ይበልጣሉ። [56]እንደ ፊነር ገለጻ፣ የሐረሪ ብሄረሰቦች በ1948 ዓ.ም ከነበረው የግዛት ርምጃ ቀድሞ የነበራቸውን የህዝብ ብዛት እስካሁን እንዲያገግም አላስቻላቸውም። [57]
በሐረር ዙሪያ ያሉ የሶማሌ ጎሳዎች በዋናነት ከጋዳቡርሲ እና ከኢሳ ከድር እና ከቀራንሌ የሐዊያ ንዑስ ጎሣዎች የተውጣጡ ናቸው ። በክልሉ ውስጥ ለረዥም ጊዜ የኖሩትን እና ታዋቂ የሶማሌ ጎሳዎችን ይወክላሉ። [58] የገሪ እና የጅድዋቅ የዳሮድ ጎሳዎችም በሐረር አቅራቢያ ባሉ አካባቢዎች ይኖራሉ። የገዳቡርሲ እና የገሪ ሱማሌዎች ከከተማው በስተሰሜን እና በሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ ወረሩ። እኤአ በ (1856) ሪቻርድ ፍራንሲስ በርተን የገዳቡርሲ እና የገሪ ሶማሌ ጎሳዎች በሐረር ዙሪያ እና በሀረር ውስጥ ግዛታቸውን እንዳስፋፉ ይገልጻል። [59][60] ኢሳ እና ካራንሌ ሃዊስ ወደ ሰሜን እና ሰሜን ምዕራብ አካባቢ ላይ ጥቃት ሲሰነዝር ጂድዋክ ደግሞ ወደ ምስራቅ አቅጣጫ ጥቃት አካሄዱ። [61][62] IM Lewis (1998) እንዲህ ይላል፡-
"በሀረር እና በድሬዳዋ ዙሪያ በተካተቱት መሬቶች ውስጥ የኢሳ እና ገደቡርሲ ጎሳ የሆኑ ሶማሌዎች በመኖሪያነት ተገልግለውበታል፡፡" [63]
የከተማ አቀማመጥ
ለማስተካከልየድሮዋ በግንብ የተከበበችው የሀረር ከተማ በ5 በሮች የተከፈለች ሲሆን እነሱም ፤ አሱም በሪ፣ አርጎብ በሪ፣ ሱቁታት በሪ፣ በድሮ ባሪ እና አስማዲን በሪ በመባል ይጠራሉ ። [12] ከዚያም እነዚህ በሮች ብዙውን ጊዜ በሙስሊም ቤተ መቅደስ ስም ወይም በአካባቢው ምልክት ሆኖ በሚያገለግል ታዋቂ ዛፍ ስም እንደሚጠሩበት ሁሉ ቶያ በሚል ሰፈሮች ይሰየማሉ። [12] እንደ ኤስአር ዋልድሮን እ.ኤ.አ. በ1975 አካባቢ 59 ያክል የሚደርሱ እንደዚህ ያሉ ሰፈሮች ነበሩ። [65]
እ.ኤ.አ. በ 1960 ዎቹ መገባደጃ ላይ በከተማው (ጁገል) ግንብ ዙሪያዋን አንድ ሰአት በሚፈጅ ጊዜ ውስጥ በእግር ጉዞ ማድረግ ይቻል ነበር ። [65] በ1980ዎቹ መጀመሪያ ላይ ግን ከከተማዋ መስፋፈት ጋር በተያያዘ ህገወጥ ግንባታ በግንቡ ዙሪያ እና ከግንቡ ጋር የተጣብቆ ቤቶች በመገንባታቸው ምክኒያት ከላይ በተጠቀሰው መንገድ የእግር ጉዞ ማድረግ አልቻለም ። [65]
ባህላዊ ቤቶች
ለማስተካከልጌይጋር ("ከተማ ቤት"፣ ብዙ ቤቶች (ጋይ ጋራች ) በመባል የሚታወቀው የሐረሪ ቤቶች ከሌሎች የሙስሊም ክልሎች እና
ከሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚለይ አርክቴክት ናቸው። [66] የሐረሪ ባህላዊ የቤት ዲዛይን ዛሬም በስፋት ጥቅም ላይ
እየዋለ ሲሆን መጠነኛ ለውጦች ብቻ የታዩ ሲሆን ወደ ሌሎች ከተሞች የሄዱ ሐረሪዎችም ተመሳሳይ ዘይቤን ለመከተል
ይሞክራሉ። [65] ሀረሪዎች በቤታቸው ትልቅ ኩራት ይሰማቸዋል እና የሀረሪ ባህል ወሳኝ አካል ናቸው። [66]
በግድግዳ የተሸፈነ ጊቢ ( አባት ) ብዙ መኖሪያዎችን ያቀፈ ነው, እነሱ ተመሳሳይ ግድግዳዎች የሚጋሩ ግን እርስ በርስ
የተያያዙ አይደሉም. [65]ቤቶቹ በግቢው ዙሪያ የተደረደሩ ሲሆን አብዛኞቹ መስኮቶች ከመንገድ ይልቅ ወደ ግቢው እንዲያመለክቱ ተደርገው የተገነቡ ናቸው።
[65] ለግለሰብ መኖሪያ በሮች ሁል ጊዜ ወደ ምስራቅ ወይም ወደ ምዕራብ ያመለክታሉ ። ወደ ሰሜን ወይም ወደ ደቡብ
የሚመለከቱ በሮች ብርቅ ናቸው። [66] እንደ ካቢር አብዱልሙሃይመን አብዱልናሲር ገለጻ፣ ገበሬዎች እና ነጋዴዎች ብዙውን
ጊዜ ወደ ምስራቅ አቅጣጫ የሚሄዱ በሮች ስላሏቸው ለስራ ቀድመው መነሳት ይችላሉ። [66] በአንድ ግቢ ውስጥ
የሚኖሩት በርካታ ቤተሰቦች አንድ ወይም ሁለት ኩሽናዎችን ይጋራሉ ፣ እነዚህም ከመኖሪያ ቤቶቹ የተቋረጡ ናቸው።
[65]በጊቢዎች ዙሪያ ያሉት ግድግዳዎች በመሠረቱ ቀጣይነት እንዲኖራቸው ይጣመራሉ. [65] ወደ ጎዳናው የሚመለከተው
የውጨኛው በር ብዙውን ጊዜ ከእንጨት የተሠራ ነው ፣ ግን አንዳንድ ጊዜ በብረት የተሰራ ሊኖር ይችላል እነዚ በሮች ቀለም የተቀቡ ወይም በነጭ ኖራ የተዋቡ ናቸው። [65] ግድግዳዎቹ በዙሪያቸው architrave ይሠራሉ። [65]
አንዳንድ ጊዜ ብዙ ጊቢዎች ወደ ሌላ "ብሎክ" ጊቢዎች ጋር ይቀላቀላሉ, ሁሉም በአንድ ግድግዳ የተከበቡ እና ከዚያም በዙሪያቸው
የራሳቸው ግድግዳዎች ይኖራቸዋል. [65] እነዚህ በጊቢ ውስጥ ሌላ ጊቢ "ብሎኮች" የተገነቡበት ምክኒያት አንድ እንግዳ ወይም ጎብኚ ሁለተኛው ጊቢ ከመድረሱ በፊት የመጀመሪያውን ግቢ እንዲያልፍ እና ወዘተ.በሚል እሳቤ ነው
የግንባታ እቃዎች የአገር ውስጥ ድንጋይ ናቸው, የተቀጠቀጠ ድንጋይ እና የሸክላ ድብልቅ እንደ ሞርታር እና ፕላስተር
ሲሆኑ እነዚህ ግብአቶች ግድግዳዎቹ ነጭ ኖራ ከመቀባታቸው በፊት ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡ [65] ይህ አሰራር በአዲሶችም ሆነ በአሮጌ ቤቶች ውስጥ አሁንም የሚሰራበት አካሄድ ነው። [65]
የተለመደው የሀረሪ ቤት የወለል ፕላን አራት ማዕዘን ነው። [65] ዋናው ክፍል ጊዲር ጋር ወይም ጋር ኤቀድ የሚባል ትልቅ
ሳሎን ነው ። [65] ጊዲር ጋር እንደ መቀመጫ ወይም አልጋ የሚያገለግሉ ነደባ(መደብ) የሚባሉ በርካታ ከፍ ያሉ መድረኮች
አሉት። [65] የተለመደው ቤት አምስት ነደባ(መደብ) ይኖረዋል። [65] በ ጊዲር ጋር ጀርባ፣ ከፊት ለፊት ባለው በር በኩል፣ ሁለት
ናዳባዎች አሉ፡- “ትንሹ” ወይም ጢት ነዳባ ፣ እና ከኋላው ደግሞ “ትልቅ” ወይም ጊዲር ነደባ, እሱም በመጠኑ ከፍ ያለ
ነው። . [65] እነዚህ ሁለቱ ትልልቅ ነደባዎች (መደቦች) ናቸው። [66]ጫማዎች እስከ ጢት ነዳባ ድረስ ሊለበሱ ይችላሉ, ነገር ግን ያ ቦታን ካለፈ ቡሀላ ጫማዎቹ መውለቅ አለባቸው. [65] ጢት ነዳባ ትናንሽ ሰዎች ወይም ደረጃቸው ዝቅ ያለ አዋቂዎች የሚቀመጡበት ነው። [66]ልጆችም በዚህ ነደባ ላይ ይተኛሉ። [66] በታሪክ እንደተጠቀሰው በአሚሩ(ንጉሱ) ፍርድ ቤት ውስጥ የከሳሾች ወይም የተከሳሾች መቀመጫ ሆኖ አገልግሏል። [66] ጊዲር ነደባ, ሽማግሌዎችን እና በይበልጥ ከፍተኛ የሚባሉ ሰዎችን ያስቀምጣል። [66] ከታሪክ አኳያ፣በአሚሩ ቤተ መንግሥት፣ ታላላቅ ሰዎች እዚህ ተቀምጠዋል። [66] አንድ ሰው ሲሞት ሰውነቱ በአክብሮት ከመቀበሩ በፊት
በጊዲር ነደባ ላይ ይቀመጣል። [66] ጊዲር ነደባ, ውስጥ ገንዳ ተቆፍሮ በውሃ ተሞልቶ ገላውን ለማጠብ ይጠቅማል
ከዚያም ገንዳው እንደገና ይሞላል።[66]
አሚር ነደባ ወይም የክብር መደብ ለቤቱ ጌታ እና ለተከበሩ እንግዶች ማረፊያ የተከለለ ነው ሲሆን የመደቡ አቀማመጥ እንደ ቤቱ አሰራር ሁኔታ በግራም ሆነ በቀኝ በኩል ሊሆን ይችላል፡፡ [65] የዚ መደብ አቀማመጥ የቤተሰቡ አስተዳዳሪ ወደ ቤቱ የሚገባውም ሆነ የሚወጣውን ሰው በንቃት እንዲከታተል እና እንዳመጣጡ ምላሽ ለመስጠት እንዲያስችለው ታስቦ የተገነባ ነው። [66]
"የተደበቀው" መደብ ወይም ሱትሪ ነደባ አቀማመጡ በሁለቱም አቅጣጫ በኩል ሊሆን ይችላል ነገር ግን ሁልጊዜ ከሚወጣው ምሰሶ
ወይም መኸዙ በስተጀርባ ነው . [65] ከታሪክ አንጻር ይህ " ማላሳይ ናዳባ" በመባል ይታወቃል ምክንያቱም የአሚሩ
ጠባቂዎች በስብሰባ ወይም በፍርድ ቤት ጉዳዮች ላይ እዚህ ይቀመጣሉ. [66] ሱትሪ ናዳባ ለመተኛት ያገለግላል።
[65]በተጨማሪም ባል ወደ ቤት ሲመጣ የሚያርፍበት መቀመጫ ሆኖ ያገለግላል. [66] በመጨረሻ፣ ገብቲ ኤሄር ነደባ
ወይም ከመግቢያው በር በስተጀርባ ያለው ነው። [65] እንደ አሚር እና ሱትሪ ነደባዎች ሁሉ አቀማመጡ በግራም ሆነ በቀኝ ሊሆን
ይችላል። [65] በኋለኛው ማዕዘኖች አንዳንድ ጊዜ ነደባ ዴራ የሚባሉ ቁም ሣጥኖች ወይም የእቃ ሣጥኖች(ብፌ) አሉ። [65]
ጥሬ ገንዘብ [66] እና ጠቃሚ ሰነዶች በነደባ ዴራ በሚቀመጥ ሳጥን ውስጥ ይቀመጣሉ። [65] የ ነደባ ዴራ የላይኛው
ክፍል የቤቱን ጌታ ልብስ ለማከማቸት ያገለግላል። [66]
ጊዲር ጋር የግል ንብረቶችን ለማከማቸት እና ለማሳየት የሚያገለግሉ ጣቄት የሚባሉ ከግድግዳው ገባ ብለው በተገነባ አግባብ የተሰራ ነው ። [65] [12] እነዚ ጣቄቶች ከፍ ብለው የተገነቡ ሲሆን በተለምዶ በቁጥር 11 ሲሆኑ 5ቱ በበሩ ፊት ለፊት ባለው ዋናው ግድግዳ ላይ፣ የተቀሩት 4ቱ ደግሞ በሌሎች ግድግዳዎች ላይ ይሆናሉ ። [65] በዋናው ግድግዳ መካከል ያሉት ሁለቱ አራት ማዕዘን ቅርፆች (ኤቀድ ጣቄት) ሲባሉ አነዚህ በተለምዶ መጽሐፍትን በተለይም ቁርአንን ለማከማቸት ያገለግላሉ ። [65] አራት ማዕዘን ቅርጻቸው ሞትን እና መቃብርን ለማስታወስ የተሰራ ነው ተብሎ ይታሰባል። [65] ከ 11 ዋና ዋና የጣቄቶች ቦታ በተጨማሪ አንዳንድ ጊዜ በነደባ(በመደቦች) አካባቢ ጫማዎችን ወይም የእጣን ማጨሻ ምድጃን(ጊርጊራ) ለማስቀመጥ ታስበው የተዘጋጁ ቦታዎች አሉ ። [65]
ከመግቢያው በሁለቱም በኩል ወደ ኪርተትት የሚወስድ ክፍት የበር መንገድ አለ ፣ እሱም ዝቅተኛ ጣሪያ ያለው የጎን ክፍል እና
የራሱ የሆነ ነዳባ(መደብ) አለው። [65] በኪርት እና በጊዲር ጋር መካከል ያለው ግድግዳ አንዳንድ ጊዜ በእንጨት ያጌጠ እና በመስታወት የተሸፈነ መስኮት ይኖረዋል። [65] ሴቶች ብዙ ጊዜ ኪርተት ውስጥ የሚቆዩት ወንዶች የበርጫ ( ጫት ለመቃም ሲሰባሰቡ )
ፕሮግራም ሲኖራቸው ነው። [65] ድሮ ኪርተቱ አንዲት ወጣት ሙሽሪት ከሠርጓ በኋላ ለ 8 ወራት ለብቻዋ የምትኖርባት ስፍራ ነበረች። [65] እንደዚያ በሆነ የሙሽርና ጊዜ ወደ የኪርተቱ መግቢያ በር የሌለው በመሆኑ በቀርከሃ መስኮት እና በመጋረጃ ይሸፈናል። [65]
ዝቅተኛ ጣሪያ ያለው ሁለተኛ የጎን ክፍል ዴራ የሚባል ሲሆን , ከ ኪርተት ጋር በአነስተኛ በር በኩል ይገናኛል. [65] ይህ ክፍል ለአይጦች ጥቃት የማይጋለጡ እቃዎችን ለማከማቸት ያገለግላል . [65] ከበሩ ቀጥሎ ባሉት የዴራ ግድግዳ ላይ አፍላላዎች (በጥቁር ሸክላ የተሰሩ እና ረጅም አንገት ያላቸው) የሚቀመጡበት ልዩ ቦታ ነው ። [65]ለእነዚህ አፍላላዎች መክደኛነት የሚያገለግሉ አፍላላ ኡፋ የሚባሉ ረዣዥም የቅርጫት ክዳን አላቸው ። [65] እቃዎቹም የቤተሰቡን ጌጣጌጥ እና ሌሎች ውድ ዕቃዎችን እንዲሁም የቤተሰቡን ልጆች እምብርት ለማከማቸት ያገለግላሉ . [65]የሐረሪ ባህል ሙዚየም ኃላፊ ወይዘሮ ፈትያ አህመድ እንደተናገሩት የአፍላላው ክዳን ተገልብጦ ከተከደነ የቤቱ አባወራ መሞቱን እና በቤቱ ውስጥ የሟች ባለቤት ብቻ እንዳለች ያሳያል። [66]
ዴራ የግል ቦታ ሲሆን ባል እና ሚስት ልጆቻቸው መስማት የሌለባቸውን ሚስጢራዊ ጉዳይ የሚወያዩበት ቦታ ነው። [66] እድሜያቸው ከ3 እስከ 7 ያሉ ህጻናት እድሜያቸው 7 አመት ሞልቶ ሙሉ ቀን መጾም ከመጀመራቸው በፊት መጾም ግዴታ ስለሌለባቸው በጾም ሰአት መብላት ሲፈልጉ ከህብረተሰቡ እይታ ውጪ ሆነው ለመብላት ሲፈልጉ ይህንን ክፍል ይጠቀሙበታል። ይህ ክፍል ለተሻለ
አየር ማናፈሻ እንዲረዳ ተብሎ በውስጡ ክፍተቶች ባሉት ቀለል ባለ የዲንጋይ አይነት እና ያለሲሚንቶ የተገነባ ነው፡፡ [66]
ከጊዲር ጋር በላይ ያለው ጣሪያ ወደ ቤቱ ሙሉ ቁመት ይወጣል. [65] ከጎን ክፍሎቹ በላይ ግን ቀላ(ፎቅ) የሚባል የላይኛው ደረጃ
አለ ። [65] በመጀመሪያ፣ ቀላ በዋነኛነት ለመጋዘንነት እና አንዳንዴም እንደ መኝታ ቦታ ሲያገለግል አሰራሩ በምንም መልኩ
ከጊዲር ጋር አይለያይም። [65] ከ 19 ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ጀምሮ ግን፣ ሁለቱን (ጊዲር ጋር እና ቀላ(ፎቅ)) በእንጨት በተሰራ ወንፊታማ መስኮት እንዲለያዩ በመደረጉ ቀላ(ፎቁ) ምንም እነኳን በጊዲር ጋር ውስጥ እንደሚገኙት ነደባ(መደብ) ብዙ ክፍሎች እና ሌሎች ጌጦች ባይኖረውም በመሠረቱ የተለየ ሁለተኛ ፎቅ ሆኗል ፡፡ [65] ወደ ቀላ የሚወስደው መወጣጫ ብዙውን ጊዜ ከ 6 እስከ 9 ደረጃዎችን ይይዛል። [65] በዘመኑ የሚገነቡት አዲሶቹ ባህላዊ ቤቶች ውስጥ የቀላው መወጣጫ የተቀረጸ የእንጨት መደገፊያ(banister) ሲኖረው በአሮጌ ቤቶች ውስጥ ግን ይህ አልነበረውም.[65]
የቤቱ ጣራዎች በባህላዊ መንገድ የሚሠሩት ቅርፊታቸው ከተገፈፈ ቀጭን የዛፍ ግንድ ነው። [65] ዛሬ ጣሪያው
ከተቀረው ቤት ጋር በነጭ ኖራ ተቀብቷል። [65] ከጢት ነዳባ ጠርዝ በላይ የሚገኘው አንድ ምሰሶ ሃሚል ይባላል ; ዛሬ የኤሌክትሪክ
መብራትን ለማንጠልጠል ጥቅም ላይ ይውላል, ነገር ግን በጥንት ጊዜ ሰዎች የሰጎን እንቁላል ይሰቅሉበት ነበር ምክንያቱም
ይህን ማድረጉ ቤቱን ከመብረቅ ይከላከላል ተብሎ ስለሚታመን ነው. [65] በአሁኑ ጊዜ ጣራዎቹ በትልቅ መጠኑ እና በተለየ ቅርጹ ጎልቶ ከሚታየው ሀሚል እና በቫርኒሽ በተሠሩ የእንጨት ጣውላዎች የተሠሩ ናቸው፡፡ [65]
ፎቆች በተለምዶ ቄህ አፈር( ቀይ አፈር) የተሠሩ ናቸው እና በንጣፎች ወይም ምንጣፎች ያልተሸፈኑ የነደባ
ክፍሎች ቀይ ቀለም የተቀቡ ናቸው። [65] ዛሬ እነሱ ብዙውን ጊዜ ንጣፍ ይደረጋሉ፣ ብዙውን ጊዜ ቢያንስ የተወሰነ ቀይ ስጦታ
አላቸው። [65] ቀይ ቀለም በጨለንቆ ጦርነት ላይ የፈሰሰውን ደም የሚያስታውስ ነው . [65]
አንዳንድ ቤቶች ቲት ጋር ወይም "ትንሽ ቤት" ይኖራቸዋል፣ እሱም የተለየ መግቢያ እና የራሱ ነደባ አለው ። [65] ጢት ጋር ብዙ ጊዜ ከዋናው ቤት ጋር ግንኙነት የለውም። [65] በጉርምስና እድሜ ክልል ላሉ የቤተሰብ አባላት ጥቅም ላይ ይውላል፣ ወይም አንዳንድ
ጊዜ ይከራያል። [65] ከ 20 ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ አንዳንድ ቤቶች ከጢት ጋር በላይ ሌላ ደረጃ ይጨምሩ እና
ከቀላ ጋር ያገናኙት እንዲሁም በቤቱ ውጭ ባለው ደረጃ በኩል የተለየ መግቢያ ይሰጡታል። [65]
እያንዳንዱ ግቢ ለአራሾች ወይም ለቤት ሰራተኞች የሚያገለግል የጎን ክፍሎች እና ነደባ የሌለው የተለየ ይኖረዋል፡፡ [65]
የላሞች እና የአህዮች በረትም ይኖራል። [65] በተጨማሪም በግቢው በአንደኛው ክፍል በኩል ከቤቶቹ ጋር
ያልተገናኙ አንድ ወይም ሁለት "የኩሽና ቤቶች" ይገኛሉ፡፡ [65] እነዚህ ኩሽናዎች ምንም መስኮት የላቸውም፣ ጭስ በበሩ
ውስጥ ስለሚወጣ በመጨረሻ ግድግዳዎቹ በጥላሸት ይሸፈናሉ ። [65] ከዛፍ ግንድ የተሰሩ መደርደሪያዎች የወጥ ቤት
እቃዎችን ለማስቀመጥ ያገለግላሉ። [65]
ድሮ የሐረሪ ቤቶች ብዙ የቤት ዕቃ አይኖራቸውም ነበር። [65] ከ20ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ቀላል የምዕራባውያን አይነት
የእንጨት ወንበሮች እየተስፋፉ መጥተዋል እንዲሁም የብረት አልጋዎች ከነፍራሻቸው በሱትሪ ነደባ ላይ ተቀምጠዋል። [65]
ሪቻርድ ፍራንሲስ በርተን የአሚሩን ቤት በ1800ዎቹ በጎበኙበት ወቅት የውጪው ክፍል በኖራ የተለበጠ ብቸኛው ህንጻ መሆኑን ገልጿል ይህ የሚያመለክተው አብዛኛው ህንፃዎች ያልተጌጡ መሆናቸውን ነው። [65] በተመሳሳይ መልኩ በ1935
ዓ.ም መገባደጃ ላይ አብዛኞቹ ቤቶች ያልተቀቡም ሆነ በኖራ ያልተለበጡ ተብለው ተገልጸዋል ። በአሁኑ ሰአት አብዛኛው የሀረሪ ማህበረሰብ በአመት ቢያንስ አንድ ወይም ሁለት ጊዜ ለረመዳን(Ramadan) እና ከአረፋ(Aräfa) በዓል መዳረሻ ነጪህ አፈር (ነጭ አፈር) ከሚባል የኖራ ድብልቅ ቤታቸውን በመቀባት ይስጌጣሉ ። [65] የቤት እቃዎች እና ቅርጫቶች በተመሳሳይ ጊዜ በደንብ ይጸዳሉ. [65]ዛሬ, በኖራ ከመታጠብ ይልቅ, ግድግዳዎች አንዳንድ ጊዜ በዘይት ቀለም ይጠቀማሉ . [65] ምንም እንኳን አረንጓዴ በጣም ተወዳጅ ቢሆንም ይህ ማንኛውም ቀለም ሊሆን ይችላል.[65]
የቤት ውስጥ ማስጌጥ በተለምዶ በሴቶች ይከናወናል. [65] ነደባዎችን በምንጣፎች፣ እና ትራሶች ደርድረው ግድግዳውን
በሐረሪ ሴቶች በተሰፋ ቅርጫት ያስጌጡታል ። [65] ኤናሜል ሳህኖች እና ጎድጓዳ ሳህኖች እንዲሁ ግድግዳ
ላይ ዛሬ ተሰቅለዋል። [65] የጌጣጌጥ ቅርጫቶች በግድግዳው ትይዩ በጥንድ ጥንድ በማጣመር ይሰቀላሉ። [65]
እያንዳንዱ ቤተሰብ የራሱ የሆነ የማስዋብ ዘይቤ አለው፣ እና ለእንግድነት የሚመጡ ሴቶች ጌጣጌጦች እንዴት በግድግዳው ላይ ማስጌጥ ዙሪያ ላይ ብዙ ጊዜ አስተያየት ይሰጣሉ። [65] ወጣት ሴቶች ከትላልቅ ሴቶች ይልቅ ቤታቸውን ለማስጌጥ በጣም ፈጣን ናቸው እና
ወጣት ጥንዶች የቤታቸውን መደብ ወለል በቀይ አፈር የማስጌጥ ስራ በሳምንት አንድ ጊዜ ሲከውኑ ትልልቅ ሰዎች ግን በአመት ውስጥ ጥቂት ጊዜ ብቻ ያስጌጣሉ የሚል አስተሳሰብ አለ።[65]
ትልቁ የጌጣጌጥ ቅርጫቶች በሴቶች ስብሰባ ላይ ዳቦ እና ጣፋጭ ለማቅረብ የሚያገለግሉ ዓይነት ናቸው. [65] እነዚህ
ከላይ የተንጠለጠሉ እና የተደራረቡ ረጃጅም ሾጣጣ ክዳኖች አሏቸው። [65] በአንድ ወይም በሁለት ረድፎች ከጊዲር ነደባ
በስተኋላ ባለው ግድግዳ ላይ እና ከቦታዎቹ በታች የተንጠለጠሉ ናቸው፣ እና በተለምዶ እንደመተካኪያ የሚያገለግሉ ጥንዶች ናቸው። [65] በ ኤቀድ ጣቄት ባሉት ሁለት አራት ማዕዘን ቅርፆች መሀከል ላይ መፃህፍትን ለማከማቸት የሚያገለግሉ ሲሆን ፣
ሳህና ሰጋሪ በሚል መጠሪያ የሚታወቁት የስፌት አይነቶች መለያቸው ክዳን ያላቸው እና ቀጥ ያለ ርዝማኔ እንዲኖራቸው ተደርገው የሚሰሩ የቅርጫት አሉ። [65] እነዚህ ቅርጫቶች በሠርግ ወይም በቀብር ስነ ስርአት ላይ የቡና ፍሬዎችን ለማቅረብ ያገለግላሉ. [65] እነዚ ቅርጫቶች በተለምዶ በ 3 ቡድን ሲከፈሉ ከነዚ ውስጥ 2 ቱ ጥለት እና ዲዛይን ይጋራሉ። [65] ከአሚር ነደባ እና ከዴራ ቀጥሎ፣ ግድግዳው በቅርጫት የተሞሉ ሳህኖች ጥንድ ጥንድ ሆነው ያጌጡ ናቸው።
[65] እነዚህ የቁርስ ሳህን የሚያህሉ ሲሆኑ በባህላዊ መንገድ ዳቦ ለማቅረብ ያገለግላሉ። [65] ከመካከላቸው ሁለቱ "የአማት
ቅርጫት " ወይም ሀማት ሞት ይባላሉ እና እነዚህም በሠርግ ስነ ስርአት ላይ ከሙሽሪት ቤተሰብ በኩል ለአማቾች ይሰጣሉ፡፡
ከሐረር ወደ ሌላ አካባቢ የሚፈልሱ ሰዎች የተለያዩ የኪነ-ህንፃ ስታይል ባሏቸው ህንጻዎች ውስጥም ቢሆን መኖሪያቸው በተቻለ መጠን በተለመደው የሀረሪ ቤት አቀማመጥ እንዲመስል ለማድረግ ይሞክራሉ። [65] በዚህም መሰረት ቤታቸው በባህላዊ ቤት ያለውን ጊዲር ጋር እንዲመስል በመኖሪያቸው ትራስ የተደረደረባቸው ምንጣፎች መደበኛ ያልሆነ ነዳባ ይሠራሉ፣ ግድግዳዎቻቸውንም በሐረሪ ባህላዊ ቅርጫት ያጌጡ ናቸው። [65]
መስህቦች
ለማስተካከል
ታላቁ የሀረር መስጂድ
የአርተር Rimbaud ቤት እና ሙዚየም
ከተማዋን ከከበበው የድንጋይ ግንብ በተጨማሪ በጥንታዊቷ ከተማ ፈረስ መጋላ አደባባይ ላይ ያማከለ 110 መስጂዶች እና ሌሎች በርካታ አድባራት አሉት ። እንደ መድኃኔዓለም ካቴድራል ፣ የአርተር ሪምባውድ ቤት ፣ የአስራ
ስድስተኛው ክፍለ ዘመን ጃሚ መስጊድ እና ታሪካዊው የሀረር አምስት በሮች ያሉበት ታዋቂ ህንጻዎች ይገኙበታል ። . በ1960ዎቹ ለረጅም ጊዜ የቆየ ጅቦች የመመገብ ባህል ለቱሪስቶች አስደናቂ የምሽት ትርኢት ፈጥሯል ። [67] ( በሐረር የጅቦችን ትርኢት ይመልከቱ ።)
ሌሎች ትኩረት የሚስቡ ቦታዎች ከተማዋን የሚመለከት ከፍተኛ ተራራ አምባ ፣ ቁንዱዶ ወይም “ደብሊው” ተራራ፣ ጥንታዊ
የዱር ፈረሶችን መኖሪያነት ያገለግላል ። እነዚ በአደጋ ላይ ያሉ የዱር ፈረሶች እ.ኤ.አ. የ 2008 በሳይንሳዊ ተልኮ ፕሮግራም እንዲጠበቁ የማድረግ ጥረት አድርጓል። [68]
የሐረር ቢራ ፋብሪካ የተቋቋመው በ1984 ዓ.ም ሲሆን የቢራውን ናሙና በሐረር ቢራ ፋብሪካ አጠገብ በሚገኘው የቢራ ፋብሪካ ማሕበራዊ ክበብ ነው።[69][70]
ትክክለኛነት
ለማስተካከልሐረር ጁጎል በአንፃራዊነት በጥሩ ሁኔታ ተጠብቆ የቆየ ታሪካዊ ከተማ ትውፊቷን፣የከተማውን እደ ጥበብ እና የበለፀገ
የሀረሪ ሙስሊም ባህላዊ ቅርሶቿን እስከ አሁን ድረስ ጠብቃ የኖረች ብርቅዬ ምሳሌ ነች። በአፍሪካ ከሚገኙ ቅዱሳን
የእስልምና ከተሞች አንዷ እና በክርስቲያን ኢትዮጵያ ውስጥ የአናሳዎች ክልል ዋና ከተማ ነች። ታሪካዊቷ ከተማ በአካል
የተገደበ እና በ 16 ኛው ክፍለ ዘመን በታነጹ የግንብ አጥር በጥሩ ሁኔታ የተገለጸች እና ባህላዊ ማንነቱ እና መቼቱ ምስራቃዊ እና
ደቡብ-ምስራቅ በኩል እስከ አሁን ዘመን ስእንዲቆይ ተደርጓል። ይሁን እንጂ ተገቢ ያልሆኑ ጣልቃ ገብነቶች ለምሳሌ ታሪካዊ ቤቶችን ኮንክሪት እና በፕላስተሪንግ በመጠቀም ወደ ዘመናዊነት መለወጥ እንዲሁም የእንጨት በሮችን ወደ ብረት መቀየር, ባህላዊ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን መፈጠር እና እንደ የቴሌቪዥን አንቴናዎች ያሉ ምስላዊ ተፅእኖዎች ቀስ በቀስ የታሪካዊውን የማንነት መገለጫዎች ትክክለኛነት ላይ ተጽዕኖ እያሳደሩ ናቸው.፡፡
እህት ከተሞች
ለማስተካከልሀገር | ከተማ |
---|---|
ፈረንሳይ | ቻርልቪል-ሜዚየርስ |
ዩናይትድ ስቴተት | ክላርክስተን |
ጅቡቲ | አርታ |
ቱሪክ | ሰኒሉርፋ |
ታዋቂ ነዋሪዎች
ለማስተካከልየሐረር የመጨረሻ አሚር አብዱላህ II ኢብኑ አሊ አብድ አሽ-ሻኩር
አባድር ኡመር አር-ሪዳ ፣ ታዋቂው የሙስሊም ቅዱስ እና የሀረር መስራች
አምሃ ሥላሴ ፣ የኢትዮጵያ ኢምፓየር ንጉሠ ነገሥት (የተሾመ)
ማህፉዝ ፣ የአዳል ሱልጣኔት ኢማም እና ጄኔራል
ባቲ ዴል ዋምባራ ፣ የአህመድ ኢብኑ ኢብራሂም አል-ጋዚ ባለቤት
የሐረር አሚር ኑር ኢብኑ ሙጃሂድ
የአል-አህባሽ መሪ አብደላህ አል-ሀረሪ
የአህመድናጋር ሱልጣኔት መሪ ማሊክ አምባር
የሐረር ኢሚሬት መስራች አሊ ኢብኑ ዳዑድ
አምባሳደር መሀመድ አብዱራህማን፣ የመጀመርያ የሀረሪ ጠበቃ፣ የሀጂ አብዱላሂ ሳዲቅ የልጅ ልጅ
ሀጂ አብዱላሂ አሊ ሳዲቅ ፣ ነጋዴ እና የኦጋዴን አስተዳዳሪ 1889-1914
ፈረንሳዊው ገጣሚ አርተር ሪምባውድ በነጋዴነት በሐረር ሰፍሮ በ1880 እና 1891 ዓ.ም.
የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ኃይለ ሥላሴ
የአዳል ሱልጣኔት መሪ አህመድ ኢብኑ ኢብራሂም አል-ጋዚ
ሼክ ማዳር ሺርዋ ፣ የሃርጌሳ ታሪቃን (ሃይማኖታዊ ማህበረሰብን) የመሰረተው የሶማሊያ ሼክ
ተጨማሪ ንባቦች
ለማስተካከልየሀረሪ ቋንቋ
የሀረሪ ህዝብ
ምስራቅ ሀረርጌ
ምዕራብ ሀረርጌ
ድሬዳዋ
ሀረር ቢራ ፋብሪካ
በሐረር የቡና ምርት
ሃርጌሳ ፣ በሶማሌላንድ ውስጥ የምትገኝ ከተማ "ትንሿ ሀረር" ትባላለች።
እስልምና በኢትዮጵያ
ሀረር በእስልምና ያለው ጠቀሜታ
ፕሮጀክት ሀረር
የስልጤ ህዝብ ፣ ከሀረር ተወላጅ ነኝ የሚል ብሄረሰብ
በኢትዮጵያ የዓለም ቅርሶች ዝርዝር
ዋቢዎች
ለማስተካከል- ^ Population and Housing Census 2007 – Harari StatisticalCentral Statistical AgencyRetrieved 19 November 2021.
- ^ Population Projection Towns as of July 2021" (PDF). Ethiopian Statistics Agency. 2021. Retrieved 31 May 2022
- ^ Chisholm, Hugh, ed. (1911). "Harrar" . Encyclopædia Britannica. Vol. 18 (11th ed.). Cambridge University Press. p. 16.
- ^ Leslau, Wolf (1959). "An Analysis of the Harari Vocabulary". Annales d'Ethiopie. 3: 275. doi:10.3406/ethio.1959.1310.
- ^ ሀ ለ Wehib, Ahmed (October 2015). History of Harar and Harari (PDF). Harari people regional state, culture, heritage and tourism bureau. p. 5.
- ^ Baynes-Rock, Marcus. Among the Bone Eaters Encounters with Hyenas in Harar. Penn State University Press.
- ^ "Panda sanctuary, tequila area join UN World Heritage sites". Un.org. 2006-07-13. Retrieved 2013-07-23.
- ^ "Harar Jugol, the Fortified Historic Town". World Heritage List. UNESCO World Heritage Centre. Retrieved 6 August 2009.
It is considered 'the fourth holy city' of Islam, having been founded by a holy missionary from the Arabic Peninsula.
- ^ "Five new heritage sites in Africa". BBC. July 13, 2006. Retrieved 2006-12-18.
Harar Jugol, seen as the fourth holiest city of Islam, includes 82 mosques, three of which date from the 10th Century, and 102 shrines.
- ^ Siegbert Uhlig, Encyclopaedia Aethiopica: He-N, Volume 3, (Otto Harrassowitz Verlag: 2007), pp.111 & 319.
- ^ Richard Pankhurst, History of Ethiopian Towns (Wiesbaden: Franz Steiner Verlag, 1982), p. 49.
- ^ Insoll, Timothy (2003). The Archaeology of Islam in Sub-Saharan Africa. Cambridge: Cambridge University Press. pp. 77–8. ISBN 0-521-65171-9. Retrieved 25 August 2021.
- ^ Gebissa, Ezekiel (2004). Leaf of Allah: Khat & Agricultural Transformation in Harerge, Ethiopia 1875-1991. Ohio State University Press. ISBN 978-0-85255-480-7.page 36
- ^ Belayneh, Anteneh (2014). "Ethnomedicinal plants used to treat human ailments in the prehistoric place of Harla and Dengego valleys, eastern Ethiopia". Journal of Ethnobiology and Ethnomedicine. 10: 18. doi:10.1186/1746-4269-10-18. PMC 3933041. PMID 24499509.
- ^ insoll, Timothy. "First Footsteps in the Archaeology of Harar, Ethiopia". Journal of Islamic Archaeology. Archived from the original on 2020-02-04. Retrieved 2020-06-18.
- ^ Adler,Elkan Nathan (2014). Jewish Travellers. Routledge. p. 61. ISBN 978-1-134-28606-5.
- ^ The St. James's Magazine. Houlston & Wright. 1868. p. 84.
- ^ The Ethno-History of Halaba People (PDF). p. 15. Retrieved 20 October 2017.
- ^ Østebø, Terje (2011). Localising Salafism: Religious Change Among Oromo Muslims in Bale, Ethiopia. BRILL. p. 56. ISBN 978-90-04-18478-7.
- ^ Braukämper, Ulrich (2002). Islamic History and Culture in Southern Ethiopia: Collected Essays. LIT Verlag Münster. ISBN 978-3-8258-5671-7., page 107
- ^ Hassen, Mohammed (2015). The Oromo and the Christian Kingdom of Ethiopia: 1300-1700. Boydell & Brewer. p. 99. ISBN 978-1-84701-117-6.
- ^ Luling, Virginia (2002). Somali Sultanate: The Geledi City-state Over 150 Years. Transaction Publishers. ISBN 978-0-7658-0914-8.
- ^ Budge, E. A. Wallis (2014). A History of Ethiopia: Volume I (Routledge Revivals): Nubia and Abyssinia. Routledge. p. 297. ISBN 978-1-317-64915-1.
- ^ Crass,Joachim (2001). "The Qabena and the Wolane: Two peoples of the Gurage region and their respective histories according to their own oral traditions". Annales d'Éthiopie. 17 (1): 180. Retrieved 15 February 2017.
- ^ Zekaria,Ahmed (1991). "Harari Coins: A Preliminary Survey". Journal of Ethiopian Studies. 24: 23–46. JSTOR 41965992. Retrieved 28 August 2021.
- ^ Richard Pankhurst, An Introduction to the Economic History of Ethiopia (London: Lalibela House, 1961), p. 267.
- ^ Reclus, Elisée (1886). The Earth and its Inhabitants The Universal Geography Vol. X. North-east Africa (PDF). J.S. Virtue & Co, Limited, 294 City Road.
Two routes, often blocked by the inroads of plundering hordes, lead from Harrar to Zeila. One crosses a ridge to the north of the town, thence redescending into the basin of the Awash by the Galdessa Pass and valley, and from this point running towards the sea through Issa territory, which is crossed by a chain of trachytic rocks trending southwards. The other and more direct but more rugged route ascends north-eastwards towards the Darmi Pass, crossing the country of the Gadibursis or Gudabursis. The town of Zeila lies south of a small archipelago of islets and reefs on a point of the coast where it is hemmed in by the Gadibursi tribe. It has two ports, one frequented by boats but impracticable for ships, whilst the other, not far south of the town, although very narrow, is from 26 to 33 feet deep, and affords safe shelter to large craft.
- ^ Richard Pankhurst, The Ethiopian Borderlands (Lawrenceville: Red Sea Press, 1997), pp. 375-377
- ^ Ahmad b. Abu Bakr. Encyclopedia Aethiopica.
- ^ Jonas, Raymond (2011). The Battle of Adwa. Harvard University Press. p. 74.
- ^ Toledano, Ehud. The Ottoman Slave Trade and Its Suppression. Princeton University Press. p. 31.
- ^ Hunter, Frederick (1877). An Account of the British Settlement of Aden in Arabia. Cengage Gale. p. 41.
- ^ Burton. F., Richard (1856). First Footsteps in East Africa. p. 360.
- ^ Abdullahi, Abdurahman (2017-09-18). Making Sense of Somali History: Volume 1. p. 80. ISBN 9781909112797.
- ^ Zewde, Bahru (17 March 2002), A History of Modern Ethiopia, 1855–1991, Ohio University Press, p. PT74, ISBN 978-0-8214-4572-3
- ^ Munro-Hay, Stuart (2002). Ethiopia, the Unknown Land: A Cultural and Historical Guide. Bloomsbury Academic. p. 184. ISBN 978-1-86064-744-4.
- ^ Caulk, Richard A. (1971). "The Occupation of Harar: January 1887". Journal of Ethiopian Studies. 9 (2): 1–20. JSTOR 41967469.
- ^ Berbera-Harrar Railway Survey Vol. 1 (Report)
- ^ Ahmed, Wehib M. (2015). History of Harar and the Hararis (PDF). Harari People Regional State Culture, Heritage and Tourism Bureau.
In the 19th century the jurisdiction of the Amirs was limited to Harar and its close environs, while the whole trade routes to the coast passed through Oromo and the Somali territories. There were only two practicable routes: one was the Jaldeissa, through Somali Issa and Nole Oromo territories, the other of Darmy through the Gadaboursi. The Somali, who held a monopoly as transporters, took full advantage of the prevailing conditions and the merchants were the victim of all forms of abuse and extortion... Under the supervision of these agents the caravan would be entrusted to abbans (caravan protector), who usually belonged to the Issa or Gadaboursi when destined to the coast and to Jarso when destined for the interior.
- ^ Anthony Mockler, Haile Selassie's War (New York: Olive Branch, 2003), pp. 145, 367f
- ^ John Spencer, Ethiopia at Bay: A personal account of the Haile Selassie years (Algonac: Reference Publications, 1984), pp. 282-287
- ^ The Navy Everywhere, 1919. p. 244
- ^ Wild, Antony (2004). Coffee: A Dark History. Fourth Estate. ISBN 978-1-84115-649-1.
- ^ Libermn, Mark (2003). "LANGUAGE RELATIONSHIPS: FAMILIES, GRAFTS, PRISONS". Basic Reference. pittsburgh, USA: University Pennsylvania Academics. 28: 217–229. Retrieved 2012-04-27.
- ^ "Climate-Data : Ethiopia". Retrieved 11 July 2013
- ^ "Harar". BRILL
- ^ Mordechai, Abir. Trade and Politics in the Ethiopian Region 1830-1855 (PDF). University of London. p. 247.
- ^ "Journal of the Asiatic Society of Bombay". Asiatic Society of Bombay. 16: 121. 1885.
- ^ Burton, Richard (1894). First Footsteps in East Africa. Tylston and Edwards. p. 19.
Up to the city gates the country is peopled by the Gallas.
- ^ "local history of Ethiopia" (PDF). Nordic Africa Institute. Archived from the original (PDF) on 10 October 2017. Retrieved 9 October 2017.
- ^ Plural Medical Systems In The Horn Of Africa: The Legacy Of Sheikh Hippocrates. Routledge. 28 October 2013. ISBN 9781136143380.
- ^ Ficquet, Éloi (2014). The Life and Times of Lïj Iyasu of Ethiopia: New Insights. LIT Verlag Münster. p. 158. ISBN 9783643904768.
- ^ Adunga, Ayanlem. "Harari" (PDF). Ethiopian Demography and Health.
- ^ Wehib, Ahmed (October 2015). History of Harar and Harari (PDF). Harari people regional state, culture, heritage and tourism bureau. p. 141. Retrieved 26 November 2017.
- ^ Matshanda, Namhla (2014). Centres in the Periphery: Negotiating Territoriality and Identification in Harar and Jijiga from 1942 (PDF). The University of Edinburgh. p. 199. S2CID 157882043. Archived from the original (PDF) on 2020-01-31.
- ^ Shetler, Jan. "Building a "City of Peace" through Intercommunal Association Muslim-Christian Relations in Harar, Ethiopia, 1887-2009" (PDF). Manchester University.
- ^ Feener, Michael (2004). Islam in World Cultures: Comparative Perspectives. ABC-CLIO. p. 230. ISBN 9781576075166.
- ^ The universal geography : earth and its inhabitants (PDF).
- ^ Burton, Richard (1856). First Footsteps in East Africa (1st ed.). Longman, Brown, Green, and Longmans.
and thence strikes south-westwards among the Gudabirsi and Girhi Somal, who extend within sight of Harar.
- ^ Lewis, I. M. (1998). Saints and Somalis: Popular Islam in a Clan-based Society. p. 100. ISBN 9781569021033.
- ^ Slikkerveer (2013-10-28). Plural Medical Systems In The Horn Of Africa: The Legacy Of Sheikh Hippocrates. Routledge. p. 140. ISBN 9781136143304.
- ^ Lewis, I. M. (17 March 2003). A Modern History of the Somali: Nation and State in the Horn of Africa. ISBN 9780821445730.
- ^ Lewis, I. M. (2000). Saints and Somalis: Popular Islam in a Clan-based Society (PDF). p. 11. ISBN 9781569021033.
Including the land round Harar and Dire Dawa inhabited by the Somalis of the 'Iise and Gadabuursi clans.
- ^ "Harar Jugol, the Fortified Historic Town". UNESCO World Heritage Convention. Retrieved 3 December 2022.
- ^ Hecht, Elisabeth-Dorothea (1982). "The City of Harar and the Traditional Harar House". Journal of Ethiopian Studies. 15: 57–78. JSTOR 41965897. Retrieved 25 August 2021
- ^ Abubaker, Abdulmalik (2016). The Relevancy of Harari Values in Self Regulation (PDF). University of Alabama. pp. 46–58.
- ^ "The hyena man of Harar". BBC News. 2002-07-01. Retrieved 2013-07-23.
- ^ "Wild horses exist in Ethiopia, but face danger of extinction: Exploratory Team". Archived from the original on July 15, 2009.
- ^ "Embassy staff visits Harar Brewery". Norway.org.et. Archived from the original on 2012-03-19. Retrieved 2013-07-23.
- ^ EthioNetworks.com. "Harrar Brewery, Ethiopia". Ethiopianrestaurant.com. Retrieved 2013-07-23.