የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቱት የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቱት በኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት የጤና ምርምር ተቋም ሆኖ የቆየ ድርጅት ነው። የተቋቋመው በቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዘመነ መንግስት ሲሆን ስሙም የፓስተር ኢንስቲቱት በሚል ነበር። ከተመሰረተ ጀምሮ እንደ ማዕከላዊ የጤና ጥናት ማዕከል ሲሰራ የቆየ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ስሙ ወደ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቱት ተቀይሯል።