አሞራ

የወፍ ዓይነት የተለመደ ስም

አሞራ መንገድ ጠራጊ ወፍ በተለይ የአውሬ በድን የሚበላ ነው። አሞራዎች በማናቸውም አህጉር ላይ ሲገኙ በአንታርክቲካ ወይም በፓሲፊክ ደሴቶች ላይ ግን አይገኙም።

አሞራ

ከአሞሮች ብዙዎቹ ከላባ መላጣ የሆነ ራስ ይኖራቸዋል። ምክንያቱ ባለ-ላባ ራስ በየጊዜ በደም ተቀብቶ ለማጽዳት ያስቸግረው እንደ ነበር ይመስላል። ከዚያ በላይ በወንዝ ውስጥ በቀላሉ ለማጽዳት ያስችለዋል።

አሞራዎች በ2 ክፍሎች ይገኛሉ። በአፍሪካእስያና በአውሮፓ የሚገኘው አሞራ ወገን ከጭላትንሥርጭልፊትጥምብ አንሣ ጋር በጭላት አስተኔ ውስጥ ይከተታል። በድን ለማግኘት የሚቻላቸው በማየት ብቻ ነው።

በአዲስ አለም (አሜሪካዎች) የሚገኙት አሞሮች ሌላ ወገን ናቸው። እነሱ መብል የሚያገኙ በማሽተት ነው።