ኔያንደርታል (ጀርመንኛNeandertal) በጀርመን አገር በ2 ገደል መካከል በኖርድራይን-ቬስትፋለን ክፍላገር የሚገኝ ሸለቆ ነው።

የኔያንደርታል ሥፍራ በስሜን-ምዕራብ ጀርመን

ከ1800 ዓ.ም. ግድም አስቀድሞ የዚህ ሸለቆ ስያሜዎች Das Gesteins (/ዳስ ገሽታይንስ/ «የጭንጫው») ወይም Das Hundsklipp (/ዳስ ሁንትስክሊፕ/ «የውሻ ገደል») ነበሩ።

1666 እስከ 1671 ዓ.ም. ድረስ፥ ስመ ጥሩ የጀርመን ፕሮቴስታንት ሠባኪ፣ አስተማሪና መዝሙር ጸሐፊው ዮኪም ኔያንደር በአካባቢው ሲኖር ወደ ሸለቆው መሄድና በዚያ ተማሪዎችን መሰብሰብ ይወድድ ነበር። የቤተሠቡ ስም ቀድሞ Neumann (/ኖይማን/ «አዲስ ሰው») ሲሆን አያቱ ግን እንደ ዘመኑ ሞድ ወደ ግሪክኛ አስተርጉሞት Neander /ኔያንደር/ ሆኖ ነበር።

በ1800 ዓ.ም. ግድም ዮኪም ነያንደርን ለማክበር የሸለቆው መጠሪያ Neandershöhle (/ነያንደርስሄውለ/ «የኔያንደር ስንጥቅ» ሆነ። ከ1842 ዓ.ም. በኋላ ይህ ወደ Neanderthal (/ኔያንደርታል/፥ «ኔያንደር ሸለቆ») ተለወጠ።

1848 ዓ.ም. በሸለቆው ውስጥ ጥንታዊ የሰው ልጅ ቅሪተ አካል በተገኘበት ዓመት፥ «ኔያንደርታል» የሚለው ቃል ዝነኛ ሆነ። ዛሬም «ኔያንደርታል» ለብዙዎቹ የጥንታዊ ሰው ልጅ ዝርያ አይነት ትርዒት ያስገባል። የቃሉ መነሻ ፍች ግን እንዳጋጣሚ ከግሪክና ከጀርመንኛ «አዲስ» «ሰው» «ሸለቆ» መሆኑን ልንረዳ እንችላለን።

1893 ዓ.ም. የሸለቆው አጻጻፍ በጀርመንኛ በይፋ ከNeanderthal ወደ Neandertal ተቀየረ። አጠራሩ ግን እንደ በፊቱ «/ኔያንደርታል/» ነው።