ኒል አርምስትሮንግ
(ከኔል አርምስትሮንግ የተዛወረ)
ኒል አርምስትሮንግ አሜሪካዊ የህዋ መንኩራኩር አብራሪ ሲሆን በጁላይ 20፣ 1969 እ.ኤ.አ. በአፖሎ ፲፩ የመንኩራኩር ጉዞ ጨረቃ ላይ በመራመድ የመጀመሪያ የሰው ልጅ ነው። ይህ በጣም ጎበዝ ሥራ ነው። ናሳን እ.ኤ.አ በ1962 ከመቀላቀሉ በፊት የአሜሪካ ባህር ሃይል ውስጥ የተዋጊ ጀት አብራሪ ሆኖ በኮሪያ ጦርነት ወቅት ተሳትፎ ነበር። ናሳን ተቀላቅሎ ከአራት አመት በኋላ ወደ ህዋ የመጀመሪያውን ጉዞ ያደረገ ሲሆን በዛም ጉዞ የመጀመሪያውን በሰው ልጅ የታገዘ የመንኩራኩሮች መያያዝ አከናውኗል። ከዚህ ጉዞው በኋላ ወደ ህዋ ያልሄደው ኒል በተወለደ በ 82 አመቱ በኦገስት 26፣ 2012 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል። [1]
ቅድመ ታሪክ
ለማስተካከልበሐምሌ ፳፱ ቀን ፲፱፻፳፪ ዓ.ም. (ኦገስት 5, 1930 እ.ኤ.አ.) በኦሃዮ ክፍላገር፣ አሜሪካ የተወለደው ኒል አርምስትሮንግ ከወላጆቹ እና እሱን ጨምሮ ሶስት ልጆች ባሉበት ቤተሰብ ውስጥ አደገ።
የህዋ መንኩራኩር አብራሪነት
ለማስተካከልከውትድርና በኋላ ወደ ኮሌጅ ገብቶ ትምህርቱን የተከታተለው ኒል ከተመረቀ በኋላ ለምርምር ፕሮግራሞች ሞካሪ አብራሪ ለመሆን ተመዝግቦ እ.ኤ.አ በJuly 1955 ተሳክቶለት ስራ ጀመረ።
ማጣቀሻዎች
ለማስተካከል- ^ "ጨረቃ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተራመደው ኒል አርምስትሮንግ ከዚህ አለም በሞት ተለየ". thearadaonline.com (26 Aug 2012). Archived from the original on 26 September 2012. በ28 Aug 2012 የተወሰደ.