ናጊብ ማህፉዝ
ናጊብ ማህፉዝ በ1988 እ.ኤ.አ. በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ሽልማትን የተቀዳጀ ግብጻዊ ደራሲ ነው።
ማህፉዝ ካይሮ ውስጥ ገማልያ በተባለው ሰፈር ዲሴምበር 11፣ 1911 እ.ኤ.አ. ተወለድ። የመጠሪያ ስሙን የወረሰው ሲወለድ አዋላጅ ሃኪም ከነበሩት ከፕሮፌሰር ናጊብ ማህፉዝ ፓሻ ነው። ማህፉዝ ለረጅም ዘመን በመንግስት መስሪያቤቶች ውስጥ ያገለገል ሲሆን በስነ-ጽሁፉም ዘርፍ 34 ወጥ ልብ-ወለዶች፣ ከ350 የሚዘሉ አጫጭር ታሪኮች፣ ከደርዘን በላይ የሲኒማ ድርሰቶች፣ እና አምስት ተውኔቶችን አበርክቷል።
በ1971 ያሳተመው «ጭውውት በአባይ ወንዝ ላይ» (Chitchat on the Nile) የተሰኘው ድርሰቱ ተወዳጅነትን ካተረፉለት ስራዎቹ መካከል ሲሆን የገማል አብድል ናስር አገዛዝ በግብጽ ማህበረሰብ ላይ ያደረሰውን ዝቅጠት የሚተች ነው።
«የገብላዊ ልጆች» (Children of Gebelawi) የተሰኘው ሌላው ልብ-ወለዱ ተምሳሌታዊ በሆነ መልክ እግዚአብሄርን እና የታላላቆቹን እምነቶች መስራቾች (ሙሴን፣ እየሱስን እና መሃመድን) በገጸባህርይነት የቀረጸበት በመሆኑ አምላክን በመገዳደር አስወንጅሎት መጽሃፉም በግብጽ ውስጥ እንዳይሰራጭ ለረጅም ጊዜ ታግዶ ቆይቷል። በ1989 ሳልማን ሩሽዲ ሰይጣናዊ ጥቅሶች (Satanic Verses) የተሰኘ መጽሃፉን በማሳተሙ የኢራኑ መሪ አያቶላህ ሮላህ ኾሚኒ የግድያ ትእዛዝ ካስተላለፉበት በኋላ ግብጻዊው የስነ-መለኮት መርማሪ ኦማር አብዱል ራህማን ለጋዜጠኞች በሰጠው ቃለ-መጠይቅ ላይ «ማህፉዝ 'የገብላዊ ልጆች'ን ሲያሳትም ተገቢው ቅጣት ተሰጥቶት ቢሆን ኖሮ ሩሽዲ 'ሰይጣናዊ ጥቅሶች'ን ለማሳተም ባልደፈረ ነበር» በማለቱ ይህንኑ ቃሉን እንደ ግድያ ትእዛዝ የወሰዱ ጽንፈኞች በ1994 ዓ.ም ማህፉዝን በስለት አንገቱ ላይ በመውጋት ጉዳት አድርሰውበታል። አጥቂዎቹ አላማቸው ማህፉዝን መግደል ነበር ቢባልም እሱ ግን በህይወት ለመትረፍ ችሏል። ይኽ መጽሃፍ ከ2006 መጀመሪያ ወሮች አንስቶ እንደ አዲስ ግብጽ ውስጥ ታትሞ መሰራጨት ጀምሯል።
ማህፉዝ የአንዋር ሳዳት መንግስት ደጋፊነቱ የታወቀ ሲሆን ግብጽ ከእስራኤል መንግስት ጋር በካምፕ ዴቪድ ያደረገችው የሰላም ስምምነት ደጋፊም ስለነበር ድርሰቶቹ ለብዙ ዓመታት በአረብ አገራት ታግደው ቆይተው እገዳው የተነሳላቸው የኖቤል ሽልማትን እንዳሸነፈ ከተሰማ በኋላ ነው።
ማህፉዝ የኖቤልን ሽልማት ለመቀበል ለግብጽም ሆነ ለአረቡ ዓለም የመጀመሪያው ሲሆን በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ተሸላሚ ከሆኑት ሰዎች ሁሉ የረጅም እድሜ ባለቤት በመሆን ሶስተኛ ደረጃን የያዘ ሰው ነው።
ማህፉዝ ኦገስት 30 ቀን፣ 2006 አርፎ ቀብሩ በኦገስት 31 ቀን ካይሮ ውስጥ በሚገኘው የአል ረሽዳን መስጊድ ተፈጽሟል።
የድርሰት ሥራዎች
ለማስተካከል- Old Egypt (1932) مصر القديمة
- Whisper of Madness (1938)همس الجنون
- Mockery of the Fates (1939) عبث الأقدار
- Rhadopis of Nubia (1943) رادوبيس
- The Struggle of Tyba (1944) كفاح طيبة
- Modern Cairo (1945) القاهرة الجديدة
- Khan al-Khalili (1945) خان الخليلى
- Midaq Alley (1947) زقاق المدق
- The Mirage (1948) السراب
- The Beginning and The End (1950) بداية ونهاية
- The Cairo Trilogy الثلاثية
- Palace Walk (1956) بين القصرين
- Palace of Desire (1957) قصر الشوق
- Sugar Street (1957) السكرية
- Children of Gebelawi (1959) أولاد حارتنا
- The Thief and the Dogs (1961) اللص والكلاب
- Quail and Autumn (1962) السمان والخريف
- God's World (1962) دنيا الله
- Zaabalawi (1963)
- The Search (1964) الطريق
- The Beggar (1965) الشحاذ
- Adrift on the Nile (1966) ثرثرة فوق النيل
- Miramar (1967) ميرامار
- The Pub of the Black Cat (1969) خمارة القط الأسود
- Chitchat on the nile (1971) ثرثرة فوق النيل
- A story without a beginning or an ending (1971)حكاية بلا بداية ولا نهاية
- The Honeymoon (1971) شهر العسل
- Mirrors (1972) المرايا
- Love under the rain (1973) الحب تحت المطر
- The Crime (1973) الجريمة
- al-Karnak (1974) الكرنك
- Respected Sir (1975) حضرة المحترم
- The Harafish (1977) ملحمة الحرافيش
- Love above the Pyramid Plateau (1979) الحب فوق هضبة الهرم
- The Devil Preaches (1979) الشيطان يعظ
- Love and the Veil (1980) عصر الحب
- Arabian Nights and Days (1981) ليالى ألف ليلة
- Wedding Song (1981) أفراح القبة
- One hour remains (1982) الباقي من الزمن ساعة
- The Journey of Ibn Fattouma (1983) رحلة إبن فطومة
- Akhenaten, Dweller in Truth (1985) العائش فى الحقيقة
- The Day the Leader was Killed (1985) يوم مقتل الزعيم
- Fountain and Tomb (1988)
- Echoes of an Autobiography (1994)
- Dreams of the Rehabilitation Period (2004) أحلام فترة النقاهة
- The Seventh Heaven (2005)
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |