አሚር ኑር ሙጃሂድ

(ከኑር የተዛወረ)

ሙሉ ስማቸው፤ ዓሊ ዕብን አብዱላህ ዓል-ዱሂ ሱሃ (በሱማልኛ፡- ኑር ዒብን-ሙጃሂድ. በአረብኛ፦نور بن مجاهد‎) ፤ የሞቱት እ.አ.አ. 1567፣ ትርጉሙም በአጭሩ፦ ብርሃን ማለት ነው። ከ ሱማሌ ዳሮድ ጎሳ ቅርንጫፍ ከሆነው የማረሃን ክፍል፣ ንዑስ ክፍል አህል-ሱሃውያን የተወለዱ ሲሆን በ16ኛው ክፍለ ዘመን የሐረር ዓሚር ነበሩ። የአህመድ ዒብን-አልጋዚ (ግራኝ አህመድአህመድ ጉሬይ) ሚሽት የነበረችውን ባቲ ዲል-ወንብራ አግብተውና ወራሽ ሆነው የሙስሊሙን ሕብረተሰብ በመምራት ከክርስትያኑ የኢትዮጵያ ተቀናቃኝ ኃይል ጋር የነበረውን ጦርነት መርተዋል።

ታሪካቸው

በኃይማኖት መሪነታቸው ሚና የተነሳ፣ ዓሚር ኑር "ሳሂብ አል-ፋትህ አት-ታኒ" ወይም "የሁለተኛው ወረራ መሪ" የሚል ስም ተሰጥቷቸዋል። የ እስላሙን ጦር ይመሩ የነበሩት ኢማም አህመድ በ1943 በጦርነት ሲገደሉ፡ የሙስሊሙ ኃይል ውስጥ መደናገጥ ፈጥሮ ወደ ሐረር እንዲያፈገፍግ ተገደደ። ኑር የኢማሙን ምሽት ባቲ ድል-ውንብራን በማግባት የከተማዋን የመሪነት ሚና ተረክበው በ1550 ቱ ወረራ የተጎዳችዉን የሐረር ከተማ መልሰው አፀኑ። ከ1550-51 ባለው ጊዘ ውስጥ የዓሚርነትን ማዕረግ ከተቀዳጁ በኋላም ትኩረታቸውን የተበታተነውን ሠራዊት መልሶ ስር ዓት በማስያዝና በከተማዋም ዙርያ የግንብ አጥር በማሰራቱ ላይ አደረጉ። በ 1554-55 ዓሚር ኑር በጅሃድ ወደ ባሌ ቆላማ አካባቢዎችና ወደ ሃድያ አገሮች ዘመቱ። በ 1559 ፈጠጋርን ወረሩ፤ እዚያም ከ ኢትዮጵያው ንጉስ ዓጼ ገላውዴዎስ ጋር ጦርነት ገጥመው በውጊያዉም ዓጼዉን ገደሉ። በመቀጠልም ለሚቀጥሉት 12 ዓመታት ወደ ም ዕራቡ ክፍል እስከ ጊቤ ድረስ ከዘለቁ በኋላ እንደ አፈ-ታሪኩ ዘገባ "ከፋ"! ወይም "በቃ"! ብለው ወደ ሐረር ተመለሱ። አንዳንዶች "ከፋ" የሚለው ቃል ከዚህ ታሪካዊ ኩነት የመነጨ ነው ይላሉ።

ኑር ከከተማቸው ርቀው በነበሩበት ወቅት፡ በከተማዋ ውስጥ የውስጥ ስልጣን ሽሚያ ተከስቶ ነበር። በዚሁም ወቅት ሐረር በኦሮሞዎች ተስፋፊ ኃይል የመደምሰስ አደጋ አንዣቦባት ነበር። በዚህ ወቅት ነው የከተማዋ ግንብ የተሰራው። ሆኖም በዘልማዳዊው ታሪክ ዓሚሩ ከ ሁለት የአካባቢ ባላባቶች፡አሁ-አባዲር እና አሁ-ዓሊ ጋር በመሆን ግንቡን አሰሩት ይላሉ። በ 1567፣ በተደጋጋሚ የተፈጸመው የኦሮሞ ኃይል ወረራ ምክንያት በከተማው አሰቃቂ የሆነ ረሃብ ገባ። ዓሚሩም ከተማዋን ለቀው በመውጣት ለ3 ወራት ጠንካራ የመከላከልና የቅጣት ዘመቻ በወራሪው የኦሮሞ ኃይል ላይ ከፈቱ። ከጦርነቱም የከተማው ሕዝብ በቸነፈር በሽታ ተወሮ ደረሱ። ዓሚሩም እራሳቸዉም በዚሁ የ ታይፈስ ወረርሽኝ በሽታ ተይዘው በዚያው ዓመት ሞቱ።

ዝናቸው

ጸሐፊዎች ዓሚሩ የጠንካራ ስብ ዕና ባለቤት እንደሆኑና፣ ኃቀኛ፣ ጠንካራ፣ እና ፍርድ-አዋቂ መሆናቸውን ይናገራሉ። ከሐረር ግንብ በተጨማሪም በከተማው ውስጥ በርካታ ሕንጻዎችን አሰርተዋል። የመቃብራቸው ቦታም ከደብሩ ላይ ሆኖ በበርካታ መኖርያ ቤቶችና የፍርድ ሸንጎዎች ተከቧል። እስከ አሁንም ድረስ የቀብር ቦታቸው በአክባሪዎቻቸው ይዘየራል (ይጎበኛል)።

^ Encyclopaedia Africana: Dictionary of African Biography, Volume 1: Ethiopia and Ghana, p. 118 ^ R.Basset (editor), Histoire de la conquete de l’Abyssinie (History of the Conquest of Abyssinia), Paris, 1897–1901 ^ Dr. E. Cerulli, Documenti arabi per la storia dell’Ethiopia, Memoria della Accademia Nazionale dei Lincei, Vol. 4, No. 2, Rome, 1931 ^ Richard Pankhurst, The Ethiopian Borderlands (Trenton: Red Sea Press, 1997), p. 373