ቲሪጋን
ቲሪጋን በሱመር የነገሠው የጉታውያን መጨረሻ ንጉሥ ነበር። በሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር መሠረት ዘመነ መንግሥቱ ለአርባ ቀናት ብቻ ነበር።
በሌላ ጽላት ዘንድ የቲሪጋን ሥራዊት ወደ ሱመር ገብተው መስኖዎቹን ገደቡ፣ መንገዶቹን ዘጉ፣ ማንም ሰው ከከተማው መውጣት አልደፈረም፤ በመንገዶች ሣር በቀለ። የኡሩክ ገዢ ኡቱ-ኸጛል ኃያላት ግን አሸነፋቸው፤ ቲሪጋንም ተማረከ፤ በብረት ታሥሮ ኡቱ-ኸጋል እግሩን በአንገቱ ላይ እንዳኖረ ይላል።
ቀዳሚው ሲኡም |
የሱመር ነጉሥ 1985 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ ኡቱ-ኸጛል |