ተፈራ አቡነ ወልድ (፲፱፻፳፰ ዓ.ም. ተወለደ[1]) ታዋቂ ኢትዮጵያዊፒያኖ ተጫዋች እና የዜማ ደራሲ ነበር።

የህይወት ታሪክ ለማስተካከል

ተፈራ አቡነ ወልድ በ፲፱፻፳፰ ዓ.ም. በደብረ ብርሃን በተጉለት አውራጃ ተወለደ። በማዘጋጃ ቤት ተፈራ በትምህርት ላይ ሳለ የሙዚቃ ስሜት ስላደረበት በ፲፱፻፴ ዓ.ም. በ፲፯ ዓመቱ በማዘጋጃ ቤት ተቀጥሮ በዚሁ ሙያ ላይ የዳበረ ችሎታ ለመጨበጥ ችሏል።[1]

በፒያኖ አጨዋወቱ የተደነቀ፣ ሲጫወት በሙዚቃ አጨዋወቱ ባቀማመጡና ባቀራረቡ የታወቀው ዕውነተኛ የሙዚቃ ተሰጥዖ ያለው በአንድ ጊዜ ሁለት መሣሪያዎችን እያፈራረቀ መጫወት የሚችል ነው። ከፒያኖ በፊትም ፍሉትክላርኔትሳክሶፎንአልቶን በማፈራረቅ ተጫውቷል። በዚህም ችሎታው ተመርጦ ፒያኒስት እንዲሆን ተደረገ።[1]

ተፈራ በሙዚቃ ማዋሃድና በዜማ መድረስም ስጦታ ያለው፣ ዜማን ከሸክላ በቀጥታ መገልበጥ የሚችል ባለሙያ ነው። ከደረሳቸውም ዜማዎች «የአባይ ውሃ»፣ «የዓይን ተስፋ» እና «እምነሸነሻለሁ» የተባሉት ይገኙበታል።[1]

ማጣቀሻ ለማስተካከል

  1. ^ "ናሽናል ቢብሊዮግራፊ ቡድን፣ የአንጋፋ አርቲስቶች መዝገበ የሕይወት ታሪክ፣ መጋቢት ፳፻፣ ገጽ 24-25". Archived from the original on 2011-09-29. በ2010-12-17 የተወሰደ.